Get Mystery Box with random crypto!

አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharainfocenter — አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharainfocenter — አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)
የሰርጥ አድራሻ: @amharainfocenter
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

Amhara Info Center(AIC) አማራ መረጃ ማዕከል ወቅታዊ መረጃ ማቅረብ ቀዳሚ አላማው ነው ።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 19:42:01 ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ከ “ኢንሳ” ዳይሬክተርነታቸው ተነሱ

ካለፈው ህዳር ወር 2014 ጀምሮ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ሰለሞን ሶካ፤ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

አቶ ሰለሞን የመሪነት ቦታውን የተረከቡት “ኢንሳ”ን ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ የመሩትን ዶ/ር ሹመቴ ግዛውን በመተካት ነው።

አቶ ሰለሞን ሶካ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሆነ መሾማቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቢያረጋግጡም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

ከማይክሮ ሊንክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በሶፍት ዌር ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ ሰለሞን፤ በ“ኢንሳ” ከሶፍት ዌር መሐንዲስነት እስከ ቡድን መሪነት ባሉት ቦታዎች አገልግለዋል።

አዲሱ ተሿሚ በኮምፒውተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከቻይና ኤሌክትሮኒክ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነው።

አቶ ሰለሞን ከዘጠኝ ወር በፊት የምክትል ዳይሬክተርነት የኃላፊነት ቦታ ተሰጥቷቸው ወደ “ኢንሳ” ከመመለሳቸው በፊት፤ “ቴክ ማሂንድራ” በተባለ የህንድ የመረጃ ቴክኖሎጂ አገልግሎት እና አማካሪ ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ሆነው ለአምስት ዓመታት ሰርተዋል።

ኃላፊነታቸውን ለአቶ ሰለሞን ያስረከቡት ዶ/ር ሹመቴ ግዛው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ከጥር 2012 ጀምሮ ለሁለት ዓመት ከመንፈቅ ገደማ በዋና ዳይሬክተርነት መርተውታል።

ዶ/ር ሹመቴ ወደ ኢንሳ ከመምጣታቸው በፊት ለስምንት ወራት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። ዶ/ር ሹመቴ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትም ነበሩ።
102 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:04:02 በደቡብ አፍሪካ ባለው “መጤ ጠል” ጥቃት ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው መዘረፉ ተነገረ

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትጵያውያን ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገረት በሀገሪቱ በሚስተዋሉ መጤ ጠል እንቅስቃሴዎች ምክንያት የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተሰብረው ንብረቶታቸው ተዘርፈዋል።

ኢትዮጵያውያኑ፡ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ለመጣው መጤ ጠል እንቅስቃሴ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ቅስቀሳ ዋነኛ አጀንዳናቸው በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑ እንደሆነም ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ለአል ዐይን አስታውቀዋል።
145 views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:02:03 ከምዕራብ ጎንደር ዞን የፀጥታ ምክር ቤትና የሰላም አማካሪ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ!

በዞኑ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለያየ መንገድ ተደናግረው ራሳቸውን የደበቁና ከህግ የራቁ ማንኛውም አካላት በዞን ፣ ወረዳ ፣ ቀበሌ የሰላም አማካሪ ምክር ቤት (የሠላም ካውንስል) አማካኝነት እንዲገቡ የተጠናከረ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

በመሆኑም በዞናችን በሁሉም ወረዳና ቀበሌዎች ከ78 በላይ የሚደርሱ ከህግ የራቁና የተደናገሩ አካላት ወደ ሰላም መንገድ የተቀላቀሉ ሲሆን አሁንም የፌደራልና የክልል መንግስት በተለያየ ምክንያት ከህግ የራቁና የተደናገሩ አካላት ለመጨረሻ ጊዜ በመንግስት በኩል ይቅርታ ተደርጎላቸው እስከ ነሀሴ 1/2014 ዓ/ም ድረስ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል።

በመሆኑም የዞኑና የወረዳ የፀጥታ መዋቅርና የሰላም አማካሪ ካውንስል አማካኝነት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሳይቀመጥ ማንኛውም ከህግ የራቀና የተደናገረ ሁሉ ሙሉ ትጥቁን ለመንግስት አስረክቦ እንዲገባና በግል የበደሉትን ታርቀው የወሰዱትን መልሠው ይቅርታው በመቀበል በየአካባቢያችሁ የወረዳ አስተዳደር አካላት እና የሰላም ካውንስል አማካኝነት በመግባት ወደ ሰላማዊ ኑሮ አንድትመለሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን ነው!
150 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:57:36 ቻይና ዶንግፋንግ የተሰኙ ሚሳኤሎችን ወደ ታይዋን ተኮሰች

ዶንግ ፋንግ የተሰኘው የቻይና የረጅም እና አጭር ርቀት ባልስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ታይዋን ባህር የትተኮሱ ሲሆን እስካሁን የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል።

ቻይና በታይዋን ባህር ዙሪያ እስከ ቀጣዩ እሁድ ድረስ የሚቆይ ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ ላይ ትገኛለች ።

የጦርነት ልምምዱ በታይዋን 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስድስት አቅጣጫ እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል።
126 views10:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:04:46 በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የመገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄን በዛሬው ዕለት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል።

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክፍሌ ዋና ሰሞኑን በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያቀረቡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በኹለት ክልል ለመደራጀት ያቀረቡትን ጥያቄ ሰነድ ለፌደሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አስረክበዋል።

የሚደራጁት ክልሎች የህዝቦችን አንድነት እንዲሁም የጋራ እሴቶችን በሚያጎላ እና መልኩ ሊሆን እንደሚገባ በምክርቤቶቻቸው የጋራ አቋም መያዛቸውን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረትወላይታ፣ጋሞ፣ጎፋ፣ኮንሶ፣ደቡብ ኦሞ፣ጌዴኦ ዞኖች፣እንዲሁም ደራሼ፣ባስኬቶ፣ኸሌ፣አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በክልል እንደራጃለን በማለት በየምክር ቤቶቻቸው በማጽደቅ መወሰናቸውን ምክትል አፈ ጉባኤው ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስልጤ ፣ከምባታ ጠምባሮ፣ሀዲያ ፣ሀላባ፣የም ልዩ ወረዳ በአንድ ላይ በመሆን ክልል ለመመስረት በምክር ቤቶቻቸው በማጽደቅ የጋራ አቋም መያዛቸውንም ጠቁመዋል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ በሚወስነው ውሳኔ መሰረት ክልል ለመሆን መወሰናቸውን መግለጻቸውን የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

የፌደሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት፤ ኹሉም ምክር ቤቶች ያስተላለፉት ውሳኔ የህዝቦችን ውክልና ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም መሰረት 10 ዞንኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች በኹለት ክልል ለመደራጀት ያቀረቡትን ጥያቄ ምክር ቤቱ መቀበሉን አረጋግጠዋል።

በመርሐ ግብሩ ከ10 ዞኖችና ከ6 ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች መገኘታቸውም ታውቋል።
189 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 18:02:34 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አብን በድጋሚ የሚያካሂደውን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ውሳኔ አሣለፈ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ እና መጋቢት ዘጠኝ እና ዐሥር 2014 ዓ.ም. የተካሄደውን የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ቦርዱ ሚያዝያ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ከሪፖርቱ ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉና ከመተዳደሪያ ደንቡ አንጻር መርምሮ ያሣለፈው ውሣኔ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. በቁጥር አ1162/11/586 በተጻፈ ደብዳቤ ለፓርቲው ገልጿል፡፡

ፓርቲው ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በቁጥር አብን392/02/14 በተጻፈ ደብዳቤ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ሥራዎች መከናወናቸውን፣ ከነዚህ መካከል የሕገ ደንብ ማሻሻያ እንደሚገኝበት ገልጾ በቦርዱ በተሰጠው አስተያየት መሠረት ማሻሻያዎች የተደረገበት ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ በጉባዔ ከመፅደቁ በፊት አያይዞ አቅርቧል፡፡

ቦርዱ ሐምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ፓርቲው ያቀረበውን ሠነድ ከሕጉ ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንጻር መርምሯል።

ፓርቲው ባቀረበው የተሻሻለ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ላይ ማስተካከያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮች፡-

1. በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 11.1.25 ማዕከላዊ ምክር ቤቱ በምዕራፍ ሁለት ከአንቀጽ ዘጠኝ- አንቀጽ 22 የተዘረዘሩትን ተግባራት እስከ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባዔ ድረስ ማሻሻል እንደሚችል ደንግጓል፡፡ ይሁንና ከእነዚሁ 14 አንቀጾች መካከል፤

በአንቀጽ 10.1 ሥር ንዑስ አንቀጽ 10.1.1 የጠቅላላ ጉባዔ የሥራ ዘመንና ፣ በንዑስ አንቀጽ 10.1.3 የጠቅላላ ጉባዔ አባላት ብዛትን የሚመለከቱት፤

በአንቀጽ 10.2 የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን ስብጥር የሚመለከተው፣

በአንቀጽ 10.3 የጠቅላላ ጉባዔውን ሥልጣንና ተግባር የሚመለከተው፣

በአንቀጽ 11.1.1 የማዕከላዊ ኮሚቴውን ተጠሪነትና አባላት ብዛትን የሚመለከተው፤

አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 12.1.1 የብሔራዊ የኦዲትና የሕገ ደንብ ተርጓሚ ኮሚቴን ተጠሪነትና ብዛት ፣ አንቀጽ 12.1.2 በሥሩ የሚያዋቅራቸውን የሕገ ደንብ ተርጓሚ ኮሚቴዎች እና 12.2.3 የራሱን የሥራ ክፍፍል መመሪያ ስለማውጣት በሚመለከቱትን፣

አንቀጽ 12.2 ከንዑስ አንቀጽ 12.2.1 - 12.2.5 የብሔራዊ የኦዲትና የሕገ ደንብ ተርጓሚ ኮሚቴን ተግባርና ኃላፊነት የሚመለከቱት ላይ በማዕከላዊ ኮሚቴው ማሻሻያ ማድረጉ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ጋር የሚቃረን በመሆኑ ከላይ በዝርዝር የተገለጹት ንዑስ አንቀጾች ለማዕከላዊ ኮሚቴ የሚሰጡ ሥልጣኖች አይሆኑም። ስለዚህ ከዚህ በላይ የተገለጹትን በማውጣት በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 11.1.25 ላይ ማስተካከያ እንዲደደረግበት፣

2. በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 24.1 ማዕከላዊ ምክር ቤቱ ዕጩ አባላትን የጠቅላላ ጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ መልምሎ እንደሚያቀርብ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የሚጠቆሙት ዕጩዎች ብዛት እና በምን መሥፈርት ዕጩዎቹ እንደሚመለመሉ መቅረብ ያለበት በመሆኑ አስፈላጊው ማሻሻያ እንዲደረግበት፣

3. በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 25 መሠረት የጠቅላላ ጉባዔ አዘጋጅ ኮሚቴው የኦዲትና ሕገ ደንብ ተርጓሚ ኮሚሽንን መልምሎ እንደሚያቀርብ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የሚጠቆሙት ዕጩዎች ብዛት እና በምን መሥፈርት ዕጩዎቹ እንደሚመለመሉ መቅረብ ያለበት በመሆኑ አስፈላጊው ማሻሻያ እንዲደረግበት፣

4. በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 15.1.5 ሥራቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሥራ አስፈጻሚው አቅራቢነት ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ቀርቦ ኮሚቴው አጣርቶ አስተዳደራዊ ውሣኔ እንደሚያሳልፍ የሚያስቀምጥ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ አንቀጽ 34.1 በሥራ አስፈጻሚ ላይ የሚቀርብ ክስ በማዕከላዊ ምክር ቤት በሚቋቋም የብሔራዊ ዲሲፒሊን ኮሚቴ እንደሚታይ ይደነግጋል፡፡ ይህም እርስ በራሱ የሚቃረን እና በሥራ አስፈጻሚ ላይ የሚቀርብ ክስ በየትኛው አካል እንደሆነ ግልጽ ባለመሆኑ አስፈላጊው ማሻሻያ እንዲደረግበት።

ጠቅላላ ጉባዔውን በተመለከተ

1ኛ/ ፓርቲው እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርግ በቦርዱ መወሠኑ ይታወቃል። ይሁንና ፓርቲው በቦርዱ ውሣኔ መሠረት ጉባዔውን ሳያካሂድ የተሰጠው ጊዜ ገደብ አልፏል፡፡ በመሆኑም ጠቅላላ ጉባዔውን መቼ ለማድረግ እንደወሠነ ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ፣

2ኛ/ ጠቅላላ ጉባዔው እንዲነጋገርበት የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አስቀድሞ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ፣

3ኛ/ የፓርቲው የጠቅላላ ጉባዔ አባላት የሚጠሩበትን ሁኔታ በተመለከተ በፓርቲው የተሰጡ የፓርቲው ውሣኔዎችን እንዲያቀርብ እና እስካሁን ያለውን ክዋኔያቸውን እንዲያብራራ፣

4ኛ/ በተጨማሪም ሌሎች የጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ጉባዔ ዝግጅቶችን ለቦርዱ እንዲገልጽ ቦርዱ የወሠነ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም.
169 views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 17:52:41
የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ያሰለጠናቸው ኮማንዶዎች!!!
171 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:07:32
218 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:04:00
218 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 18:01:57 9ኛ. መንግስት ከትሕነግ ጋር የጀመረው ድርድርም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ከፓርቲ ፖለቲካ እና ከአንድ አንባገነናዊ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት እና ሁሉን ነገር ከመቆጣጠር አባዜ ተላቆ ህዝብ ያመነባቸው ፣ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ፣ እውቀቱ እና ቁርጠኝነቱ ባለቸው የህዝብን ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም በሚያስጠብቁ እውነተኛ ወኪሎች እንዲመራ እንፈልጋለን። በዚህ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በፌደራል መንግስቱ በኩል የተወከሉ ተደራዳሪዎች የአማራን ጥቅም ሊያስጠብቁ የማይችሉና ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የአማራን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ በመሆኑ ህዝባዊ አመኔታ የሚጣልባቸው ባለመሆኑ በምትካቸው በቀጥታ አማራን ሊወክሉ የሚችሉ ከአማራ ምሁራን ፣ ከህግ ባለሞያዎች ፣ ከታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወጣጡ እውነተኛ ወኪሎች እንዲወከሉ እንጠይቃለን ፤ በድርድር ስም አንድ ስንዝር የአማራ መሬት ለማንም አሳልፎ መስጠት እንደማይቻል አበክረን ማስገንዝብ እንወዳለን ።

10ኛ. አማራ የገጠመውን የህልውና አደጋ መቀልበስና አንደ ህዝብ መቀጠል የሚችለው እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ ለአማራዊ እንድነት መቆም ሲቻል ነው ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል አማራው ብቻ እየሞተላት የምትድን አገር ስለማትኖርና ዛሬ በአማራው ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ለሌሎችም ህዝቦች ሊዳረስ የሚችል የጋራ አደጋ መሆኑን በመገንዘብ መላው ኢትዮጵያዊ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በስሙ በመጥራት "የአማራን የዘር ፍጅት" እንዲያወግዝና ከአማራ ጎን ቆሞ የትግሉ አካል እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

አንድነት ኃይል ነው !!!
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ !!!
ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም
219 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ