Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 491

2021-02-04 19:54:36
ብሄራዊ የመረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአቪዬሽን ደህንነት ሙያ ያሠለጠናቸውን 200 ኦፊሰሮች አሰመረቀ!

በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ስር የሚገኘው ብሄራዊ የመረጃ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በአቪዬሽን ደህንነት ሙያ ያሠለጠናቸውን 200 ኦፊሰሮች አስመረቀ። የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመሰገን ጥሩነህ  ተመራቂዎቹ የሀገር ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚያደርገውን  የተሳካ ጉዞ ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ እገዛ እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
12.8K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 19:51:52
ዕቃ ለማውረድና ለመጫን የተጋነነ ዋጋን የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆችን የማጣራት ሥራ በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ ለዕቃ ማውረድና መጫን የሚከፈለው ገንዘብ በዕቃ ባለቤትና በአውራጁ መካከል በሚደረገው ስምምነት እንጂ አውራጁ በተመነው ዋጋ ብቻ እዳልሆነ አስታውቀዋል።የዕቃው ባለቤት ከፈለገ እቃውን በራሱ የማውረድና የመጫን ሙሉ መብት እንዳለ ያመለከቱት ሃላፊው ፣ ባለቤቱን የመጫንና የማውረድ መብት የሚከለክሉ እንዲሁም ለመሥራትም የተጋነነ ዋጋ የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆች ተጣርተው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት በተለይ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ወረዳ 10 እና ወረዳ 12 በጎሮ፣ በቡልቡላና በሰሚት አካባቢ እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በኮዬ ፈጬና የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በመናኸሪያ አካባቢ፣ በጫኝና በአውራጅ ሥራ የተደራጁ 170 የሚሆኑ ሰዎች ለራሳቸው ከቤት ሆነው ሌሎች ሰዎችን በመቅጠር በህብረተሰቡ ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲያስፈጽሙ ተደርሶባቸው ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጠቁመዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
11.9K viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 19:49:54 በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሞጣ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሞጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

መነሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ንብረትነቱ የቻይና መንገድ ስራዎች ከሆነ ፒካፕ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የተፈጠረው።

በህዝብ መኪና ውስጥ ያሉ አራት ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የግጭቱ መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ከሞጣ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa
14.5K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 19:36:53 የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች በህወሃት ታጣቂዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሲከላከል እንደነበር ከስደተኞች መስማቱን የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞች ከጥቃት እንዲጠበቁ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አስታውቀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ራሳቸው ከ15 በላይ ስደተኞችን ማነጋገራቸውን የገለጹ ሲሆን ለህይወታቸው በመፍራት ከሽመልባና ከጻጽ መጠለያ ጣቢያዎች መውጣታቸውንና መከላከያ ሰራዊት ጥቃት እንዳይደርስባቸው እንደተከላከለላቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ተስፋሁን የኢትዮጵያ መንግስት “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” ከመጀመሩ በፊት በሽመልባ 8ሺ፤ በህጻጽ ደግሞ 11 ሺ 500 ስደተኞች ይኖሩ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን በነዚህ መጠለያ ጣቢዎች ውስጥ ምንም ስደተኛ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

በትግራይ በሚገኙ አራት የሥደተኛ መጠለያ ጣቢዎች 92ሺ ስደተኞች ይገኙ እንደነበር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከነዚህ ውስጥ በሁለቱ ጣቢያዎች ውስጥ የነበሩ ስደተኞች አሁን ላይ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባና በዛው በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በሽመልባና በህጻጽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ይኖሩ ከነበሩት መካከል አራት ሺ የሚሆኑ ስደተኞች አሁን ላይ ወደ ማይ አይኒ እና አድሀሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች መግባታቸውን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡ በስደተኞቹ ላይ ከፍተኛ ችግር መድረሱን፤መጎዳታቸውንና ሌሎችንም በተመለከተ ወደፊት የማጣራት ስራ እንደሚሰራ አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡
በሱዳን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በተመለከተ መቸ ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ የሚለውን በትክክል ማስቀመጥ እንደሚያስቸግር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ቁጥራቸው ወደ 60 ሺ እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መግለጹን ያነሱት አቶ ተስፋሁን ሁሉም ዜጎቻችን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ሱዳን ያሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ እንፈልጋለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ 

Via:- Alian
@Yenetube @Fikerassefa
11.2K viewsedited  16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 16:34:56
መልካም ገና ይሁንላችሁ - ዴሊቨሪ ሀዋሳ
ከተማችን ላይ ከሚገኙ ሁሉም ሬስቶራንቶች ጋር አብረን እንሰራለን በቤቶ ሆነው የሚያስፈልጎትን ይዙዙን።

ስልክ :- 0952626262 / 0462126282

#deliveryhawassa #Hawassa
4.1K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 16:31:44 የኦነግ አባላት፣ የተለያዩ የድርጅቱ መዋቅሮች እና አመራሮች በፓርቲው የተፈጠረው ችግር መፍቻ ሊሆን የሚችለውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ፡፡

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮች ክፍፍልን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተቋቋመበት አዋጅ 1133/2011 በምርጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች እና በስነምግባር አዋጅ 1162/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ እና ቁጥጥር የሚያደርግ ተቋም ነው። በዚህም መሰረት በኦነግ ፓርቲ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ህጋዊ እና ተደጋጋሚ ጥረቶችን ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህም መሰረት

1. የፓርቲው የተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ አባላት ነሃሴ 01 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ እና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር በተፈረመ ደብዳቤ የድርጅቱን ሊቀመንበር መታገዳቸውን ለቦርዱ አሳውቀው እንደነበር፣ ከዚህም በተጨማሪ የድርጅቱ አመራር ላይ ተከታታይ አቤቱታዎች አስገብተው እንደነበር ይታወሳል።

በሌላ በኩል የድርጅቱ ሊቀመንበር መስከረም 02 ቀን 2013 ዓ.ም ድርጅቱ ብሔራዊ ምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት እስከሚቀጥለው የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ ከሃላፊነታቸው ታግደው እንዲቆዩ እንደወሰነ ለቦርዱ አሳውቀዋል።

2. ፖለቲካ ፓርቲ አባላት መኻከል አለመግባባት ሲከሰት እና ለቦርዱ አቤቱታ ሲቀርብለት በአዋጅ ቁጥር 1162/11 አንቀፅ 74 ንዑስ አንቀፅ 6 መሠረት ጉዳዩን ተመልክቶ የውሣኔ ሃሣብ የሚያቀርብ የባለሙያዎች ጉባኤ ለማቋቋም በተሰጠው ስልጣን መሰረት በማድረግ የሁለቱንም ቡድኖች ደብዳቤዎች እና አቤቱታዎች እንዲሁም የውስጥ ህጎች የሚያይ የባለሞያዎች ኮሚቴ ለማቋቋም ውሳኔ አሳልፎ እንደነበርም ይታወሳል፡፡

በዚህም መሰረት በእነ አቶ አራርሶ በኩል ባለሞያ ቢመድቡም ፣ በእነ አቶ ዳውድ በኩል ባለሞያ ለመመደብ ፍቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ የፓርቲው የውስጥ ደንብ መሰረት መጠናቀቅ ያለበት ጉዳይ ነው በማለት መልስ በመስጠታቸው የባሞያዎች ጉባኤ ማቋቋም ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

3. በኦነግ አመራር መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የተደረገው የመጀመሪያው የቦርዱ ጥረት ባለመሳካቱ ጉዳዩን ከባለሞያዎች ጉባኤ ይልቅ በራሱ ሊያየው ተገድዷል። በዚህም መሰረት ከሁለቱም ወገን የገቡትን እገዳዎች በማየት እና የገቡ ሰነዶችን በመመርመር እንዲሁም ከሁለቱም ቡድን አመራሮች ጋር እንዲሁም ከስነስርአት እና ቁጥጥር ኮሚቴ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።
በውይይቱም ወቅት ፓርቲው አመራር ቀውስ ውስጥ እንደገባ፣ ለአባላቱ አመራር መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ፣ በተለይም ደግሞ ሁለቱም ቡድኖች ያቀረቧቸው እገዳዎች ህጋዊ እንዳልሆኑ ቦርዱ ወስኗል። በዚህም መሰረት የሁለቱም ወገን እገዳ የቀረበባቸው አባላት በነበራችው ህጋዊ ሃላፊነት ላይ እንደሚቆዩ ወሰነ።

በተጨማሪም ሁለቱም አካላት ህጋዊ ሂደቱ የተሟላ ሰነድ ባለማቅረባቸው፣ ፓርቲው ያለበት የአመራር ቀውስ ለመፍታት አለመቻላቸውን በመረዳት ቦርዱ የአመራር መከፋፈሉን ጠቅላላ ጉባኤ በማከናወን የፓርቲው አባላት መሪዎቻቸውን እንዲመርጡ ታህሳስ 08 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ከመወሰኑም በተጨማሪ የጠቅላላ ጉባኤውን ለማመቻቸት ሃላፊነቱንም እንደሚወስድ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

4. ከላይ በተጠቀሰው ውሳኔ መሰረት ለሁለቱም አመራር ቡድኖች ቦርዱ ውሳኔ በደብዳቤ ደርሷቸው የመጀመሪያውን ውይይት በቦርዱ አመቻችነት በጋራ ለማከናወን የመጀመሪያውን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ አባላት ጥሪ ቢደረግላቸውም በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አራርሶ የሚመራው የስራ አስፈጻሚ ቡድን ቦርዱ በጠራው ስብሰባ ላይ ሲገኝ በአቶ ዳውድ የሚመራው ቡድን ግን “ቦርዱ ይህንን የማመቻቸት ህጋዊ ሚና የለውም” በማለት በውይይቱ ላይ አልገኝም በማለታቸው በቦርዱ የተደረገው ጥረት አሁንም ሊሳካ አልቻለም።
5. ይህ ሂደት በዚህ ላይ እንዳለ ሁለቱም ወገኖች የተለያዩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ማመልከቻዎችን ለቦርዱ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።

6. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው የቦርድ አመራር አባላት ስብሰባ በኦነግ ስራ አስፈጻሚ መከፈልን አስመልክቶ እስከአሁን የተደረጉ ጥረቶችን እና ለመፍታት የወሰዳቸውን እርምጃዎች በዝርዝር መርምሯል። በዚህም መሰረት ቦርዱ እጁ ላይ ባሉት የህግ እና የአስተዳደር መሳሪያዎች በመጠቀም ሊያግዝ የሚችልበት ተጨማሪ አሰራር አለመኖሩን ተረድቷል።

7. በዚህም መሰረት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አባላት፣ የተለያዩ የድርጅቱ መዋቅሮች እና አመራሮች ለችግሩ መፍቻ ሊሆን የሚችለውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ቦርዱ ማሳሰብ እንደሚገባው ወስኗል። በመሆኑም ፓርቲው በመሃከሉ ያለውን አለመግባባት በስራ አስፈጻሚ አመራሮቹ ሊፈታ ባለመቻሉ የተለያዩ የድርጅቱ መዋቅሮች እና አባላት አውቀው ጠቅላላ ጉባኤ እነዲከናወን የሚያደርጉባቸውን ማንኛውንም መንገዶች እንዲጠቀሙ ቦርዱ በጥብቅ ያሳስባል።

Via:- FBC
@Yenetube @Fikerassefa
12.3K viewsedited  13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 16:18:07 ኮሮና ቫይረስ ወንዶች በተፍጥሮ የመውለድ አቀማቸውን ሊቀነስው እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታወቁ።

በቻይና ሃውዞንግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ ተማራማሪዎች አገኘን ባሉት ውጤት ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትላቸው የረዥም ጊዚያት የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዱ የወንዶችን የመውለድ አቅም የሚያዳክም መሆኑ ነው ያስታወቁት፡፡

እንደ ሳይንቲስቶ ከሆነ (called Angiotensin-converting enzyme 2) የተባለው ኢንዛይም በከፍፈተኛ ቁጥር በሳንባ፤ በአንጀቶች፤ በልብ፤ በኩላሊቶችና በወንዴ የዘር ማምረቻ አካላት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይሄውም በወንዶች የዘር ምርት እንዲመረት ይረዳል ብለዋል፡፡

ስለሆነም ቫይረሱ የዚህን ኢንዛይም ቁጥሩን እንደሚቀንሰው ደርሰንበታል ብለዋል እነዝ፡፡

ይሄውም በውንዶች የዘር ፍሬ ምርት ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተጽእኖ አለው ብለዋል ሳይንቲስቶቹ፡፡

ተመራማሪዎቹ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ምርምር የተደረገላቸው ወንዶች በመራቢያ አካላቸው ውስጥ የዘር ፍሬ ምርታቸው በቁጥር ሳይያዙ ከነበረው የቀነሰና እየቀነሰ እንደሚሄድም አመላክተዋል፡፡

ቁጥሩ ከመቀነሱም በተጨማሪ ያሉት የዘር ፍሬዎችም ቢሆኑ እንቅስቃሲያቸው የዘገየና በሴቶች ማህጸን ውስጥ ጽንስ ለመፍጠር የሚስችለውን እንቁላል የመስበር ጉልበቱ የተዳከመ ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በተለይይ በኮሮና ቫይርስ ተይዘው ላገገሙ ወንዶች፤ ልዩ ክትትልና ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል በማለት ያስጠነቀቁ ሲሆን፤ አሁን የተገኘው አመላክች ነገር ደግሞ በጉዳዩ ላይ እጅግ እንገብጋቢ የሆነ ጥናትና ምርምር እንዲደረግበት በር ከፋች መሆኑን ጥሪ አቅበዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
15.1K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 16:16:59 የጥር ወር ዋጋ ግሽበት ጭማሪ አሳየ፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበትመረጃ ሁኔታ በጥር ወር 2013 ዓ/ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ19.2 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በ1.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የጥር ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ23.1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በያዝነው ወር በአብዛኛው የእህል አይነቶቸ፣ አትክልትና አንዳንድ የጥራጥሬ ዓይነቶች የዋጋ ጭማሪ አስመዝግበዋል።

በሌላ በኩል ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም፣ ድንች እና ቡና ዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል ሲል የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አውርቷል።

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወርም ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የጥር ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጋር ሲነፃፀር የ14.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ አነቃቂዎች (ጫት)፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል) ፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ህክምና፣ ትራንስፖርት (ነዳጅ) እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል፡፡

Via:- Sheger
@Yenetube @Fikerassefa
11.4K views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 12:39:34
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በጎንደር ከተማ ያቋቋመውን የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከል ሥራ አስጀመረ።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ 347 አባላትና ከ140 በላይ አባል ያልሆኑ ተገበያዮች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክ የግብይት ማዕከላት በአዲስ አበባ፣ በሃዋሳ፣ በሑመራና በነቀምት ከ22 ሺህ በላይ ደንበኞች አሉት።

ዛሬ ደግሞ በጎንደር ከተማ ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከልን ወደ ሥራ አስገብቷል። ማዕከሉ ከ90 በላይ ተገበያዮችን በአንድ የግብይት መርሐ ግብር ማስተናገድ የሚችል ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ ነገራን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው ወደ ሥራ መግባቱ የተበሰረው።

የአካባቢው ተገበያዮች ወደ አዲስ አበባ መሔድ ሳይጠበቅባቸው በቀጥታ የግብይት ውድድሩ አካል እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ዘመናዊ አሰራር ነው። ይህም ከፍተኛ ወጭንና እንግልትን የሚቀንስ አሰራር ነው ተብሏል።

ምርት ገበያው የጥራጥሬና ቅባት እህሎችንና ቡና አቅራቢዎች ከሸማቾች ጋር በኤሌክትሮኒክ ሥርዓት በመደራደር የሚገበያዩበት ዘመናዊና ቀልጣፋ አሠራር መሆኑን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የንግድ ኦፕሬሽን ከፍተኛ ስፔሻሊስት አቶ ቸርነት ታመነ ለአብመድ ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
12.3K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-04 11:26:51 አልማ በዚህ አመት መጨረሻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርቼ አስረክባለው አለ።

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከተመሰረተ ጀምሮ የአባላቱን ቁጥር እየጨመረ የተለያዩ ስራዎችን እንደሰራ ይገለጻል።

በተለይም በትምህርት በጤና እና ስራ ፈጠራ ዘርፎች የሰራው ስራ ተጠቃሽ ነው።

የአማራ ልማት ማህበር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች 84 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና ደረጃቸውን ጥሩ ለማድረግ በዘንድሮው አመት ብቻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርተን እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የሚሰሩትም በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ሲሆን መማሪያ ክፍሎቹም ከመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እስከ መሰናዶ ላሉት አገልግሎት ይሰጣል ስለመባሉ ተሰምቷል።

የአማራ ልማት ማህበር በአሁኑ ሰአት 4.7 ሚሊየን አባላት እንዳሉት ገልጿል።

የአባላቱ ቁጥር ሲጨምርና የሀብት መጠኑ ሲያድግ በማህበራዊ ሀላፊነቶችም የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ በተሰራው ስራና በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
12.3K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ