Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ አፍሪካ ባለው “መጤ ጠል” ጥቃት ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው መዘረፉ ተነገረ በደቡብ አፍሪ | አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)

በደቡብ አፍሪካ ባለው “መጤ ጠል” ጥቃት ኢትዮጵያውያን ንብረታቸው መዘረፉ ተነገረ

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትጵያውያን ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገረት በሀገሪቱ በሚስተዋሉ መጤ ጠል እንቅስቃሴዎች ምክንያት የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሱቆች ተሰብረው ንብረቶታቸው ተዘርፈዋል።

ኢትዮጵያውያኑ፡ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየተስፋፋ ለመጣው መጤ ጠል እንቅስቃሴ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያደርጉት ቅስቀሳ ዋነኛ አጀንዳናቸው በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጣረ መሆኑ እንደሆነም ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና በጉዳዩ ላይ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ለአል ዐይን አስታውቀዋል።