Get Mystery Box with random crypto!

በሰላም ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከ | YeneTube

በሰላም ሚኒስትር የተመራ ልዑክ በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገባ!

በሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊ የተመራ የልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት መቐለ ገብቷል።

እንደ ኢዘአ ዘገባ የልዑክ ቡድኑ አባላት በትግራይ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በመቐለ እና በአካባቢው እንዲሁም በኩሃ ያለውን የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት ሁኔታን ተዘዋውረው ይጎበኛሉ።

በተጨማሪም በትግራይ ክልል እየተሰጠ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa