Get Mystery Box with random crypto!

የአውስትራሊያ መንግስት በኮቪድ የተያያዘ አንድ ግለሰብ ማግኘቱን ተከትሎ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች | YeneTube

የአውስትራሊያ መንግስት በኮቪድ የተያያዘ አንድ ግለሰብ ማግኘቱን ተከትሎ ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከቤታቸው እንዳይወጡ እገዳ መጣሉ ተሰምቷል ።

ባለፈው ሰኞ በምዕራባዊው አውስትራሊያ ፔርዝ ከተማ ሪፖርቱ ይፋ የተደረገ ሲሆን መንግስት ለ5 ቀን የሚቆይ ጥብቅ እገዳ ማስተላለፉን ሮይተርስ ዘግቧል ።

በቫይረሱ ከተያዘው ግለሰብ ጋር ቀረቤታ ነባራቸው የተባሉ 13 ሰዎችም በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።
አውስትራሊያ ኮቪድ 19 በመከላከል ውጤታማ ስራዎችን የሠራች አገር ስትሆን እስካሁን 29 ሺህ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ 909 ሰዎች ደግሞ ህይዎታቸውን አጥተዋል ።

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን ሁሉም ዜጎች ክትባት እንዲያገኙ እየሠራን ነው ብለዋል።

አሁን ላይ አውስትራሊያ 4.4 ቢሊዮን ዶላር በመመደብ 26 ሚሊየን ዜጎቿን ለመከተብ እየሠራች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን ተጨማሪ 1.9 ቢሊዬን ዶላር ያስፈልገናል እያሉ ይገኛሉ።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa