Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ ተዳርጓል! የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽ | YeneTube

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ ተዳርጓል!

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ሕገወጥ ተግባራትና በአመራር ዝርክርክነት ለ53 ቢሊየን ብር ኪሣራ መዳረጉ ተገለፀ። ኮርፖሬሽኑ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ኦዲት አለመደረጉም ተጠቆመ።በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት መምህርና በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዙሪያ ጥናት ያደረገው ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ቱሉ ቶላ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት፤ የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል።በዚህ ጊዜ ውስጥም ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።

ግንባታው ከፍተኛ የሀገሪቱ ሀብት የፈሰሰበት ቢሆንም በሕግና በሥራት የሚመራ አልነበረም የሚሉት ዶክተር ቶላ፤ በዚህ የተነሳ ለከፍተኛ የአሠራር ብልሹነትና የገንዘብ ዕዳ መዳረጉን አመልክተዋል።ቡድኑ ባደረገው የማጣራት ሂደት ለግለሰቦች የተላለፈበት መንገድ ያልታወቀ፣ መረጃ ያላቀረቡ፣ ዝግ የሆኑ፣ ባዶ ቤቶችና መሰል ችግሮች መለየታቸውን ጠቁመው፣ በከተማዋ ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት እጥረት እያለ ለ11 ዓመታት ዝግ ሆነው የቆዩ ቤቶች እንደነበሩም ጠቁመዋል። ከዚህም ባሻገር 21 ሺህ የሚሆኑ ቤቶች በማን እንደተያዙ ምን አይነት መረጃ ያልቀረበባቸው እንደነበሩም አስታውቀዋል።ቤቶቹ በዚህ መልኩ እንዲባክኑና ለሙስና እንዲዳረጉ የተደረገው ሆን ተብሎ ነው የሚሉት ዶክተር ቱሉ፣ ለዚህም ቤቶቹ መረጃ እንዳይኖራቸው ማድረግ አንዱ የሌብነት ስልት እንደነበረ ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት 85 ከመቶ የሚሆኑ ቤቶች ምንም አይነት የቤት መግለጫ የሌላቸው እንደሆኑ አመልክተዋል።በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከህብረተሰቡ የሚሰሙ ሮሮዎች የቆዩ መሆናቸውን የሚናገሩት ዶክተር ቱሉ፣ ሆኖም በዚህ ደረጃ ችግሩ ሥር የሰደደ ስለመሆኑ ግንዛቤ አልነበረንም።ጥናት በምናደርግበት ወቅትም ሀገሪቷ በምን አይነት ውስብስብ ችግር ውስጥ እንደነበረች ማየት ችለናል ብለዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa