Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክ | YeneTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ገለጸ፡፡አየር መንገዱ ለተፈጠረው መጉላላትም ደንበኞቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰው በረራውን የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል፡፡ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰውም በጥሪ ማዕከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም በፌስቡክ ገጹ ጠቅሷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa