Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕ | YeneTube

የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት ለተጎዳዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ለመሰጠት ተስማሙ።

የዓለም ምግብ ድርጅት የበላይ ዴቪድ ቤስሌይ የትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ከጎበኙ በኋላ ትናንት እንዳሉት ድርጅታቸዉ ሠብአዊ ርዳታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር «በተጨባጭ ርምጃዎች» ላይ ተስማምቷል።አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የቤስሌይን መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ዓለም አቀፉ ድርጅት የትራንስፖርት አገልግሎት የሌለባቸዉ አካባቢዎችን ጨምሮ ለችግር ለተጋለጠዉ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ርዳታ እንዲያደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበዉን ጥያቄ ለማሟላት ተስማምቷል።ቤስሌይ ትናንት በቲዊተር ባሰራጩት መግለጫ ትግራይ ዉስጥ 3 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ «የኛን ርዳታ እየጠበቀ ነዉ» ብለዋል።«የምናጠፋዉ ጊዜ የለም።» አከሉ ኃላፊዉ።

@YeneTube @FikerAssefa