Get Mystery Box with random crypto!

የጥር ወር ዋጋ ግሽበት ጭማሪ አሳየ፡፡ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ | YeneTube

የጥር ወር ዋጋ ግሽበት ጭማሪ አሳየ፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበትመረጃ ሁኔታ በጥር ወር 2013 ዓ/ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ19.2 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በ1.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የጥር ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ23.1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በያዝነው ወር በአብዛኛው የእህል አይነቶቸ፣ አትክልትና አንዳንድ የጥራጥሬ ዓይነቶች የዋጋ ጭማሪ አስመዝግበዋል።

በሌላ በኩል ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም፣ ድንች እና ቡና ዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል ሲል የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ አውርቷል።

ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወርም ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት የጥር ወር 2013 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጋር ሲነፃፀር የ14.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ከምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም በአልኮልና ትምባሆ፣ አነቃቂዎች (ጫት)፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል) ፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ህክምና፣ ትራንስፖርት (ነዳጅ) እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው ተብሏል፡፡

Via:- Sheger
@Yenetube @Fikerassefa