Get Mystery Box with random crypto!

ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በ | ወግ ብቻ

ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጀ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ አስተማሪውን "አስታወስከኝ ወይ?" አለው።አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" አለው፤ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ፤ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር።እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ሄዶ ይናገራል፤አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፍታችንን ወዴ ግድግዳ ኣዙረን እንድንቆም አዘዝከን።በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤የሚገባበትን አጠሁ።አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ሲሆን፤ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርግቴን ስሰሙ።በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ስገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤በቃ መጥፎ ዜናው ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ።ፍተሻውም ስያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን።እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ።በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠራ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤አንተም ምንም ብለሃኝ አታውቅም።እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬ እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው።አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

# NB በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል።እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ግጥም አብዮት