Get Mystery Box with random crypto!

ወግ ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ wegoch — ወግ ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ wegoch — ወግ ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @wegoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.12K
የሰርጥ መግለጫ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch
✔ @zefenbicha
Creator @lula_al_greeko

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2021-09-06 20:11:35 የተለየ ፍቅር አለ. በቃ ልዩ!... ይህ ፍቅር ሚመጣው ተስፋ ቆርጠህ ባለፈው ፍቅርህ ተደቁሰህ ሁለተኛ ላለመደቆስ ወስነህ ጥግህን ከያዝክ ቦሀላ ነው. መጀመርያ ቦታ አትሰጠውም ቀልድ ታደርገዋለህ ምክንያቱም ከጨዋታው ራስህን አግልለሀላ! ሲቀጥል እስቲ ልየው ብለህ በሶምሶማ የኧሯሯጥ ስልት ታስቀጥለዋለህ... መሀል ላይ የትላንት ቁ ስልህ ትዝ ይልህና ሶምሶማውን ወደ እርምጃ ትቀይረዋለህ. ውስጥህ ግን ይረበሻል.. እኔ ላይ ሆኖ የነበረውን እዚ ሰው ላይ እንደገምኩት ይሆንን? ብለህ... ከዛ ግን ህሊናህን አፍነህ ገድለህ ትረጋጋለህ. ያሰው ግን ሳይቀየር አንድ ቀለም ሆኖ ይቀጥላል. ወጣ ብለህ ትርዒቱን ስታይ እስስቱ ራስህ ሆነህ ታገኘዋለህ. ያሰው አሁንም ላንተ ደስታ ደፋ ቀና ይላል. እያስመሰለ ይሆንን? ደፍሬ ብገባ እጋጋጥ ይሆን? ወይስ ይህ ሰው የተሻለ ነው? እድል ልስጠው ይሆን እንዴ? ብለህ ብዙ ታወራርዳለህ? የዶ/ር እዮብ "የፍቅር ህይወት" ከሚለው መፅሀፍ ላይ ባገኘኸው መለኪያ ሁሉ ትለካዋለህ ከዛ ይመዝንብሀል.... "አይ ይሄ ነገር ይቅርብኝ" ብለህ ለደመነፍስህ እንዲወስን መሪውን ታቀብለዋለህ. ... ሁሉንም መንገድ መዝጋት ትጀምረህ... ትረሳዋልህ ሁላ... ማስተካከል የማይስማማው ጠማማ ትሆናለህ... ከብረት የጠነከረ ልብ ይኖርሀል... ያሰው ይጎዳል ስንት ለሊት ስንት ቀን ያነባል... በስተመጨረሻ "እያለቀስኩማ አልኖርም!" ብሎ የመንገዱን አቅጣጫ ይቀይራል. ድሮ ሲያደርግ የነበረውን ተቃራኒ እያቃረውም ቢሆን ያደርጋል.... ይሄኔ ነው ብረቱ ልብህ ወደ ቄጤማነት ሚለወጠው.... እሱ ያሳለፋት እያንዳንዷ ነገር በአስር ተባዝታ ትሰማሀለች.. የድሮ ህግህን ብትጠቀምም አይሰራልህ...... ተሸንፈሀላ! የድሮ ቁስልህ እንደገና ለመቁሰል ሙሉበሙሉ ይስማማል! ህመምህን ትወደዋለህ! በእብርክክህ እየዳኽክ የገፋኸውን ሰው ትፈልገዋለህ.... ልክ እንደ 'ህል ውሀ. አማራጭ የለህም ሄደህ ትናዘዛለህ! አበቃ! ያም ሰው አይጨክንም. "ለመቅረብ መራቅ!" ሚለን ህግ ተጠቅሞ ኖሮ ያንተን መመለስ ነበር ሚጠብቀማው ፈገግታውን እፊቱ ላይ ፍቅሩን እልቡ ላይ እንደእንጀራ አስፍቶ ይጠብቅሀል. አሁንማ ማን ይቻላቹ! አንድ ላይ ተበርራላቹ.....

ልዩ ፍቅር አለ ያላሰብከው ግዜ የሚመጣ... ህይወትህን ከስር መሰረቱ ጀምሮ በማር ሚለውስ ... ያለፈው ህይወቴ እንዴት እሬት ነበር ብልህ እንድትገረም የሚያደርግህ.... ግን ሳታስበው ሳትዘጋጅ እንዲው ስሜትህ ውርድ ባለበት ሰአት ይከሰትና ዋጋ ያስከፍልሀል.

#በMaggie
@getem
@getem
@paappii
5.8K viewsDAVE / PAPI, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 22:13:46 እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ልቧን : ይመራዋል : እንጅ ልቧ : አይኗን : እንደሚከተለው : አታውቅም.....
ግንኮ : አይን : ያየውን : ለልብ : ካልነገረው : ልብም : አድምጦ : ካላመነበት : አይንን : ይከተለዋልን?

መቼም አንዴ ለጉዞ ፈጥሮኛልና መንገድም : እወድ የለ .....
በጉም : ላይ : እየተረማመድኩ : ሳለ ብቻዬን : አግዜሩን : አግኝቸው : ነበር : በምናባዊ : ፀዳል እንደምናስበው : አደለም : ኮስማና ነው።

እናተ : ሰዎች: ለምን : ትጠሉኛላችሁ : ስለምንስ ከክብሬ : ቁልቁል : አፈረጣችሁኝ : ማቅለላችሁ : ሳይቀር : ለሌሎች : መሳለቂያ : አረጋችሁኝ ፥ ከዙፋኔ እያለሁ : እንደሌለሁ : አበሸቀጣችሁኝ ለምን? ስለምንስ? ተጠራጣሪ : ሆናችሁ : በኔ ለምን? እንባ እንቅ እንባ እንቅ ,,,,,
እያረገው : ሶስት : የእንባ : ዘለላ :ከገፁ ፥ ሲረግፍ እየሁ።

እንባው ፥ ወደስቅለቱ : ትዝታ : እያላጋ : ወሰደን በስቅለቴ : ግዜ አንድ : ደንባራ : ወታደር : በጦር ጎኔን ሲወጋኝ : ህመሙን : አታውቅም : ይሁዳ : በከንፈሮቹ ሀሞት : ተጎንጭቶ : ጉንጨ : ላይ : ሲተፋብኝ : የተሰማኝን : አታውቅም : ጴጥሮስ : ሶስት : ግዜ : አንድ ለአብ አንድ ለወልድ አንድ ለመንፈስቅዱስ ለያንዳንዳችን : በአንድነት : የክህደትን : ኮሶ : ሲያግተን : ምሬቱን : አታውቅም።

40 ቀን 40 ለሊት ስፆም ሰይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈትነኝ የፈጠርኩትን መልሶ የኔ ሊያረጋቸው ሲደራደረኝ ቤተ መቅደሴን ሲሻቀጡበት እናቴን ከቁሻሻ መሀል ትቢያ እንደተደፋ ልቅላቂ ሲጠየፏት አታውቅም።

አዎ አታውቅም ........ እናት ሰዎች ህመሙን አታውቁም .........

የእግዜር እንባ ግን ምን አይነት ነው?

እኔም: ሆድ : ብሶኝ : የልቤን : ዘረገፍኩለት :ጌትዬ : በሁለት : አለም : ሰካር : ውስጥ: አየዳገርኩ: ለምን ዝም አልከኝ? አንተኮ: ብትታመምም : አምላክ ነህ የአምላክነትህ : ባህርይ ረቂቅ : ነው ያስችልሀል::

ግን ለምን ፈጠርከኝ? ማጥ: ረመጥ : ውስጥ : ከተትከኝ? እውነት አውጣኝ : ብዬ : ስለምንህ: ሳትሰማኝ : ቀርተህ ነው?
የህይወትስ ጣዕሙ በምን ይለካል ? በድን : አካልን አሸክመኸኝ : ለአመመታት : መክረሜን ዘንግተኸው ነውን?

እኔ : የነካሁት : ሁሉ : ርኩሰትን : እንዲላበስ : ሁሌ እንድሸሸግ : የምታረገኝ : ራሴን : በራሴው እንደ እፉኝን : ስውጥ አላሳዝንህምን?

የእናትህስ : ህመም : አንተን : ብቻ : የሚቆረቁርህ ይመስልሀል?
እሷኮ : አምጣ : አልወለደችህም : ደም : አልፈሰሳትም
ምነው_ቸሩ _መድሀኔ_አለም : የኔዋ : እናት: ወዝ ወዘናዋን : አጠንፍፋ : ባማጠች : የህመሟን ሲቃ ባስረቀረቀች : አኔን : ወልዳ : እንኳ_ማርያም : ማረችሽ ቢሏት : አንተው : የማርካት መሰለህ? በድኩም : አካሏ : ተንፏቃ : አፈር : ልሳ : ብትለምንህ : መች ምሬሻለው : አልካትና? የማርያም ልጅ...!!

አንተ : ብትፆም :ባህሪህ : ቅዱስ : ነህና : ይፈቅድልሀል እኛስ :አንጀታችን :ሲታለብ :ቆርቆሮ :ቤታችን :ውስጥ : በችጋር : ስንለበለብ :ዞር ብለህ : አይተኸናል : እንዴ?
ቅፅበታዊ : ደስታን : አሳይተህ : ዛላቂያዊ : ህመምን ከልባችን : የቸነከርከው : እውነት : ከሳዶርና ፣ አላዶር የሚተናነሱ : ይመስልሃልን?

ተው : እንጅ : ቤዛ ከሉ መድሀኔ አለም..... ተው እንጅ የማርያም ልጅ!!

ተስፋዬን : በምኞት : ደግፌ : ብጓዝ :ባንተ : አይደል የጨነገፈው : ማያዬ :መመልከቻ : አድማሴን : ባገኛት
ባንተም : አይደል : ያጣኃት? እንደኩታ : አይሽሞንሙነህ : ያለበስከኝ : ይህን :ማንነት አንተም አደል : የፈጠርከው ? ይኸው : እሷም /ወደመሸሹ አጋደለች....
እስቲ : ልወቀው : ጥፋቴን :ለምን : ግራ አርገህ ፈጠርከኝ?
ምን ትለኝ ይሆን? ምንስ ምላሽ ይኖርህ?

ግን ለምን አትወስደኝም? ኖሬ : የህይወት : ጣዕሙንስ በምን :ምላሴ : ላጣጥመው? ምላሴን : ቆርጠህብኝ ......ሳላጣጥመው : ኮመጠጠኝ።

ተፈጥሮ : ፊቱን : አጨፍግጎብኝ : ሳለ : ከነፍሴ የተጣባች : እንስትን : ወዳንተ : ልካኝ : ነበር። አንተ የምድርና ፣ የሰማይ : ጌታ : ሆይ : ቸኮሌት : ላክልኝ ብልሀለች።

ከጥሪው : መዝብ : ሳሟ :ሳይሰፍር : ወደኔ መታ የነበረችው : ማያዬን አወካት?

ለነገሩ : አንተ : ብታቅም : አላቅም :ከማለት : ወደኃላ አትልም...... ብቻ እሷ ታቅሀለች።

በቃና : ዘገሊላ :ግዜ : ውሀውን : ወይን : ጠጅ : አድገህ : ነበር : በሰው : ሰርግ : እንደዚ : የሆክ : በራህ : ሰርግ : እንዴት: ትሆን?
በስቅለትህ : ወቅት : ጎንህን : ሲወጉህ : ውሀ፣ ደም፣ ወተት : ፈሶህ ነበር ።

በመጀመሪያ :ቀን : ማያዬን : ሳገኛት : ውሀ ጠጥታ ነበር ።
በሁለተኛው : ቀን : ስንገናኝ : በተፈጥሮ : ደም እየፈሰሳት :ነበረ ።
በሶስተኛ : ቀን : ፈጣሪ : ቸኮሌት : በኔ : በኩል እንዲልክላት : ጠይቃኝ ነበር።

በቸኮሌት: ውስጥ : ወተቱን : ለማግኘት :ፈልጋለው ይሆናላ....


ቸኮሌቷን : አንድቀን : ይዤላት: እንምመጣ :ታውቅ ይሆን?

አታውመቅም.........

የእግዚአብሄርን : ልጅ : ሰርግ : አይቼ : ከድግሱ : በልቼ ጠጥቼ : መሞቴን : እንኳን : አታውቅም..........


አዎ አታውቅመም.....

አደራ
**ንገሩልኝ******

ሱራፌል ጌትነት (ሱራ ቢራቢሮ)

የግማሽ አለም ጣኦት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
6.0K viewsDAVE / PAPI, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-27 20:54:57 ‹‹እንዴት ነው ግን ከዚያስ በኋላ አንድ ሰው እንኳን ወይም የከተማው አስተዳደር ራሱ በግድም ቢሆን ወስዶ የወሊድ መቆጣጠሪያ የማያስደርግላት…! አሁንስ ቢሆን ምንድን ነው ዋስትናዋ በድጋሜ እንደማይደፍሯት?›› ብዬ ፈርጠም ብዬ ጠይቄ ነበር፡፡ አሁንም ያቺ ደግ አክስቴ ያደረገችውን ነገረችኝ፡፡ ‹‹አይ በልዬ… እሱማ ከዚያ በኋላ እንደምንም ብዬ ይሄ ክንድ ላይ የሚቀበረውን የ4 ዓመት የወሊድ መከላከያ አስደርጌላት ነበር፡፡ የሆነ ቀን ራሷ ቆፍራ አወጣችውና ጣለችው፡፡ ይኸው ይግረምህና… አሁንም ነፍጠ-ጡር ነች… ፈጣሪ የስራውን ይስጠው እንዲህ ያደረጋትን እንጂ ምን ይባላል…›› ብላ በቁጭት ተነፈሰች፡፡ እብዷ አሁንም ሁለተኛ ነፍሰ-ጡር ነች፡፡ ይህንን ስሰማ እንዴት እንደነዘረኝ የማውቀው እኔ ነኝ፡፡

"ጨርሰናል"

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun abebe
6.1K viewsDAVE / PAPI, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-27 20:54:57 ከሁሉም አይኔን የሳበችው ግን አንድ ጊዜ ‹እማዬ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹አባዬ› እያለች የምትጣራ እና ሙልቅቅ ብላ አባዬን አላንቀሳቅስና ከሰው አላስወራ የምትለው ሕጻን ልጅ ነበረች፡፡ ሕጻኗን የ3 ዓመት ልጅ ገደማ መሆኗን መገመት ከባድ አልነበረም። የሚገርመው ግን ከ10 ቀን በኋላ ልክ 3 ዓመት የሚሞላት ልጅ መሆኗ ነበር፡፡ እሷ ማለት ደግሞ ያቺው ከላይ የተረኩላችሁ ተዓምረ-እግዚአብሔር ናት… "ሚጡ" እንበላት ለወጋችን ያክል፡፡ አባዬ እናቴ በምትጠራኝ ስም ‹በልዬ› እያለች ነው የምትጠራኝ፡፡ ሌላኛዋ አክስቴ ደግሞ ‹ጥላሁን› ነው የምትለኝ፡፡ በውስጤ ጥያቄ እንዳለ የገባት የመሰላት አባዬ ከምሳ በኋላ ቡና እየጠጣን በጨዋታ መሃል…‹‹ይኸውልህ በልዬ በስተርጅና ይቺን የመሰለች ልጅ ወለድኩ…›› ብላ ወሬ ከመጀመሯ ተዓምሪቷ ሚጡ አሁንም አላስወራ አለቻትና ከወሬው አናጠበቻት፡፡ ወዲያውም ደግሞ ለጠየቃትም ላልጠየቃትም ስሟን እስከ አያቷ ድረስ ደጋግማ መጥራት ትይዛለች፡፡
‹‹ማነው ስምሽ አንቺ…›› ሲሏት…‹‹እኔ… ሚጡ… አቡሽ… አባባ…›› ትላለች አሁንም አሁንም የራሷንም፣ የአባቷንም፣ የአያቷንም ስም ሳታዛንፍ በልጅ አፍ በትንሹ ኩልትፍ እያለችና ፊደላቱን እየጠራች፡፡ በአባትነት የምትጠራው አቡሽ በጥቂት ዓመት የሚበልጠኝን የአባዬ የመጨረሻ ወንድ ልጅ ነው፣ በአያትነት ደግሞ የአባዬን ባል (የአቡሽን አባት)…! ግራ መጋባቴ ቀጥሏል፡፡ አቡሽ የሚኖረው አሜሪካ እንደሆነና ይቺ ልጅ ከመወለዷ ብዙ ዓመት በፊት አግብቶ ልጆች
እንደወለደም አውቃለሁ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ አባዬ ወደ ጓዳ ሄድ ስትል… እህቴ ላይ የጥያቄ ፊት ዘረገፍኩባት፡፡ ይህን ያወጋኋችሁን ታሪክ እህቴ ከሌላኛዋ አክስቴ ልጅ ጋር ሆነው ፈጠን ፈጠን እያሉ ተጋግዘው በአጭሩ ነገሩኝ፡፡ ግፋ ቢል ከአምስት ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ አጠናቀቁት፡፡
‹ይህንንማ ከራሷ ከአባዬ ሙሉ ዝርዝሩን ካልሰማሁ በቀር አይሆንም…› አልኩና ለምሽት የእራት ላይ ጨዋታ አቆየሁት፡፡ አላስቻለኝምና እራት ገና እራት መብላት እንደጀመርን አነሳሁላት…‹‹አባዬ… ምንድን ነው ቅድም እኮ ስለዚህች ሕጻን ልጅ እንዲህ እንዲህ አሉኝ… ኧረ
እንደው ሙሉውን ንገሪኝ አባይዬ…›› ብዬ ጀመርኩ፡፡ ‹‹አይ በልዬ… የሷ ነገርማ ተዓምር ነው፡፡ ይሄ እናንተ በምታነቡት መፅሐፍ ውስጥ ራሱ ቢፈለግ አይገኝም…!›› አለችና ጀመረች፡፡ ‹ይሄ የምታነቡት መፅሐፍ ውስጥ አይገኝም›
ማለቷ በልብ-ወለድ እንኳን የማይታሰብ ነው ለማለት ነው፡፡ የንጽጽሯ ጥልቀት የገባኝ ታሪኩን ከጨረሰችልኝ በኋላ ነበር፡፡ Stranger than fiction የሚልና በጣም ወድጄ የተመለከትኩትን አንድ የሆሊዉድ ፊልም አስታወሰኝ አገላለጿ፡፡ ድንቅ ነበር ንጽጽሩ…!ለታሪኩ ስክት ብሎ የሚገባ ጠቅላይ ዐረፍተ ነገር…!ከዚያም ቀስ እያለች እስከላይ ድረስ የነገርኳችሁን ተረከችልኝ፡፡ የሰሙት ሁሉ እንደ አዲስ አደመጡ፡፡ አንዳንዴም በየመሃሉ እየገቡ ጨማመሩበት፡፡ ባለቤቴ በተፈጥሮ ያላት ቦጅቧጃ ስብዕና ላይ እናትነት ተጨምሮበት ፊቷን ለመግለጽ በሚከብድ ስሜት አብራኝ አባዬ አፍ ላይ ተተክላለች፡፡ እኔም በየመሃሉ ለማመን የሚከብደኝን ነገር በጥያቄ ማጣደፌ አልቀረም፡፡ ደጋግሜ የምጠይቃት ግን እንዴት ከሌቱ ስምንት ሰዓት ጀምሮ እንደዚያ ሆና በሕይወት ተረፈች…? እንዴትስ እስከ ማታ 11፡00 ድረስ ጡት ሳትጠባ ልትተርፍ ቻለች…? እንዴትስ
እትብቷ በዚያ መልክ ተበጥሶ እና ሳይታሰር ተረፈች…? እናትየውስ እንዴት ተረፈች…? ማለቂያ አልነበረውም ጥያቄዬ፡፡ ‹‹አይ በልዬ እንደሚሉትማ እትብት በ30 ደቂቃ ወይም ቶሎ ተቆርጦ ካልተቋጠረ ልጅ ይሞታል ይባላል፡፡ በዚያ ላይ ብርዱ፣ ዝናቡ፣ ጡት አለመጥባቱ፣ እንደዛ በጭቃ እያድበለበለች ስትጫወትባት አድራ በሕይወት መትረፏ ሌላ ምን መልስ አለው በልዬ…የፈጣሪ ስራ ነው እንጂ! የእመቤቴ ማርያም ስራ ነው እንጂ! የባለወልድ ተዓምር ነው እንጂ በልዬ! የሚገድልም የሚያድንም አንድ ፈጣሪ እንጂ እንደ ሰው ግምትማ መች ትተርፍ ነበር…!» የሚል ነበር መልሷ። አባዬ ይህን ስትለኝ በወቅቱ አንቀጹ ትዝ ባይለኝም ድሮ መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ያነበብኩት አንድ ጥቅስ ትዝ አለኝ፡፡
‹‹አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ፤ እኔ እገድላለሁ፥ አድንማለሁ፤ እኔ እመታለሁ፥ እፈውስማለሁ፤ ከእጄም የሚያድን የለም።›› ዘዳግም ምዕ.32፣ ቁ.39፡፡ እውነትም ይህን ጥቅስ ከማመን ውጪ ሌላ ሰውኛ ማብራሪያ ለመስጠት ከባድ ነውና
እኔም በፈጣሪ የማያልቅ ተዓምር ተደምሜአለሁ፡፡ እኔ በማምነው መንገድ በፈጣሪ ላይ ያለኝን እምነቴንም ይበልጥ አጠናክሮታል፡፡ አባዬ ብዙ ካለችኝ በኋላ ታሪኩን እያጠቃለለች ነው፡፡ ‹‹እናልህ በልዬ… እቤት ከመጣን በኋላ አቡሽዬ ሲደውል ነገርኩት፡፡ ‹አቡሽዬ… ይኸውልህ
በስተርጅና ሴት ልጅ ወለድኩ› አልኩትና ታሪኩን ስነግረው እጅግ ተደስቶ ለየዘመዱ እየደወለ ‹አባዬ ልጅ ወልዳለችና እንኳን ማርያም ማረሽ በሏት…› እያለ ሰዉን ሁሉ ግራ አጋባው፡፡ ወዲያውም የሚያስፈልጋትን በሙሉ እሱ እንደሚያሟላ እና የአባትነት ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ቃል ገብቶ ይኸውልህ ሚጡም በሱ ስም ትጠራለች… እሷም አባትሽ ማነው ስትባል አቡሽ ትላለች…›› አለችና ተነስታ ከፎቶ ማህደሯ ውስጥ ከልጅነቷ ከምሮ ያስነሳቻትን ፎቶዎች አምጥታ ሰጠችኝ፡፡ እየተቻኮልን እና እየተቀማማን ተመለከትነው፡፡ ገና የወር ዕድሜ ሳይሆናት ጀምሮ በየጊዜው የተነሳቻቸው ፎቶዎች ልዩ ናቸው፡፡ የአንድ ዓመት እና የሁለት ዓመት ልደቷ ሲከበር ድል ያለ ድግስ እንደነበረው መመስከር ይቻላል፡፡ ሁለት ፎቶዎች ትርፍ ቅጂ ስለነበራቸው አባዬን ለምኜ ፈቀደችልኝና ወሰድኳቸው፡፡ ከሁሉም ግን የልደት ፎቶዎቿ ይለያሉ…‹‹ይገርማል፣ በተለይ ለልደቶቿ ትልቅ ድግስ ነው ያደረግሽላት አባዬ…›› አልኩ፡፡ ‹‹እኔ አይደለሁም በልዬ… የሚገርምህ ልጅቷ ከዚህ ሁሉ ታሪኳ ቀጥሎ የሚገርመኝ በብዙ ነገር ዕድለኛ ነች፡፡›› አለችና በሁለቱ ልደቶቿ ወቅት ድግሱ እንዴት ሊያምርላት እንደቻለ የተከሰቱትን ድንገቴዎች አወራችኝ፡፡ ‹‹ይኸው አሁን ደግሞ ሶስተኛ ዓመት ልደቷ መጪው ባለወልድ ነው ከ11 ቀናት በኋላ፡፡ ነገር ግን ሚሚ መጪው ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ ስለምትሄድ ልደቷን ቀድመን እናክብር ብለን ነገ ልናከብርላት ወስነን ነበር፡፡ እኔም ቤት ባፈራው የሆነውን አደርጋለሁ ብዬ እንጂ በግ አርዳለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ ይኸው ዕድለኛ ነች ብዬህ አልነበር… አምላክ ደግሞ ምንም የማታውቀውን አንተን በግ አስገዝቶ ላከላት… ታዲያ ከዚህ በላይ ዕድለኝነት
አለ…? ኧረ የሷስ ድንቅ ነው በልዬ…›› አለች፡፡
እንዳለችውም እኔ እጅ መንሻ ብዬ የወሰድኩላቸው በግ በነጋታው ዕለተ እሁድ ታርዶ፣ የልደት ግብዓቶች ሁሉ ተሟልተው ትልቅ ድግስ ሆኖ የሚጡ 3ኛ ዓመት ልደት በድምቀት
ተከበረ፡፡ ድንቅ እኛም እሁድን አድረን ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ተመለስን…! ማክሰኞ ማታም ይህንን ታሪክ ማካፈል ጀመርን…!እነሆ ዛሬ ዕለተ ረቡዕም ለመደምደም እየተንደረደርን ነው…!
***
መውጪያ…
(እስቲ ደግሞ ጥቂት አብረን እንናደድ) እብዷን የደፈራት ሰው በአደባባይ የሚታወቅ ጤነኛ ሰው ነው መባሉን ስሰማ በመጀመሪያ የተሰማኝ ስሜት "ምናለ ፈጣሪ ያን የሚደፍራትን ሰው እጅ ከፍንጅ ቢያሲይዘኝ…" የሚል ነበር፡፡
5.7K viewsDAVE / PAPI, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-27 20:54:57 እውነት እብዱ ማነው?
ክፍል - ሁለት
(የመጨረሻ ክፍል)

አባዬ፣ አለወትሮዋ የጠዋቱ ብርድ እና ዝናብ ከአልጋ አላላቅቅ ብሏት ተኝታለች። ሰዓቱን
ስትመለከት ሶስት ሰዓት ገደማ ስለሆነ እንደምንም ብላ ተነስታ ወደ ማርያም ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ሳያልቅ ለመድረስ ተጣድፋለች። በዚያ ላይ ከልጆቿ መካከል አራቱን የወለደችው በባለወልድ ቀን ስለሆነ ለባለወልድ የተለየ ስሜት አላት። "አዬ የኔ ጉድ፣ ለዛውም በባለወልድ ቀን እንዲህ ላርፍድ?" እያለች ነጠላዋን ተከናንባ ከወጣቷ ልጇ ሚሚ ጋር አውራ መንገዱን ተሻግረው ወደ ማርያም የሚያስገባውን መንገድ ሲጀምሩ ከአንድ ግቢ ውስጥ የሚጮኹ፣ የሚንጫጩ፣ የሚተራመሱ ሰዎች ሲመለከቱ በድንጋጤ እየተጣደፉ ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሁለቱም በአይናቸው ያዩትን ማመን አልቻሉም…በግቢው ውስጥ ያለው አብዛኛው ሰው ፈራ-ተባ ባለበት ወቅት አባዬ አለፍ ብላ የማትናገር የማትንቀሳቀሰዋን ሕጻን አንስታ በሕይወት ትኑር ትሙት ለማወቅ ትንፋሿን ለማዳመጥ ሞከረች። ከሌቱ ስምንት ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ ሶስት ሰዓት ድረስ ለዘለቁት ሰባት ወይም ስምንት ሰዓታት ገደማ በዚያ አይነት ሁኔታ የቆየችው አራስ ልጅ አሁንም እስትንፋሷ አለ፡፡ በምን እንደተቆረጠ የማይታወቀው ቁራጭ እትብቷ አሁንም ሳይታሰር ጠልጠል እንዳለ ነው፡፡ አባዬ ሕጻኗን ለሚሚ ሰጥታ እየሮጠች ወደ ቤቷ ተመልሳ መጠራረጊያ እና ማቀፊያ የሚሆኑ ልብሶች ይዛ መጣች፡፡ ልጅቷን ሲጠራርጓት በጣም የገረማቸው ነገር ከጭቃ በቀረ ምንም አይነት ደም የቀላቀለ ነበር አልነበረባትም፡፡ ምናልባትም እናትየው ከወለደቻት በኋላ በዝናቡ ውስጥ መንገድ ላይ ዘለግ ላለ ጊዜ ይዛት ስለቆመች ዝናቡ አጥቧትም ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ጭቃዋ ሲጠራረግ ልቅም ያለች ቀይ ልጅ ብቅ አለች፡፡ ‹‹ፀጉሯ ግንባሯ ድረስ ድፍት ብሎ ቻይና ነበር እኮ የምትመስለው…›› ትላለች አባዬ ለኔ ባወራችኝ ጊዜ እንኳን ሶስት ዓመት ወደ ኋላ ተመልሳ በትዝታ፡፡ የግቢው ባለቤት፣ አባዬ እና ሚሚ ልጅቷን ከበው ምን እንደሚያደርጉ ለአፍታ መምከር ጀመሩ፡፡ ‹‹ለመንግስት እንስጣት ይሆን እንዴ…? ምን ይሻላል…? ምንስ እናድርግ…?›› ይላሉ
የግቢው ባለቤት፡፡ ‹‹አዪ ለመንግስት ብንሰጥስ ምን ይበጃታል ብለሽ ነው…? መጀመሪያ ግን ወደ ጤና ጣቢያ መውሰድ አለብን… ሌላውን በኋላ እናያለን…›› አሉ አባዬ ልባቸው የሚነግራቸው ሌላ መፍትሄ እንደሆነ በውስጣቸው እርግጠኛ ሆነው፡፡ መጀመሪያ ግን የልጅቷን ሕይወት ማትረፍ እንደሆነ ስለገባቸው ወደ ጤና ጣቢያ ለመውሰድ እየተሰናዱ፡፡ አባዬ በቃል አያውጡት እንጂ በልባቸው ያለውን አሳብ ምንም ሳይዘገይ ነበር ሚሚ ያቀበለችው፡፡ ይህ ሲሆን ሚሚ ነበረች የተጠራረገችውን ልጅ በማቀፊያ ይዛ የነበረችው፡፡ ‹‹አባዬ ይቺን ልጅማ ለማንም አንሰጥም… እኛው እናሳድጋታለን…›› አለች ፍጹም ፍርጥም ባለ እርግጠኝነት እና ስስት በእቅፏ ያለችውን አራስ ቁልቁል ትክ ብላ እያየች…‹‹ይሁን እኔም እንደሱ ነበር እያሰብኩ የነበረው… በይ ወደ ጤና ጣቢያ እንውሰዳት መጀመሪያ… በጣም ደክማለች…›› ብለው እየተጣደፉ ወደ ጤና ጣቢያ ሄዱ፡፡ ጤና ጣቢያ ደረሱ፡፡ ቁራጭ እትብቷም ተቋጠረ፡፡ ሙቀቷ 27 ዲግሪ ስለነበር በወቅቱ የነበረችው ሐኪም ወደ ማሞቂያ ክፍል እንድትገባ አደረገቻት፡፡ ሕጻኗ እየቆየች የበለጠ
ነፍስ እየዘራች ብትሄድም አንድም ጊዜ ስላልጠባች ጉዳት እየገጠማት ስለሆነ እነ አባዬ እብዷ ወዳለችበት ተመልሰው መጥተው እንዴት አድርገው እናትየውን አግባብተው በመውሰድ ልጅቷን እንድታጠባ ለማድረግ ከሰፈሩ ሰዎች ጋር ይመክራሉ፣ ይህ ሲሆን ተሲያት ሆኗል፡፡ የሚሚ ስልክ አቃጨለ፡፡ ሐኪሟ ነበረች… ‹‹ሐሎ አለች ሚሚ…›› ምናልባትም መጥፎ ዜና ልትነግራት የደወለች መስሏት እንደመደንገጥ ብላለች፡፡
‹‹ሐሎ… ምንድን ነው በዚያው የጠፋችሁት…እዚህ አምጥታችሁ ጥላችሁ የሄዳችሁትን
መጥታችሁ ውሰዱ እንጂ… ማን ላይ ጥላችሁ ለመሄድ አስባችሁ ነው…›› እያለች
አበሻቀጠቻት፡፡ ‹‹ስሚ የኔ እህት… እዚያ ጥለን የሄድነው ዕቃ አይደለም… የሰው ልጅ ነች እሺ…!?
እንዲህማ ልትናገሪ አትችዪም እሺ…! ለማንኛውም አሁን እንመጣለን ሌላ ትርፍ ነገር
አትናገሪ…›› ብላ እሷም አስታጠቀቻትና ወደ ጤና ጣቢያው ተመለሱ፡፡ እብዷም በዚህም በዚያም ተወስዳ ልጅቷን ባታጠባም ቢያንስ ኤች.አይ.ቪ እንድትመረመር ተደረገ፡፡ የፈጣሪ መልካምነት ማለቂያ አልነበረውምና እናትየው ከቫይረሱ ነፃ መሆኗን ሲያውቁ ለሁሉም ትልቅ እረፍት ነበር፡፡ ልጅቷን የማጥባቱ ነገር ግን የሚሆን ስላልሆነ
ከአመሻሹ 11፡00 ገደማ የፎርሙላ ዱቄት ወተት ተገዝቶና በጡጦ ተበጥብጦ ልጅት አፍ ላይ ሲደረግ በርሃብ ስትናጥ የነበረችው ሕጻን ወዲያው መጥባት ጀመረች፡፡ አባዬ ትልቅ
እረፍት እና ደስታ ተሰማት፡፡ የሚገባውን ጊዜ ወስደው፣ ልጅቷ በሙሉ ጤንነትና ጥንካሬ ላይ ስትሆን አባዬና ሚሚ ልጃቸውን ይዘው ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ለአባዬ ትልቅ ትዝብት የነበረው ነገር እና እስካሁን ስታወራው እጅግ እየከነከናት ያለው ነገር አንዳንድ ሰዎች፣ የጤና ጣቢያዋን ሐኪም ጨምሮ የተናገሩት ነገር ተመሳሳይ እና እጅግ ኢሰብዓዊ የመሆኑ ነገር ነበር፡፡ ‹‹እንዲህ አይነቱ ልጅ ሲገኝስ ወስዶ ማሳደግ ነበር…! ግን ምን ዋጋ አለው… ሴት ሆነች እንጂ…! ወንድ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ቤት ይጠብቃል… ወይም ጥሩ እረኛ ይሆን ነበር… እያሉኝ እኔ ግን ልጄን ይዤ ስመጣ በጣም ነበር ደስ ያለኝ…›› ትላለች አባዬ አሁንም በጥልቅ ትዝብት የሰዎቹን ክፋት እየታዘበችና ወደኋላ እየተመለሰች፡፡ "ልጄ" ብላ ነው የምትጠራት። አባዬን ላስተዋውቃችሁ…?
አባዬ አክስቴ ነች… የእናቴ ታናሽ እህት… ከመንታ የማትተናነስ ቁርጥ እናቴን መሳይ…ከቁመና እስከ ፊት መልክ… ከድምጽ እስከ ውስጠ ስብዕና…! ላለፉት 14 ዓመታት አባዬን ባየሁ ቁጥር ስሜቱን ለማስተናገድ እጅግ ከባድ ነበር ለኔ፡፡ እናቴ ከሙታን ዓለም መጥታ የምታናግረኝ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር መመሳሰላቸው… ድምጻቸው… ስብዕናቸው…እርጋታቸው… ጥርሳቸው… ጣቶቻቸው… ምኑ ቅጡ…!እናም አባዬን ለመጨረሻ ጊዜ ያየኋት ሌላኛዋ አክስቴ በሞተች ወቅት ለቀብር እዚያች ከተማ በሄድኩበት ጊዜ ነበር፡፡ እሱ ደግሞ ጊዜው ዘለግ እያለ ስለመጣ የሆነ ቀን ታላቅ እህቴን አብረን ሄደን እንደምንጠይቃት እንደዋዛ ቃል ገባሁላት፡፡ እህቴም የዋዛ አልነበረችም አውቃ ቀን አስቆረጠችኝ፡፡ እኔም ተስማማሁ፡፡ ቀኑ ደረሰና ከመጓዛችን በፊት ባለቤቴም የጉዞው ተሳታፊ እንደምትሆን አሳውቃን እጅግ ደስ የሚል ጉዞ አደረግን፡፡ አባዬን እና ሌላኛዋን አክስቴን እንዲሁም ዘመድ አዝማድን ከማየት እና ከመጠየቅ በዘለለ እንዲህ አይነት ተዓምረ ክስተት እመሰክራለሁ ብዬ ፍፁም አላሰብኩምም አልገመትኩምም ነበር፡፡ ቅዳሜ ተሲያት በኋላ ነበር የደረስነው፡፡ መምጣታችንን ቀድመን አሳውቀን ስለነበር ምንም ነገር ሳይጎድል ሁሉ ሙሉ ሆኖ ነበር የጠበቀን፡፡ ደስታው ልዩ ነበር፡፡ የአክስቶቼ ስስት የሚዘገን የሚታፈስ ነበር፡፡ እናቴን እያስታወሱ ለማለቃቀስ ሞከር አድርጓቸውም ነበር እኔ ኮምጨጭ ብዬ መለስኳቸው እንጂ፡፡ እነሱ እንደሁ እናቴን አንስተው ለማልቀስ ጥንጥዬ ነገር በቂያቸው ነች፡፡ በዛውም እንደ ወናፍ እስክወጠር ድረስ ‹ዘመድ ጠያቂና ቁምነገረኛ› መሆኔ ተደጋግሞ
ሲነገረኝ፣ ስመሰገን፣ አሁንም አሁንም ስመረቅ እንደ መነፋፋትም ቢጤ ሞክሮኝ ጎምለል ማለቴ አልቀረም፡፡ ቤቱ ውስጥ የአክሰቶቼ ልጆች፣ ጎረቤት፣ ተጨማሪ ዘመድ አዝማድ ውር ውር ይላል፡፡
4.3K viewsDAVE / PAPI, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-27 20:54:35
#የህልም ፍታት - ከአመታት ወደ ቀናት

ክተታችን ደርሶ እየመታነው እንገኛለን። አዲስ ነገርን አስበን ብዙ አስበን ሩቅ አልመን ያዘጋጀነውን አጣፍጠን የሰራነውን ማዕድ ብትቀምሱ ለብርዱም ኩታችሁን ደርባችሁ የኪነ-ጥበብ ማዕድ ላይ ብትቋደሱ እያልን ስንጋብዝ። ገጣሚው ቃሉን ሰድሮ ሙዚቀኛውም ዜማውን ወጥሮ የሰራውን ማዕድ ቅመሱልኝ ብሎ ስለተጣራ ሁላችሁም በጠራነው ክተት ተከታችሁ ነሀሴ 23 ፒያሳ በሚገኘው hi5 coffe house እንድትገኙ እንላለን። ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ የእሽቅድምድም ጉዳይ እና ቀድሞ ብታ የማስያዙ ጉዳይ ይታሰብበት ልንል እንወዳለን። ኩታችሁን ደርባችሁ አልያ በሀገር ባህል ልብስ አሸብርቃችሁ ኑልን እኛም ጎንበስ ብለን እንቀበላለን።

ሁላችንም ግብዣውን እናድርስ
share
4.4K viewsDAVE / PAPI, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-23 09:28:04 "The secret of your future is hidden in your daily routine."

@words19
5.5K views ገብርዬ, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-21 20:41:44 መቼም ጊዜ የማያሳየን ጉድ የለም።
ዛሬ የ you tube ከርስ ውስጥ ገብቼ አንጀቱን ሳማስል ቆየሁ። ከሁሉም ከሁሉም ግርምቴን የወሰደው የ 90 ዎቹ ሙዚቃ ነበር ። ሙዚቀኛ አቤል ነይ ማታ ማታ የሚለውን ሙዚቃ መለስ ብላችሁ እዩት እስቲ?
አቤሎ ያደረገው ከርፋፋ ሱፍ አነስ ያለ ዩንቨርስቲ ተምረው ለመመረቅ የተዘጋጁ 5 ተማሪዎችን ጥንቅቅ አድርጎ ያስመርቅ ነበር ... አቤት የሱፍ ግፍ! ጓዶች በ 90 ዎቹ ጊዜማ የሱፍ ጨርቅ ላይ ግፍ አቆይተናል። እዛ የሰራነው ግፍ ነው ዛሬ ሱፍ ልብስንም የሱፍ ቆሎንም ያስወደደብን
ወደ አቤሎ ሱሪ አዘቅዝቄ ተመለከትኩ።
ሱፍ ዑመር ዋሻማ ምን ይሰፋል? እንዝርት ለምታክል ቅልጥም የደብረ ብርሀን ብርድ ልብስ የሚያህል ጨርቅ ሱሪ ገድግዶበታል።
ወያኔ ምሽግ ሳይሰራ የቀረው እሱ ሱሪ ውስጥ ብቻ ነበር
ደግሞ ሁሌ ሁሌ የሚል የሀይልዬ ክሊፕ አለ። በሰዓቱ ብዙ እይታ አድርጎ የሰቀለው ቪድዮ ላይ የሚደንሱ ሴቶች ሁለቴ ራመድ.. .ሶስቴ ወደ ኋላ መለስ እያሉ ይጨፍራሉ ። ደግሞ አሰላለፋቸው የኮንሶ ወረዳ ካዘጋጃቸው እርከኖች ፈፅሞ አይለይም።
ወደ ሌላ ሙዚቃ ተሸበለልኩ።
አሸንፈን...አሸንፈን...በማራቶን
ወይኔ ወንድሜ ጆሲ !
የራሱ ትልቀትና የሰውነቱ ቅጥነት የሚመጠጠውን ከረሜላ ቁጭ!
ጀላቲም እንደመምሰል ይላል ። ፈረንጆች ይሄን አይተው ኖሯል ለካ እናንተ ጠኔያሞች ብለው የሚሞሸልቁን።
ነይ በክረምት የሚለው የመስፍኔ ሙዚቃ ለጥቆ መጣ ። የዳሎል ጨው !
ጭው ያለ ፊት ... የኢትዮጵያን መከራ የተሸከመ ፊት...ጦርነት ፊት ። ንግድ ባንክ ፊት ... ከዚህ እስከዛ ፊት ...ከዛ እስከዚህ ፊት ይሄም ቢሆን ግን የእናት አሜሪካ ውለታ ን መዘንጋት የለብንም። የማክዶናንድ በርገር አጋርነትን መርሳት የለብንም። መስፍኔ እንደገና ተወለደ ! መስፍኔ እንደገና አበበ ። መስፍኔ ከጨው ፊት ወደ ፓሎኒ ኳስ ፊት ያሸጋገርክልን ጌታ ክሪሺና ምስጋናህን ውሰድ
ትንሽ ቆየት ያለ የፍቅራዲስ ሙዚቃ ደግሞ ዠመረ ። ብትን ጨርቋ ብትንትን ብሎ መሬት ላይ ፍስስ.. .ስጋ ያልያዘ ፀጉራም ፍየል ቁጭ! ዛሬ እድሜ ለጊዜ ይሁንና የፍቅርዬ ቻፓ ወንዱን ሁሉ እያማለለው ይገኛል /አበበ ብርሀኔ አፉ ይበለኝና ቻፓዋ ግን ይመስጣል! /
ቴዲ አፍሮን ብነካ ጀማው ይነክሰኛል እንጅ የሆነ ዳፍንታም መነጥር አድርጎ ለማን ልማሽ እያለ መሞዘቁን ላሽ ልል አልፈልግም። ለዛ ክሊፕ ሳይሆን ለብረት ቤት ብየዳ አገልግሎት ነበር ያ መነጥር መዋል የነበረበት ።
ከአፍታ በኋላ ቴድዮ ከተፍ አለች ። ጡት ከጣለ ሳምንት ያልሞላው ምስኪን ራፐር ። የጉራጌ ቶን ምናምን ክሊፑ ላይ ሲደንስ ሳየው እንደ ወፍ እንዳይበር እንዴት እንደፈራሁለት ብታዩ!
በሰው ይሄን ያህል ስቄ ከ አራት ዓመታት በፊት የተነሳሁትን የራሴን ፎቶ አየሁት ።
በዛን ጊዜ ሉሲን አገኘኋት ያለው አንትሮፖሎጂስት እኔ አይቶ መሆንማ አለበት !
እህል ከቀመሰ ዓመታት ያስቆጠረ ነብይ ይሄን ያህል አይሞግግም። ስማር ነበር ወይስ ተማሪዎችን ፉጨት ሳስተምር ነበር ? በሚል ጥያቄ ትንሽ እንደተወዛገብኩ.. . የመሰረት መብራቴ ድራማ ሰተት ብሎ ላፕቶፔ ስክሪን ላይ ተገሰጠ ። መሲ የኔ Philps ከጥንት እስከ ጠዋት አንድ አይነት ፊት።
አባቴ በጋን ቁልፍ ጠርቅሞ ሲጠቀምበት የኖረው Philips ካውያ ዛሬም ድረስ አዲስ መሆኑን አስቤ ፈገግ አልኩኝ።
አባዬ ካውያውን ዝም ብሎ ሲያየው ይቆይና አይ የድሮ እቃ! ይላል በግርምት ። በነገራችን ላይ እሷን ካውያ የነካ አይደለም የቁም ሳጥኗን ቁልፍ በእጁ የያዘ የቤተሰቡ አባልን አባዬ በርግጫ እንደ ኳስ ያነጥረው ነበር ። ቀልቃላዋ ታናሽ እህቴ ስንት ጊዜ በረንዳውን ተሻግራ የግቢው አበባ ላይ እንዳረፈች እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው !
ሸሚዙን ጠረጴዛ ላይ ጥሎ ካውያውን ከወዲህ ወድያ ሲያንገላታው መሲዬ ን ያሰቃያት እየመሰለኝ በልቤ አዝንበት ነበር :)

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael aschenaki
6.9K viewsDAVE / PAPI, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-21 09:07:19 ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ አስተማሪውን "አስታወስከኝ ወይ?" አለው።አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" አለው፤ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ፤ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር።እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ሄዶ ይናገራል፤አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፍታችንን ወዴ ግድግዳ ኣዙረን እንድንቆም አዘዝከን።በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤የሚገባበትን አጠሁ።አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ሲሆን፤ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርግቴን ስሰሙ።በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ስገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤በቃ መጥፎ ዜናው ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ።ፍተሻውም ስያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን።እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ።በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠራ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤አንተም ምንም ብለሃኝ አታውቅም።እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬ እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው።አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

# NB በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል።እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ግጥም አብዮት
6.8K viewsDAVE / PAPI, 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-12 13:49:17 #ወግ_ብቻ

#ናፍቆትህ ናፍቆኛል. .
ትዝታዬ
.
" . . . ወሰን አልባው ፍቅርሽ ፣ ጠብቆኝ
በስስት ፣ አድርጎኛልና መንገዴን እንዳልስት።

ለአንኳኳለት ሁሉ ልቤ አይከፈትም ፣
እንኳንስ አካሌ ሃሳቤ አይሸፍትም።. . . ..
. . . "

ይኼን ሙዚቃ እንደ ዛሬ ብቻዬን ሳልቆዝምበት በፊት………ጮክ ብለን ዘፍነነዋል . . . ተለጣጥፈን አዳምጠነዋል. . . ተገባብዘነዋል. . . ትዝታ ፅፈንበታል. . . . .

ያኔ ……

ጥር ከመግባቱ በፊት ሳውቀው. . .

"ምወደው ጫካ አለ" አለኝ የመጀመርያ የአብሮነት ምሳችንን እየበላን ነበር. . .

"ትወስደኛለህ "

"ከፈለግሽ ደስ ይለኛል "

ካለንበት ዕሮብ ለቀጣዩ ዕሮብ አቀድን. . .

ፍቅሩን አንዴ ነው የጠጣሁት ለዚህም ነው አሁንም እንደ አማልክት ምኖረው. . .

የዓለምን ምስጢር የገለጠልኝ እውነት ነበር. . . ሚሆነውም እሱ ነው. .

አስፈሪው ጫካውን ሲያሳየኝ አልፈራውም ፣ አልደነገጥኩም. . . . አልተጨነኩም. . . . ነፍሴ ስትዘል . . . ስታመሰግን አየዋት . . . ያኔ ነው ያፈቀረችው መሰለኝ . . አክብራው ስታጎነብስ አይቻታለው. . . ነፃነቷን ሰቷት ነበር እና. . . .

ከዛ ቀን በኃላ ከንፈናል . . . ያለሱ ሚታየኝ ውበት፣ የሚጣፍጠኝ ስም አጣው. . . በረርኩ . . ልቡ ውስጥ ፣ ነፍሱ ውስጥ ፣ አዕምሮው ውስጥ . . በፍቅር ፈቀደልኝ. . .

ለኔ ደክሞት ፣ሰንፎ አያውቅም. . . ያፈቅረኛል!!
ፍቅሩን መላው አካላቱ ይናገራሉ. . .


ሊመሽ ሲል ከመለያየታችን በፊት መንገድ ዳር ሻይ እንጠጣለን. . . እኔ ችፕስ ወዳለው . . . እሱ ጨጓራውን ያመዋል . . . ቢሆንም ይበላልኛል. . .ቦታውን ወዶት እኮ አደለም ሚቀመጥልኝ እኔ ስላልኩት ነው. . . .

ማይወደውን ፣ ማይፈልገውን ሁሉ ለኔ ፣ ለፍቅራችን ሲል ፈልጎት ነበር . .

* * *


ዛሬ…………

ደክሞት ፣ ደክሞኝ ጠፍተናል. . . የዘረጋነውን እውነት በመቆሳሰል ደብቀነዋል. . . ያቀፈኝ ክንዱ ተሰብስቦዋል ፣ ጥጉ ፣ ጥጌ ላይ ነኝ. . . ህልሞቻችን ከቀኖቻችን ጋር ተኳርፈዋል . . . የራሱ ልብ ውስጥ ፣ የራሴ ነፍስ ውስጥ ተወታትፈናል. . . . ደምኖብናል . . .

እራሴን ጠይቃለው " ፍቅራችን እውነት አበቃ ?"

ይቆጨኛል. . . ሚቆጨኝ ስለሌለ ሳይሆን ያልነገርኩት ስላለ ነው. . .

"ያልኖርኩልክ የቀረኝ ሂወት አለኝ. . . ያላሳየሁክ ያልሆንኩልክ እውነት አለኝ ፣ ውሃን ልወልድልህ ፈልጋለው ፣ እስከ እድሜዬ አመሻሽ አንተን ነው ምፈልገው ፣ እንደ ደነስናቸው ዳንሶች ፣ እንደነበሩን ፀሃይና ጨረቃ ፣እደተሳሙት ከንፈሮቻችን ፣ እደተራመድንባቸው ጓዳናዎች ፣ እዳለቀስንበት ምሽት ፣በጅብ እንደፈራንበት ቀን ፣ እንደ ደበደበን ዝናብ ፣ እዳቃጠለን ሀሩር ፣ እንደ ጉርሻችን ፣ እንደ ሰጠከኝ አበቦች . . ተው ትዝታ አንሁን . . " ልለው ፈልጋለው!

"ከአንተ ጋር የአንዲት ሰዓት ሐሴት ዘላለማዊ ውድ ቅርፅ ነው።. . . ፍቅራችን ከዘመናት በፊት የጠፋውን ማሙዝ እንዲሆን አልፈልግም. . . የሳትነውን መንገድ እንመለስበት፣ ኑርልኝ፣ ልኑርልህ ፣ ና ፣ ልምጣ " ልለው እፈልጋለው

. . . . ግን አልለውም

አንዳንድ እውነቶች መነገር አይፈልጉም ፣ ቁጭትን እየወለዱ ቢሆን እንኳን በመደበቅ ይፀናሉ. . .

ቢሆንም ናፍቆትህ ዝም ብሎ ይናፍቀኛል ፣ ናፍቆ ያሰኘኛል. . . እንዳልመጣም ፣ እንድመጣም
ይመክረኛል!!

/ትዝታ /


|❀:✧๑♡๑✧❀|

@wegoch
@wegoch
@wegoch
7.7K viewsC-ራክ, edited  10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ