Get Mystery Box with random crypto!

ኮሮና ቫይረስ ወንዶች በተፍጥሮ የመውለድ አቀማቸውን ሊቀነስው እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታወቁ። | YeneTube

ኮሮና ቫይረስ ወንዶች በተፍጥሮ የመውለድ አቀማቸውን ሊቀነስው እንደሚችል ሳይንቲስቶች አስታወቁ።

በቻይና ሃውዞንግ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ ተማራማሪዎች አገኘን ባሉት ውጤት ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ከሚያስከትላቸው የረዥም ጊዚያት የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዱ የወንዶችን የመውለድ አቅም የሚያዳክም መሆኑ ነው ያስታወቁት፡፡

እንደ ሳይንቲስቶ ከሆነ (called Angiotensin-converting enzyme 2) የተባለው ኢንዛይም በከፍፈተኛ ቁጥር በሳንባ፤ በአንጀቶች፤ በልብ፤ በኩላሊቶችና በወንዴ የዘር ማምረቻ አካላት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይሄውም በወንዶች የዘር ምርት እንዲመረት ይረዳል ብለዋል፡፡

ስለሆነም ቫይረሱ የዚህን ኢንዛይም ቁጥሩን እንደሚቀንሰው ደርሰንበታል ብለዋል እነዝ፡፡

ይሄውም በውንዶች የዘር ፍሬ ምርት ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተጽእኖ አለው ብለዋል ሳይንቲስቶቹ፡፡

ተመራማሪዎቹ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ምርምር የተደረገላቸው ወንዶች በመራቢያ አካላቸው ውስጥ የዘር ፍሬ ምርታቸው በቁጥር ሳይያዙ ከነበረው የቀነሰና እየቀነሰ እንደሚሄድም አመላክተዋል፡፡

ቁጥሩ ከመቀነሱም በተጨማሪ ያሉት የዘር ፍሬዎችም ቢሆኑ እንቅስቃሲያቸው የዘገየና በሴቶች ማህጸን ውስጥ ጽንስ ለመፍጠር የሚስችለውን እንቁላል የመስበር ጉልበቱ የተዳከመ ነው ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በተለይይ በኮሮና ቫይርስ ተይዘው ላገገሙ ወንዶች፤ ልዩ ክትትልና ምርመራ ሊደረግላቸው ይገባል በማለት ያስጠነቀቁ ሲሆን፤ አሁን የተገኘው አመላክች ነገር ደግሞ በጉዳዩ ላይ እጅግ እንገብጋቢ የሆነ ጥናትና ምርምር እንዲደረግበት በር ከፋች መሆኑን ጥሪ አቅበዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa