Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የ | YeneTube

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ እንደሚነቅል ዛሬ ለፕሮጀክት ስንዲኬት በጻፉት መጣጥፍ ገልጠዋል፡፡ ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሕወሃት ያወደማቸው የኮምንኬሽን መስመሮች ዕርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉለዋል፤ በዚህ ረገድ የዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa