Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 127.33K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 487

2021-02-07 20:24:21
የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ።

የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል።አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጠዉ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ርዳታ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉን ጥያቄ ለማሟላት ተስማምቷል።ቤስሌይ ትናንት በቲዊተር ባሰራጩት መግለጫ ትግራይ ዉስጥ 3 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ «የኛን ርዳታ እየጠበቀ ነዉ» ብለዋል።«የምናጠፋዉ ጊዜ የለም።» አከሉ ኃላፊዉ።

@YeneTube @FikerAssefa
17.2K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 20:22:15 የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያን በሰበብ-አስባቡ መጎነታተላቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።

የሱዳን ጦር ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ግዛት ይዟል መባሉ አወዛግቦ ሳያበቃ ሠሞኑን፣ የካርቱም ባለስልጣናት የሕዳሴዉ ግድብ የዉኃ አሞላልን የአዲስ ማስጠነቀቂያ ሰበብ አድርገዉታል።የሱዳኑ የመስኖና የዉኃ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድን በተናጥል ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ስጋት ትጭራለች።ሚንስትር ያሲር አባስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ሐምሌ ግድቡን ከሞላች ሱዳን ከሁለት ግድቦችዋ የምታመነጨዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ይታወካል፤ የ20 ሚሊዮን ሱዳናዉያን ኑሮም ይቃወሳል።ኢትዮጵያ ባለፈዉ ዓመት ክረምት ግድቡን መሙላት ጀመራለች።ግብፅና ሱዳን የኢትዮጵያን ርምጃ አልፈቀዱትም።ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት የዉኃ ሙሌቱ ይቀጥላል።ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የሱዳኑን ሚንስትር ጠቅሶ እንደዘገበዉ የ3ቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ፣የአዉሮጳ ሕብረት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና እንዲገቡ ካርቱም ሐሳብ አቅርባለች።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa
7.7K viewsedited  17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 19:18:42
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የምስጋናና የመፅሀፍ ምረቃ መርሀ ግብር ተከናወነ።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ የጥበብ ስራዎች ላይ ያሳረፈውን ደማቅ አሻራ ተከትሎ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል። በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዘፈኖቹ በርካታ መልክቶችን ሲያስተላልፍ የነበረ ጠንካራና ታታሪ ባለሙያ መሆኑንም የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። አክለውም አርቲስቱ ዘፈኖቹን በተለያዩ ብሄር ብሄረሰብ ቋንቋዎች በመጫወት በሀገሪቱ የጥበብ ስራ ውስጥ ያሥቀመጠው አሻራ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የተዘጋጀለት የምስጋና ፕሮግራም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa
17.5K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 17:32:13
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዝደንት አነጋገሩ!

ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ማህበራት ፌደሬሽን ፕሬዝደንት የሆኑትን ፍራንቼስኮ ሮካን ማነጋገራቸውን ከፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
10.1K viewsedited  14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 10:32:42
ከዛሬ ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደረገ፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከጥር 30 ቀን 2013 ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን አስታውቋል።በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች በሊትር ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ሆኗል፡-

-ቤንዚን 25 ብር ከ82 ሳንቲም

-ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 25 ብር ከ32 ሳንቲም

-ነጭ ናፍጣ 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ኬሮሲን 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ቀላል ጥቁር ናፍጣ 20 ብር ከ27 ሳንቲም

-ከባድ ጥቁር ናፍጣ 19 ብር ከ77 ሳንቲም

-የአውሮፕላን ነዳጅ 35 ከ12 ሳንቲም ሆኗል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች እንደየርቀታቸው መጠን ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መገለፁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
19.1K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 10:24:55
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መቐለ ገቡ!

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ መቐለ ከተማ ገብተዋል።ፕሬዝዳንቷ ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ተፈናቅለው በመቐለ ከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲሁም ሆስፒታሎች ይጎበኛሉ።በተመሳሳይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከመቐለ ያገር ሽማግሌዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
16.8K views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-07 10:22:57
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የቡሬ ኢንዱስትርያል ፓርክ ሥራው በመጀመሪያ ምእራፉ 260.5 ሔክታር መሬት ላይ አርፎ የውኃ፣ የመብራት እና ቴሌኮም መስመሮች እንዲሁም የመንገድ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎች እና የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ ቢሮዎችም ተገንብተውለታል።

በቀጣይ ሁለት ምእራፎች በማካተት እስከ አንድ ሺህ ሔክታር ይለማልም ተብሏል።በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገቡ ፋብሪካዎችም በዋናነት የግብርና ምርቶችን በግብዓትነት የሚጠቀሙ እና የሚያቀነባብሩ ፣ ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ እና ለግብርናው ዘርፍ መዘመን መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውም ተገልጿል።የግብርና ምርቶችን በፋብሪካ በማቀነባበርና እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እገዛው የጎላ መሆኑም በምረቃው ላይ ተገልጿል። የፓርኩ የመጀመሪያ ምእራፍ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ እስከ 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
11.9K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 20:45:03 በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አልፋሽጋ አል-ሱግራ በተባለው አወዛጋቢ አካባቢ የሁለቱ ሀገሮች ወታደሮች ሐሙስ’ለት እንደገና እንደተጋጩ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡ ግጭቱን ተከትሎ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ይዞታ ሥር የነበውን እና ልዩ ስሙ ኩምቦ መልካሙ የተባለ ቦታ አስለቅቄያለሁ ማለቱን ዘገባው ጠቅሷል፡፡ በግጭቱ አንድ የሱዳን ወታደር ሞቶ፣ ስምንቱ ቆስለዋል ተብሏል፡፡ በዘገባው ስለተጠቀሰው ግጭት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለው ነገር የለም፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
19.3K views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 19:32:28 ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ እንደሚነቅል ዛሬ ለፕሮጀክት ስንዲኬት በጻፉት መጣጥፍ ገልጠዋል፡፡ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሕወሃት ያወደማቸው የኮምንኬሽን መስመሮች ዕርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉለዋል፤ በዚህ ረገድ የዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
15.5K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-06 18:53:34
አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ አፍሪካ ማጓጓዝ ጀመረ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ አፍሪካ ማጓጓዝ መጀመሩን አስታወቀ፡፡አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ የመጀመሪያውን ክትባት ወደ አፍሪካ መጓጓዝ መጀመሩን ገልጿል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
15.0K viewsedited  15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ