Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊ | YeneTube

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከሦስት ቀናት በፊት የተነሳው እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል።

ሚያዚያ 10፣ 2016 ዓ.ም. በስፍራው የተነሳው እሳት በቁጥጥር ሥር አለማዋሉን የክልሉ ባለሥልጣን ገለጹ።የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አባይ መንግሥቴ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እሳቱ ከተነሳበት ቀን ጀምሮ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና አመራሮች ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

“የቦታው አቀማመጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ጠፋ ሲባል እንደገና እየተነሳ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም” ብለዋል።ሆኖም እሳቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይስፋፋ የአሰሳ እና የጥበቃ ሥራ እየተሠራ ነው ያሉት ኃላፊው፣ እሳቱ ከቁጥጥር ውጪ አለመውጣቱን ተናግረዋል።

በፓርኩ የእሳት አደጋ ሲከሰት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም።
ከአምስት ዓመታት በፊት በፓርኩ ከፍተኛ እሳት ተነስቶ ከክልሉ እና ከፌደራል አቅም በላይ ሆኖ የእስራኤል እና የኬንያ እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተርን ድጋፍ እስከ መጠየቅ ተደርሶ ነበር።

@YeneTube @FikerAssefa