Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ። በምረቃ | YeneTube

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቡሬ የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

በምረቃ ስነ ስርአት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የፌደራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።አራት ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የቡሬ ኢንዱስትርያል ፓርክ ሥራው በመጀመሪያ ምእራፉ 260.5 ሔክታር መሬት ላይ አርፎ የውኃ፣ የመብራት እና ቴሌኮም መስመሮች እንዲሁም የመንገድ እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ተሟልተውለታል።ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎች እና የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ ቢሮዎችም ተገንብተውለታል።

በቀጣይ ሁለት ምእራፎች በማካተት እስከ አንድ ሺህ ሔክታር ይለማልም ተብሏል።በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገቡ ፋብሪካዎችም በዋናነት የግብርና ምርቶችን በግብዓትነት የሚጠቀሙ እና የሚያቀነባብሩ ፣ ምርታቸውን ወደ ውጭ የሚልኩ እና ለግብርናው ዘርፍ መዘመን መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውም ተገልጿል።የግብርና ምርቶችን በፋብሪካ በማቀነባበርና እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እገዛው የጎላ መሆኑም በምረቃው ላይ ተገልጿል። የፓርኩ የመጀመሪያ ምእራፍ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ እስከ 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርም ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa