Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ኤርትራ ወታደሮቿን ከትግራይ በአስቸኳይ ታስወጣ›› በሚል የወጣውን የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ አ | YeneTube

‹‹ኤርትራ ወታደሮቿን ከትግራይ በአስቸኳይ ታስወጣ›› በሚል የወጣውን የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ አስመራ አግባብነት የሌለው ስትል ውድቅ አደረገች፡፡

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል በቲውተር ገፃቸው ባሰፈሩት አጭር ምላሽ በኤርትራ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ያወጣውን መግለጫ ሀሰተኛና ተንሳፋፊ ወይም ማስረጃ ያልቀረበበት ክስ ብለውታል፡፡በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን በቲውተር ገፃቸው ያሰፈሩት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ‹‹የተወሰኑ አገራት መንግሥት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ ሳይሰጥ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ሲጠይቁ እየተመለከትን ነው›› ብለዋል፡፡‹‹ግን ለምን ወረራ የፈፀመውና የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር የያዘውን የሱዳን ኃይል እንዲወጣ ጥያቄ አያቀርቡም?›› ሲሉም አገራቱን ተችዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ አርብ ባወጣችው መግለጫ ‹‹በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋ ይታወሳል፡፡‹‹ወታደሮቹ የሰብኣዊ መብት ጥሰትንም እየፈፀሙ ነው›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋን በኤርትራ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ማሳወቁም አይዘነጋም።የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ግን በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች ተሳትፎ አለ የሚለውን ሪፖርት አይቀበሉትም።

አሐዱ
@YeneTube @FikerAssefa