Get Mystery Box with random crypto!

እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ል | ወግ ብቻ

እስስት : ስትጎተትና : ስትቀያየር እንደምትጠላ : አታውቅም : አካሄዷም : ቢሆን ፥ አይኗ : ልቧን : ይመራዋል : እንጅ ልቧ : አይኗን : እንደሚከተለው : አታውቅም.....
ግንኮ : አይን : ያየውን : ለልብ : ካልነገረው : ልብም : አድምጦ : ካላመነበት : አይንን : ይከተለዋልን?

መቼም አንዴ ለጉዞ ፈጥሮኛልና መንገድም : እወድ የለ .....
በጉም : ላይ : እየተረማመድኩ : ሳለ ብቻዬን : አግዜሩን : አግኝቸው : ነበር : በምናባዊ : ፀዳል እንደምናስበው : አደለም : ኮስማና ነው።

እናተ : ሰዎች: ለምን : ትጠሉኛላችሁ : ስለምንስ ከክብሬ : ቁልቁል : አፈረጣችሁኝ : ማቅለላችሁ : ሳይቀር : ለሌሎች : መሳለቂያ : አረጋችሁኝ ፥ ከዙፋኔ እያለሁ : እንደሌለሁ : አበሸቀጣችሁኝ ለምን? ስለምንስ? ተጠራጣሪ : ሆናችሁ : በኔ ለምን? እንባ እንቅ እንባ እንቅ ,,,,,
እያረገው : ሶስት : የእንባ : ዘለላ :ከገፁ ፥ ሲረግፍ እየሁ።

እንባው ፥ ወደስቅለቱ : ትዝታ : እያላጋ : ወሰደን በስቅለቴ : ግዜ አንድ : ደንባራ : ወታደር : በጦር ጎኔን ሲወጋኝ : ህመሙን : አታውቅም : ይሁዳ : በከንፈሮቹ ሀሞት : ተጎንጭቶ : ጉንጨ : ላይ : ሲተፋብኝ : የተሰማኝን : አታውቅም : ጴጥሮስ : ሶስት : ግዜ : አንድ ለአብ አንድ ለወልድ አንድ ለመንፈስቅዱስ ለያንዳንዳችን : በአንድነት : የክህደትን : ኮሶ : ሲያግተን : ምሬቱን : አታውቅም።

40 ቀን 40 ለሊት ስፆም ሰይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈትነኝ የፈጠርኩትን መልሶ የኔ ሊያረጋቸው ሲደራደረኝ ቤተ መቅደሴን ሲሻቀጡበት እናቴን ከቁሻሻ መሀል ትቢያ እንደተደፋ ልቅላቂ ሲጠየፏት አታውቅም።

አዎ አታውቅም ........ እናት ሰዎች ህመሙን አታውቁም .........

የእግዜር እንባ ግን ምን አይነት ነው?

እኔም: ሆድ : ብሶኝ : የልቤን : ዘረገፍኩለት :ጌትዬ : በሁለት : አለም : ሰካር : ውስጥ: አየዳገርኩ: ለምን ዝም አልከኝ? አንተኮ: ብትታመምም : አምላክ ነህ የአምላክነትህ : ባህርይ ረቂቅ : ነው ያስችልሀል::

ግን ለምን ፈጠርከኝ? ማጥ: ረመጥ : ውስጥ : ከተትከኝ? እውነት አውጣኝ : ብዬ : ስለምንህ: ሳትሰማኝ : ቀርተህ ነው?
የህይወትስ ጣዕሙ በምን ይለካል ? በድን : አካልን አሸክመኸኝ : ለአመመታት : መክረሜን ዘንግተኸው ነውን?

እኔ : የነካሁት : ሁሉ : ርኩሰትን : እንዲላበስ : ሁሌ እንድሸሸግ : የምታረገኝ : ራሴን : በራሴው እንደ እፉኝን : ስውጥ አላሳዝንህምን?

የእናትህስ : ህመም : አንተን : ብቻ : የሚቆረቁርህ ይመስልሀል?
እሷኮ : አምጣ : አልወለደችህም : ደም : አልፈሰሳትም
ምነው_ቸሩ _መድሀኔ_አለም : የኔዋ : እናት: ወዝ ወዘናዋን : አጠንፍፋ : ባማጠች : የህመሟን ሲቃ ባስረቀረቀች : አኔን : ወልዳ : እንኳ_ማርያም : ማረችሽ ቢሏት : አንተው : የማርካት መሰለህ? በድኩም : አካሏ : ተንፏቃ : አፈር : ልሳ : ብትለምንህ : መች ምሬሻለው : አልካትና? የማርያም ልጅ...!!

አንተ : ብትፆም :ባህሪህ : ቅዱስ : ነህና : ይፈቅድልሀል እኛስ :አንጀታችን :ሲታለብ :ቆርቆሮ :ቤታችን :ውስጥ : በችጋር : ስንለበለብ :ዞር ብለህ : አይተኸናል : እንዴ?
ቅፅበታዊ : ደስታን : አሳይተህ : ዛላቂያዊ : ህመምን ከልባችን : የቸነከርከው : እውነት : ከሳዶርና ፣ አላዶር የሚተናነሱ : ይመስልሃልን?

ተው : እንጅ : ቤዛ ከሉ መድሀኔ አለም..... ተው እንጅ የማርያም ልጅ!!

ተስፋዬን : በምኞት : ደግፌ : ብጓዝ :ባንተ : አይደል የጨነገፈው : ማያዬ :መመልከቻ : አድማሴን : ባገኛት
ባንተም : አይደል : ያጣኃት? እንደኩታ : አይሽሞንሙነህ : ያለበስከኝ : ይህን :ማንነት አንተም አደል : የፈጠርከው ? ይኸው : እሷም /ወደመሸሹ አጋደለች....
እስቲ : ልወቀው : ጥፋቴን :ለምን : ግራ አርገህ ፈጠርከኝ?
ምን ትለኝ ይሆን? ምንስ ምላሽ ይኖርህ?

ግን ለምን አትወስደኝም? ኖሬ : የህይወት : ጣዕሙንስ በምን :ምላሴ : ላጣጥመው? ምላሴን : ቆርጠህብኝ ......ሳላጣጥመው : ኮመጠጠኝ።

ተፈጥሮ : ፊቱን : አጨፍግጎብኝ : ሳለ : ከነፍሴ የተጣባች : እንስትን : ወዳንተ : ልካኝ : ነበር። አንተ የምድርና ፣ የሰማይ : ጌታ : ሆይ : ቸኮሌት : ላክልኝ ብልሀለች።

ከጥሪው : መዝብ : ሳሟ :ሳይሰፍር : ወደኔ መታ የነበረችው : ማያዬን አወካት?

ለነገሩ : አንተ : ብታቅም : አላቅም :ከማለት : ወደኃላ አትልም...... ብቻ እሷ ታቅሀለች።

በቃና : ዘገሊላ :ግዜ : ውሀውን : ወይን : ጠጅ : አድገህ : ነበር : በሰው : ሰርግ : እንደዚ : የሆክ : በራህ : ሰርግ : እንዴት: ትሆን?
በስቅለትህ : ወቅት : ጎንህን : ሲወጉህ : ውሀ፣ ደም፣ ወተት : ፈሶህ ነበር ።

በመጀመሪያ :ቀን : ማያዬን : ሳገኛት : ውሀ ጠጥታ ነበር ።
በሁለተኛው : ቀን : ስንገናኝ : በተፈጥሮ : ደም እየፈሰሳት :ነበረ ።
በሶስተኛ : ቀን : ፈጣሪ : ቸኮሌት : በኔ : በኩል እንዲልክላት : ጠይቃኝ ነበር።

በቸኮሌት: ውስጥ : ወተቱን : ለማግኘት :ፈልጋለው ይሆናላ....


ቸኮሌቷን : አንድቀን : ይዤላት: እንምመጣ :ታውቅ ይሆን?

አታውመቅም.........

የእግዚአብሄርን : ልጅ : ሰርግ : አይቼ : ከድግሱ : በልቼ ጠጥቼ : መሞቴን : እንኳን : አታውቅም..........


አዎ አታውቅመም.....

አደራ
**ንገሩልኝ******

ሱራፌል ጌትነት (ሱራ ቢራቢሮ)

የግማሽ አለም ጣኦት

@wegoch
@wegoch
@wegoch