Get Mystery Box with random crypto!

Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ abiyahmedaliofficial — Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @abiyahmedaliofficial
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.85K
የሰርጥ መግለጫ

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን!
Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf!
Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-07-03 12:45:43
ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር በቱሪዝም ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት እና የሀገራችንን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ለመጠቀም በትብብር ለመሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውይይት አድርገናል።

Productive discussions with Marriott International President and CEO Anthony Capuano focused on Ethiopia’s aspirations in the tourism sector and ways and means of collaborating to maximize our nation's potential.
15.7K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 20:13:32
ከጥንት ጀምሮ የባህል መድሀኒት እውቀት ያላት ሀገራችን ዛሬም በመድሀኒት ምርት ከራሷ አልፋ ለሌሎች መትረፍ ትችላለች ።
24.0K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 15:49:52
“የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ”
28.7K viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-22 13:21:04
የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዐቶችንና እና መድኃኒቶችን ለማምረት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ጀምሮ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል:: ከ120 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ላላት ኢትዮጵያ መድኃኒቶችን በራስ ዐቅም ማምረት ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም።

Considerable attention has been directed towards the sector, beginning with policy reforms aimed at the domestic production of medical supplies and medicines. For Ethiopia, with a population exceeding 120 million, producing its own medicines is an urgent priority.
24.9K views10:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-21 22:04:03
በአረንጓዴ ዓሻራ ጥረቶቻችን አማካኝነት ልናሳካው ለምንፈልገው ለውጥ የአመለካከት እና የአዕምሮ ውቅር ሽግግር ያስፈልገናል። እንደ ሀገር ልናሳካ ካለምነው 50 ቢሊዮን ችግኞች በያዝነው አመት 40 ቢሊዮን ችግኞች ላይ ለመድረስ እየጣርን በመሆኑ በዘንድሮው የተከላ ዙር 7.5 ቢሊዮን ችግኞችን በጋራ መትከል ይኖርብናል። ለነገው ትውልድ ቅርስ ለመተው የሚሻ ሁሉ ዛሬ ላይ ማዋጣት የግድ ይለዋል።

A paradigm and mindset shift is needed for the change we want to see in our Green Legacy endeavors. Our goal for this year is to reach 40 billion seedlings from our overall target of 50 billion, which means we need to collectively plant 7.5 billion seedlings this planting cycle. For anyone who wants to leave a legacy for future generations, we must invest in the future today.
28.7K views19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-15 14:02:58
እንኳን ለ2016 የዒድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የኢድ አል አድሃ በዓል የፈተናና የመሥዋዕትነት በዓል ነው፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም በአላህ ትእዛዝ ልጃቸውን ለመሥዋዕትነት ያዘጋጁበት፤ ጽናታቸው ተፈትኖ ያሸነፉበት በዓል ነው፡፡ ለዚህ ጽናታቸውም ከአላህ ዘንድ ምትክ በግ ያገኙበት በዓል ነው፡፡
ከዚህ በዓል የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ማንኛውም ፈተና በጽናት ካለፉት ዋጋው ከፈተናው በላይ መሆኑን እንማርበታለን፡፡ ልጅን ያህል ነገር እንዲሠዉ መጠየቅ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ልጅን ለመሥዋዕትነት ማዘጋጀት ደግሞ ከባድ ጽናት ነው፡፡ ከባድ ፈተና ከባድ ቆራጥነት ይፈልጋል፡፡ ከባድ ቆራጥነት ከባድ ውሳኔን ይጠይቃል፤ ከባድ ውሳኔም ታላቅ ዋጋን ያስገኛል፡፡
ኢትዮጵያን ታላቅና የበለጸገች ሀገር ለማድረግ ስንነሣ ፈተናው ከባድ እንደሚሆን እናምን ነበር፡፡ ሳይፈቱ የተከማቹ ሀገራዊ ችግሮች አሉ፡፡ በዘመናችን የተፈጠሩ አሁናዊ ችግሮችም አሉ፡፡ እነዚህ ሁለቱን በአንድ ጊዜ መጋፈጥ ይጠይቀን ነበር፡፡ ተራራውን መጋፈጥ ሳይሆን ተራራውን ማንሣት ይጠይቀን ነበር፡፡ ይሄንን ፈተና ለመጋፈጥ ከባባድ ውሳኔዎችን መወሰን ይገባን ነበር፡፡ እንደ ልጅ የምንወዳቸውን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ቡድኖች፣ ወዳጆችና አካሄዶች ለመሠዋት መወሰን ነበረብን፡፡ መወሰን ብቻ ሳይሆን ማድረግም ነበረብን፡፡
ነቢዩ ኢብራሂም ልጃቸው ኢስማኤልን ሳይሆን በምትኩ ከአላህ የተሰጣቸውን በግ ሠዉተዋል፡፡ የእኛ ፈተና ከዚህም የባሰ ነበር፡፡ ሀገራችን ባከማቸቻቸው ዕዳዎችና ስብራቶች የተነሣ፣ ያለን አማራጭ የራሳችንን ነገር መሠዋት ብቻ ነበር፡፡ ሀገራችንን ለማዳን፣ የሕዝባችንን ዘላቂ ጥቅሞች ለማስከበር እና ከዛሬው የተሻለ ነገን ለመፍጠር ስንል፣ ብዙ ነገሮችን ሠዉተናል፡፡
ችግሮቻችን ቀስ ብለን እንድንሄድ አይፈቅዱልንም፡፡ በጥንቃቄ እንድንሮጥ እንጂ፡፡ የልማት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ እንደ ሕዝብ ሁላችንም የምንወዳቸውን ነገሮች ሠዉተናል፡፡ ከምንወደው አካባቢ ወደ ሌላ ሄደናል፡፡ ትዝታዎቻችንን ሠዉተናል፡፡ የባንዳውን ጩኸት ችለናል፤ ሀገርን ለመለወጥ ስንል ቤቶቻችንና ሕንጻዎቻችን እንዲፈርሱ ፈቅደናል፡፡ የመብራትና የውኃ መጥፋትን ታገሠናል፤ የመንገድ መዘጋትንና የአካባቢ መፈራረስን ተቀብለናል፡፡ ያለ መሥዋዕትነት የሚያድግ ሕዝብ፣ ያለ መሥዋዕትነት የሚበለጽግ ሀገር የለም፡፡ የኮሪደር ልማቱን በዚህ መልኩ በመሥዋዕትነት ነው የሠራነው፡፡ ፍሬው ግን እጅግ ጣፋጭ መሆኑን አይተናል፡፡
ሰላማችንን ለማስፈን በዚሁ መንገድ ነው መቀጠል ያለብን፡፡ ነፍጥን መጣል፤ ከጫካ መውጣትና የራስን ዋሻ ትቶ ወደ መስኩ መውጣትን ይፈልጋል፡፡ የራስን ኢጎ መሠዋትን ይጠይቃል፡፡ ምቾትንና ፍላጎትን መተዉን ይፈልጋል፡፡ ከመቀበል በላይ መስጠትን ይሻል፡፡ እንደ ኢብራሂም በጣም የምንሳሳለትን ነገር ለመሠዋት መቁረጥ ይፈልጋል፡፡ ሁላችንም ለመሥዋዕትነት ከተዘጋጀን የማይሳካ የሰላም መንገድ የለም፡፡ እንደ ልጅ ያሳደግናቸው ብዙ ልማዶች፣ ጠባዮች፣ አመለካከቶች፣ ርእዮተ ዓለሞችና አካሄዶች አሉን፡፡ እነርሱን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ስንል ለመሠዋት ዝግጁ ከሆንን፣ ውጤቱ ከሰላም በላይ ነው፡፡
ምክክር የሚሳካው የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት በማዋጣት ብቻ አይደለም፡፡ የተሻለ ሐሳብና የላቀ ዕውቀት ስላለን ብቻ የሠመረ ውጤት አናገኝም፡፡ ሌላ ወሳኝ ነገር ይፈልጋል፡፡ እርሱም መሥዋዕትነት ነው፡፡ የራስን ፍላጎት ለመሠዋት መቻል አለብን፡፡ ለትልቅ ግብ ሲባል ይቅርብኝ ማለት አለብን፡፡ ከእኔ የተሻለ ሐሳብና ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ ሊኖር ይችላል ብለን ማመንና መቀበል አለብን፡፡ ለተሻለው ሐሳብ መገዛት አለብን፡፡ ልክ ልኩን ከመንገር፤ ነጥብ ከማስቆጠር፤ ጀግና ጀግና ከመጨዋት የወጣ ትኁት ሰብእና መያዝ አለብን፡፡ ይሄ ሁሉ መሥዋዕትነትን ይጠይቃል፡፡ እንደ ነቢዩ ኢብራሂም ያሳደግናቸውን ብቻ ሳይሆን አብረውን ያደጉትን ብዙ ጠባዮች ለመሠዋት መዘጋጀትን ይጠይቃል፡፡ መሥዋዕትነት የሚከፍሉ ዜጎች በበዙ ቁጥር፣ ምክክር የላቀ ውጤት ያስገኛል፡፡
የኮሪደር ልማታችን በየከተሞቻችን እንዲስፋፋ፤ ሰላማችን የጸና እና የማይደፈርስ እንዲሆን፤ ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ተካሂዶ እንዲሳካ - ያሳደግናቸውንና ያደጉብንን አንዳንድ ነገሮች መሥዋዕት ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ ሐሳቦቻችን ትጥቅ ይፍቱ፡፡ ከመተኮሻ ወደ ማረሻ እንመለስ፡፡ ከጠመንጃ ወደ ማጨጃ እንዛወር፡፡ ከዲሞትፈር ወደ ምክክር እንምጣ፡፡ ከብሔር ግጭት ወደ ሐሳብ ፍጭት እንሻገር፡፡ የምንወደውን፣ የምንፈልገውንና ያሳደግነውን እንኳን ቢሆን - ለሀገር ስንል ለመሠዋት እንዘጋጅ፡፡
መልካም በዓል ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ስኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
17.4K views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 11:47:50
ዛሬ ጠዋት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሃሙድ አሊ ዩሱፍ መልዕክት ከፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጉሌ ይዘው መጥተዋል በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። እንዲህ ያሉት ግንኙነቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ለንግግር እና ትብብር አውታር በመሆን የጋራ መግባባትን ያሳድጋሉ።

I welcomed this morning Mahamoud Ali Youssouf, the Foreign Minister of Djibouti, to my office this morning. Minister Youssouf came bearing a message from President Ismail Omar Guelleh. Such exchanges serve as vital channels for dialogue and cooperation, fostering mutual understanding and collaboration on bilateral and regional matters of shared interest.
8.1K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ