Get Mystery Box with random crypto!

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ | YeneTube

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች በአግባቡ ምልሽ እንዲሰጥ በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ተጠየቀ።

ቦርዱ ዛሬ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ እስካሁን የተከናወኑ የዝግጅት ተግባራትን ዘርዝሯል። ተቃዋሚዎች በበኩላቸው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በማድነቅ በየጊዜው ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፈጣን እና በደብዳቤ ምላሽ አለመስጠቱን ወቅሰዋል። በጽሑፍ ለሚቀርቡ አቤቱታዎች በጽሑፍ ምላሽ አለመሰጠቱን በተመለከተ፦ ቅሬታውን የተቀበሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፦ «ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ» በመጠየቅ የሚቀርቡ አቤቱታዎች እጅግ መብዛታቸውን ጠቊመዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa