Get Mystery Box with random crypto!

9ኛ. መንግስት ከትሕነግ ጋር የጀመረው ድርድርም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለ | አማራ መረጃ ማዕከል (Amhara Information Center)

9ኛ. መንግስት ከትሕነግ ጋር የጀመረው ድርድርም ሆነ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ከፓርቲ ፖለቲካ እና ከአንድ አንባገነናዊ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት እና ሁሉን ነገር ከመቆጣጠር አባዜ ተላቆ ህዝብ ያመነባቸው ፣ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ፣ እውቀቱ እና ቁርጠኝነቱ ባለቸው የህዝብን ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም በሚያስጠብቁ እውነተኛ ወኪሎች እንዲመራ እንፈልጋለን። በዚህ መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በፌደራል መንግስቱ በኩል የተወከሉ ተደራዳሪዎች የአማራን ጥቅም ሊያስጠብቁ የማይችሉና ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ የአማራን ጥቅም አሳልፈው የሰጡ በመሆኑ ህዝባዊ አመኔታ የሚጣልባቸው ባለመሆኑ በምትካቸው በቀጥታ አማራን ሊወክሉ የሚችሉ ከአማራ ምሁራን ፣ ከህግ ባለሞያዎች ፣ ከታሪክ ተመራማሪዎች ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተወጣጡ እውነተኛ ወኪሎች እንዲወከሉ እንጠይቃለን ፤ በድርድር ስም አንድ ስንዝር የአማራ መሬት ለማንም አሳልፎ መስጠት እንደማይቻል አበክረን ማስገንዝብ እንወዳለን ።

10ኛ. አማራ የገጠመውን የህልውና አደጋ መቀልበስና አንደ ህዝብ መቀጠል የሚችለው እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ ለአማራዊ እንድነት መቆም ሲቻል ነው ብለን እናምናለን። በሌላ በኩል አማራው ብቻ እየሞተላት የምትድን አገር ስለማትኖርና ዛሬ በአማራው ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ለሌሎችም ህዝቦች ሊዳረስ የሚችል የጋራ አደጋ መሆኑን በመገንዘብ መላው ኢትዮጵያዊ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በስሙ በመጥራት "የአማራን የዘር ፍጅት" እንዲያወግዝና ከአማራ ጎን ቆሞ የትግሉ አካል እንዲሆን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

አንድነት ኃይል ነው !!!
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ !!!
ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም