Get Mystery Box with random crypto!

አልማ በዚህ አመት መጨረሻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርቼ አስረክባለው አለ። የአማራ ልማት ማህ | YeneTube

አልማ በዚህ አመት መጨረሻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርቼ አስረክባለው አለ።

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከተመሰረተ ጀምሮ የአባላቱን ቁጥር እየጨመረ የተለያዩ ስራዎችን እንደሰራ ይገለጻል።

በተለይም በትምህርት በጤና እና ስራ ፈጠራ ዘርፎች የሰራው ስራ ተጠቃሽ ነው።

የአማራ ልማት ማህበር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ሞገስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች 84 በመቶዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው ብለዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና ደረጃቸውን ጥሩ ለማድረግ በዘንድሮው አመት ብቻ 6 ሺህ የመማሪያ ክፍሎችን ሰርተን እናስረክባለን ሲሉ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የሚሰሩትም በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ሲሆን መማሪያ ክፍሎቹም ከመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እስከ መሰናዶ ላሉት አገልግሎት ይሰጣል ስለመባሉ ተሰምቷል።

የአማራ ልማት ማህበር በአሁኑ ሰአት 4.7 ሚሊየን አባላት እንዳሉት ገልጿል።

የአባላቱ ቁጥር ሲጨምርና የሀብት መጠኑ ሲያድግ በማህበራዊ ሀላፊነቶችም የእንቦጭ አረምን ለማስወገድ በተሰራው ስራና በጎርፍ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa