Get Mystery Box with random crypto!

‹‹እንዴት ነው ግን ከዚያስ በኋላ አንድ ሰው እንኳን ወይም የከተማው አስተዳደር ራሱ በግድም ቢሆን | ወግ ብቻ

‹‹እንዴት ነው ግን ከዚያስ በኋላ አንድ ሰው እንኳን ወይም የከተማው አስተዳደር ራሱ በግድም ቢሆን ወስዶ የወሊድ መቆጣጠሪያ የማያስደርግላት…! አሁንስ ቢሆን ምንድን ነው ዋስትናዋ በድጋሜ እንደማይደፍሯት?›› ብዬ ፈርጠም ብዬ ጠይቄ ነበር፡፡ አሁንም ያቺ ደግ አክስቴ ያደረገችውን ነገረችኝ፡፡ ‹‹አይ በልዬ… እሱማ ከዚያ በኋላ እንደምንም ብዬ ይሄ ክንድ ላይ የሚቀበረውን የ4 ዓመት የወሊድ መከላከያ አስደርጌላት ነበር፡፡ የሆነ ቀን ራሷ ቆፍራ አወጣችውና ጣለችው፡፡ ይኸው ይግረምህና… አሁንም ነፍጠ-ጡር ነች… ፈጣሪ የስራውን ይስጠው እንዲህ ያደረጋትን እንጂ ምን ይባላል…›› ብላ በቁጭት ተነፈሰች፡፡ እብዷ አሁንም ሁለተኛ ነፍሰ-ጡር ነች፡፡ ይህንን ስሰማ እንዴት እንደነዘረኝ የማውቀው እኔ ነኝ፡፡

"ጨርሰናል"

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun abebe