Get Mystery Box with random crypto!

በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ በ30 ሄክታር መሬት የተገነባው ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በነ | YeneTube

በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ በ30 ሄክታር መሬት የተገነባው ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በነገው ዕለት ይመረቃል፡፡

ሰባት ከፋብሪካዎች የያዘ ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በቀን 1ሺህ 500 ቶን የምግብ ዘይት የሚያመርት ሲሆን፣ የሀገሪቱን 60 በመቶ የዘይት ፍላጎት የሚሸፍንና ለዘይት ይወጣ ከነበረው 30 በመቶ ወጪውን የሚያስቀር እንደሆነ ባለሃብቱና የቢኬጂ ቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ክንዴ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ፊቤላ እንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ከዘይት ፍብሪካው በተጨማሪ በቀን 200 ቶን ሰሊጥ ማቀነባበር የሚችል ፋብሪካ፣ በቀን 96 ቶን ሳሙና የሚያመርት ፋብሪካ፣ የአትክልትና ማርጋሪት ማምረቻ፣ የፕላስቲክና ጠርሙስ እንዲሁም የካርቶን ፍብሪካዎችን በውስጡ እንደሚያመርት ተናግረዋል።የዘይት ፍብሪካው ምርት የጥራት ደረጃው ተፈትሾ ለገበያ እንዲቀርብ ፍቃድ በማግኘቱ ከሰኞ ጀምሮ ለሸማቹ እንደሚደርስም ተገልጿል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa