Get Mystery Box with random crypto!

የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የምስጋናና የመፅሀፍ ምረቃ መርሀ ግብር ተከናወነ። አርቲስቱ በ | YeneTube

የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የምስጋናና የመፅሀፍ ምረቃ መርሀ ግብር ተከናወነ።

አርቲስቱ በኢትዮጵያ የጥበብ ስራዎች ላይ ያሳረፈውን ደማቅ አሻራ ተከትሎ የእውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቶለታል። በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ ጀኔራል ብርሀኑ ጁላ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የሙያ አጋሮቹ እንዲሁም በርካታ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዘፈኖቹ በርካታ መልክቶችን ሲያስተላልፍ የነበረ ጠንካራና ታታሪ ባለሙያ መሆኑንም የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። አክለውም አርቲስቱ ዘፈኖቹን በተለያዩ ብሄር ብሄረሰብ ቋንቋዎች በመጫወት በሀገሪቱ የጥበብ ስራ ውስጥ ያሥቀመጠው አሻራ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የተዘጋጀለት የምስጋና ፕሮግራም እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa