Get Mystery Box with random crypto!

አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharainfocenter — አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharainfocenter — አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)
የሰርጥ አድራሻ: @amharainfocenter
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.18K
የሰርጥ መግለጫ

Amhara Info Center(AIC) አማራ መረጃ ማዕከል ወቅታዊ መረጃ ማቅረብ ቀዳሚ አላማው ነው ።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-03 18:01:38 ከአማራ ህብረት ሙኒክ/ ባቫሪያ/ጀርመን የተሰጠ የአቋም መግለጫ
*

የአማራን ህልውና መታደግ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መታደግ ነው!

ለአገር ህልውና ዋጋ የከፈለ ፣ ከሌሎች ህዝቦች ጋር ተሰባጥሮ የሚኖር ፣ በሌሎች ህዝቦች ጥቃት የሚታመም ፣ የትልልቅ እሴቶች ባለቤት የሆነው የአማራ ህዝብ ዛሬ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበት ፣ ወንጀሉ በህግ የማያስጠይቅ፣ ሞቱ እውቅና የማይሰጥበት፣ ሃዘኑንም ሞቱንም መግለጽ የማይችልበት ፣ አልፎ ተርፎ እንወክለዋለን የሚሉ ፖለቲከኞች በሞቱ የሚሳለቁበትና የሚያዋርዱት ግዜ ላይ ደርሷል ። "በመንግስት መዋቅር ድጋፍ የሚደረግ ግድያና ጭፍጨፋን እንደ ቁማር ጨዋታ የቆጠሩ ፖለቲከኞች ፣ በዜግነት እንኑር ስትላቸው ኢትዮጵያ በብሄር ብሄረሰቦች ነው የተሰራችው ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለመደፍጠጥ ነው እንዲህ የምትለው ይሉሃል ። ሞተህ ግን ፣ በማንነት የተገደለው አማራ ነው ስትል ዜጎች ናቸው የሞቱት ብለው ይሳለቁብሃል።" በዚህ መንገድ አማራው ማህበራዊ እረፍት እንዳያገኝና ለከፋ ድህነት እንዲጋለጥ እየተደረገ ስለሆነ ፣ እንደ ማህበረሰብ የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ፣ በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ዘግናኝ የዘር ፍጅት ፣ (Genocide) የዘር ማጽዳት (Ethnic cleansing) ወንጀልና ማንነትን መሰረት ያደረገ ዘርፈ ብዙ የመብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ለማድረግ ፣ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ድምጽ ለመሆን ፣ ስጋት ላለባቸው ወገኖቻችን ልሳን ለመሆን ፣ ከሞት ለተረፉ ሰለባዎች እርዳታ ለማድረግና የህልውና ትግሉን ለማገዝ እንዲሁም ከሌሎች መሰል የአማራ ማህበራት ጋር በመቀናጀት እገዛ ለማድረግ፣ እኛ በሙኒክና አካባቢው ( ባቫሪያ -ጀርመን) የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያዊ አማራዎች፣ ይህንን የአማራ ህብረት በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ ሐምሌ 30.2022 (እ.አ.አ) መስርተናል ። በዚህ የምስረታ ጉባዔያችን ዕለት መስራች አባላት ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ በሰፊው በመወያየት የሚከተለውን የአቋም መግለጫም አስተላልፏል ።

1ኛ. ከ30 ዓመት በላይ ያስቆጠረው በመላው ኢትዮጵያ በአማራ ላይ ሲፈፀም የኖረውንና አሁንም የቀጠለውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ተግባር መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ወንጀሉን በስሙ በመጥራት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ጭፍጨፋውን ፈጻሚና አስፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቁርቡ እንጠይቃለን። ብሄራዊ የሀዘን ቀን ታውጆ በመላው ኢትዮጵያ ህዝቡ ሀዘኑን በይፋ እንዲገልጽ ፣ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብና ወንጀሉ በተፈጸመባቸው ቦታዎች የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሚዲያ ባለሞያዎች ፣ እንዲሁም የሰባዊ መብት ተቋማት በተገኙበት ፣ በየቦታው ወዳድቀው የቀሩ ከአውሬ የተረፉ አጽሞች ተሰብስበው በክብር እንዲያርፉና የጅምላ መቃብር ቦታዎች ተለይተው እና ታውቀው፣ መታሰቢያ ሃውልት እንዲቆምላቸው እንጠይቃለን።

2ኛ. ለረዥም ግዜ ከአማራው ፊቱን አዙሮ የነበረው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የአማራው ሰቆቃ እንዳሳሰበውና የዘር ፍጅቱ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር መጠየቅ መጀመሩን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች አስተውለናል ። ቢዘገይም ጅማሮውን እያደነቅን መሬት ላይ የወረደ ስራ ያልተጀመረ በመሆኑ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመሰጠት የዘር ማጥፋቱ አድማስ ከመስፋቱ በፊት ለማስቆም ያላሰለስ ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

3ኛ. በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ ለተፈጸመው የዘር ፍጅት የኦሮሚያ፣የቢኒሻንጉል ክልሎች እና የፌደራል መንግስቱ ሀላፊነት በመውሰድ ለተጎጂ ቤተሰቦች ከሳ ፣ ለተፈናቃዮች የህግ ከለላ እና የስነልቦና ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ በአስቸኳይ የመልሶ ማቋቋም ስራ ተስርቶ እንዲመለሱ እንዲደረግና ይህን መሰል ችግር ዳግም እንዳይከሰት መዋቅራዊ ማስተካከያ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

4ኛ. አማራ ጠል የሆነው ህገ መንግሥትና እሱን መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ህዝብ አጫራሽ የሆነው የጎሳ ፌደራሊዝም ተወግዶ ህዝብ የተወያየበትና ያመነበት ህገመንግስት እና አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲመሰረት እንጠይቃለን።

5ኛ. አማራ ከሚባለው ክልል ውጭ የሚገኘው የአማራ ተወላጅ ፍታዊና አካታች የሆነ ሕገ መንግሥት እስከሚኖር ድረስ ባለው ህገ መንግሥት መሰረት የፖለቲካ ውክልና ኖሮት መብቱን ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያስከብርብት እኩል መደላድል እንዲፈጥር ፤ የፌደራሉም ሆነ የክልል መንግሥታት ተቀዳሚ ተግባራቸው ሰላምና ጸጥታ ማስፈን በመሆኑ ዜጎች የፈለጉበት ቦታ የመስራትና የመኖር መብታቸው እንዲጠበቅ የመድረግ ኃላፊነትና ጊዴታ አለባቸው ።

6ኛ. የትግራይ ወራሪ ሀይል በፈጸመው ወረራ የወደሙ ከተሞች፣መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ በበቂ ሁኔታ እየተሰራ እንዳልሆነ እንረዳለን ። የፌደራል መንግስቱ ከለጋሽ ሃገሮችና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ክልሉ ከደረሰበት የኢኮኖሚ ድቀት እንዲያገግምና አፋጣኝ የመልሶ ግንባታ ስራ እንዲሰራ እንጠይቃለን።

7ኛ. ፋኖነት ለአማራ ህዝብ ደምና አጥንት የተገበረለት የአባቶቻችን ዉርስ፣ ዛሬም ያለ ወደፊትም ከአማራ ህዝብ ጋር ህያው ሆኖ የሚኖር ስሪታችን ነው ።
መንግስት "በህግ ማስከበር " ስም ለአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ የሆነውንና በህልውና ዘመቻው ግንባር ድረስ በመዝመት ሀገርን ከመፍረስ የታደገውን የፋኖ አባላትንና አመራሮችን ያለምንም የፍርድቤት ማዘዣ በወታደራዊ ካምፖችና በስውር ቦታዎች በጅምላ እያሰሩ ይገኛል ። መንግስት ባመነው እንኳን ከ5000 በላይ የአማራ ተወላጆችን አስሮ እንደሚገኝ ጥምር ግብረሃይል ብሎ ያሰማራው ሀይል በኩል አሳውቋል ። ይህ የጅምላ እስር የህልውና አደጋ የተጋረጠበትን አማራ የበለጠ የጥቃት ተጋላጭ ለማድረግ እና በህልውና ዘመቻው በአዋጅ ራሱን እንዲከላከል ተፈቅዶለት ማርኮ በእጁ ያስገባውን ለማስፈታት የተጀመረው ዘመቻ እጅግ አደገኛና ውጤቱ የከፋ እንደሚሆን እያስጠነቀቅን፣ በዚህ አጋጣሚ የፋኖ ትግል አማራን ብሎም ኢትዮጵያን የመከላከልና የነጻነት ተጋድሎ በመሆኑ በዚሁ ድጋፋችን እንደማይለየው ማረጋገጥ እንወዳለን ።

8ኛ. አዲስ አበባ ራሷን የቻለች በቻርተር የምትተዳደር የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ መሆኗን በህገ መንግስቱ ቢደነገግም ከዚህ በተጻራሪ የኦሮሚያን ህገ-መንግስት አዲስ አበባ ላይ ለመተግበርና የኦሮሚያን ከፋፋይ የክልል መዝሙር ነፍስ ባላወቁ ህጻናት ላይ በኃይል ለመጫን ፣የአንድን ክልል ባንዲራ በተለየ መልኩ አዲስ አበባ ውስጥ እንዲሰቀል ማድረግ ፍጽም የለየለት ህገ-ወጥነትና ሌሎችን ብሄርብሄረሰቦች መናቅና ህገመንግስቱንም መናድ በመሆኑ ይህን በፌደራልና በኦሮሚያ መንግስት የተጀመረውን አዲስ አበባን የመስልቀጥና ጥንታዊቷን ኢትዮጵያን በማፈራረስ ኦሮሙማን የመመስረት ህገ ወጥ ተግባር በጽኑ እያወገዝን መላው ኡትዮጵያዊም ይህን ተግባር እንዲቃወም ጥሪያችንን እናስተላፋለን። የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ ባጠራቀመው ገንዘብ የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችች ከህግ ወጪ እንዲተላለፉ ፣ የመሬት ወረራ እንዲስፋፋ እና ህገወጥ ዘረፋ እንዲካሄድ ያደረጉት ካንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ያለመከሰስ መብታቸው ተንስቶ ጉዳያቸው በህግ እንዲታይ እንጠይቃለን።
206 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:49:21 ኢትዮጵያና ኤርትራ ከአፍሪካ ሀገራት መካከል የከፋ የጋዜጠኞች እስር የሚገኝባቸው ሀገራት መሆናቸውን ሲፒጄ ገለጸ

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ጦርነት ላይ የትርክት የበላይነት ለመያዝ የሚደረገው ፉክክር ጋዜጠኞችን ለጥቃት እንዳጋለጠ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሲፒጄ ያደረገው ጥናት ያመለክታል።

መንግስት ሕግ ማስከበር እያለ ሲጠራው ከነበረውና በውሸት፣ በሀሰተኛ መረጃና በማህበራዊ ሚዲያ የጦርነት ትርክት ከታጀበው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተለየ ሀሳብ ያራመዱ ወይንም ገለልተኛ ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞች ለእስር፣ ለዛቻና መሰል ጥቃቶች ተጋላጭ መሆናቸውም ተጠቅሷል።

እንዲሁም አንዳንዴ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በተፋላሚ ሀይሎች ንጹሀን ዜጎች ላይ ከሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጅምላ እስር ጋር ተዳብሎ እንደሚፈጸም ተነግሯል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ ቢያንስ 63 ጋዜጠኞችና የሚዲያ ሰራተኞች መታሰራቸውን ሲፒጄ ዘግቧል።

ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ ስምንቱ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ።

በአብዛኞቹ እስረኞች ላይ የሚፈጸመው የመብት ጥሰት ተመሳሳይ አካሄዶችን እንደሚከተል ያስረዳው የሲፒጄ ዘገባ ጋዜጠኞች ወይም የሚዲያ ሰራተኞች ከተያዙና ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኃላ ለምርመራ በሚል ተደጋጋሚ የፍርድ ቤት ቀጠሮ መጠየቅ አንዱ የመብት ጥሰት አካል እንደሆነ ገልጿል።

ሆኖም በሲፒጄ ከተመዘገቡት እስሮች መካከል በጣም ጥቂቶቹ ላይ ብቻ መደበኛ ክስ እንደተመሰረተ የሲፒጄ ዘገባ ያመለክታል።

ምንም እንኳን ፍርድ ቤቶች ለጋዜጠኞች የዋስትና መብት ቢሰጡም ፖሊሶች የጋዜጠኞቹን መፈታት የሚያዘገዩ ይግባኞችን በተደጋጋሚ መጠየቅና አንዳንድ ጋዜጠኞች ከቤተሰብም ሆነ ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ሳይገናኙ በእስር እንዲቆዩ ማድረግ የመብት ጥሰቱ ሌላው አካል ነው ተብሏል።

ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኞች ላይ ደግሞ የእንቅስቃሴ ገደብና የባንክ ሂሳባቸው ላይ እግድ እንደተጣለባቸው ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኞች ለሲፒጄ ተናግረዋል።

አለማቀፍ ጋዜጠኞችን ከሀገር ማባረር፣ ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ላይ ደግሞ አካላዊ ጥቃትና ግድያን መፈጸምም በጋዜጠኞች ላይ ከደረሱት የመብት ጥሰቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

በመሆኑም ሲፒጄ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም፣ በጉዳያቸው ላይ ግልጽና ተአማኝነት ያለው ምርመራ እንዲደረግና አጥፊዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል።

በተጨማሪም የቴሌኮም አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የቴሌኮም አገልግሎት እንዲጀመርና ጋዜጠኞች ከጦርነቱ ጋር የተያያዙትን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የህዝቡን ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን እንዲዘግቡ የሚያስችላቸው መረጃ የማግኘት መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል።
185 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:46:41 የብልፅግና ባለስልጣናት በእስራኤል እየሩሳሌም ባረፉበት ሆቴል በአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው። የሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሞፈሪያት ካሚል እንዲሁም አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ጨምሮ ሌሎች 14 የብልፅግና ባለሰልጣናት የእስራኤልን መንግስት ደጅ ሊጠኑ ቢገኙም የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ያረፉበትን ሆቴል ትክክለኛ መረጃ በማጣራት ሆቴሉ በር ላይ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል::
ይህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቀደም ሲል የደረሳቸው ባለስልጣናት ሻንጣቸውን
ጥለው ከሆቴሉ መሰወራቸውን ምንጮቻችን አክለው ገልፀውልናል::
ከስፍራው አክሎ በደረሰን መረጃ የብልፅግና ባለስልጣናት ለአንድ ሳምንት
ያህል በሀገሪቱ እንደሚቆዩና ቆራጥ የአማራ ልጆችም ብልፅግና አማራውን
እረፍት ነስቶ እያሳደደ መግደሉን እስካላቆመ ድረስ ባለስልጣናቱም እረፍት
እንደማያገኙና በሄዱበት ሁሉ ተሳደው ለፍርድ እስኪቀርቡ ትግላቸው ተጠናክሮ
እንደሚቀጥል ገልፀውልናል::

ንሥር ብሮድካስት ከእስራኤል
186 views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ