Get Mystery Box with random crypto!

ከዛሬ ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደረገ፡፡ የንግድ እና ኢንዱስትሪ | YeneTube

ከዛሬ ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ ተደረገ፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከጥር 30 ቀን 2013 ጀምሮ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ክለሳ መደረጉን አስታውቋል።በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች በሊትር ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ሆኗል፡-

-ቤንዚን 25 ብር ከ82 ሳንቲም

-ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚን 25 ብር ከ32 ሳንቲም

-ነጭ ናፍጣ 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ኬሮሲን 23 ብር ከ04 ሳንቲም

-ቀላል ጥቁር ናፍጣ 20 ብር ከ27 ሳንቲም

-ከባድ ጥቁር ናፍጣ 19 ብር ከ77 ሳንቲም

-የአውሮፕላን ነዳጅ 35 ከ12 ሳንቲም ሆኗል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳው ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ አካባቢዎች እንደየርቀታቸው መጠን ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መገለፁን ኢብኮ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa