Get Mystery Box with random crypto!

ከምዕራብ ጎንደር ዞን የፀጥታ ምክር ቤትና የሰላም አማካሪ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ! በዞኑ | አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)

ከምዕራብ ጎንደር ዞን የፀጥታ ምክር ቤትና የሰላም አማካሪ ካውንስል የተሰጠ መግለጫ!

በዞኑ ውስጥ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለያየ መንገድ ተደናግረው ራሳቸውን የደበቁና ከህግ የራቁ ማንኛውም አካላት በዞን ፣ ወረዳ ፣ ቀበሌ የሰላም አማካሪ ምክር ቤት (የሠላም ካውንስል) አማካኝነት እንዲገቡ የተጠናከረ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

በመሆኑም በዞናችን በሁሉም ወረዳና ቀበሌዎች ከ78 በላይ የሚደርሱ ከህግ የራቁና የተደናገሩ አካላት ወደ ሰላም መንገድ የተቀላቀሉ ሲሆን አሁንም የፌደራልና የክልል መንግስት በተለያየ ምክንያት ከህግ የራቁና የተደናገሩ አካላት ለመጨረሻ ጊዜ በመንግስት በኩል ይቅርታ ተደርጎላቸው እስከ ነሀሴ 1/2014 ዓ/ም ድረስ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል።

በመሆኑም የዞኑና የወረዳ የፀጥታ መዋቅርና የሰላም አማካሪ ካውንስል አማካኝነት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሳይቀመጥ ማንኛውም ከህግ የራቀና የተደናገረ ሁሉ ሙሉ ትጥቁን ለመንግስት አስረክቦ እንዲገባና በግል የበደሉትን ታርቀው የወሰዱትን መልሠው ይቅርታው በመቀበል በየአካባቢያችሁ የወረዳ አስተዳደር አካላት እና የሰላም ካውንስል አማካኝነት በመግባት ወደ ሰላማዊ ኑሮ አንድትመለሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን ነው!