Get Mystery Box with random crypto!

#ወግ_ብቻ #ናፍቆትህ ናፍቆኛል. . ትዝታዬ . ' . . . ወሰን አልባው ፍቅርሽ ፣ | ወግ ብቻ

#ወግ_ብቻ

#ናፍቆትህ ናፍቆኛል. .
ትዝታዬ
.
" . . . ወሰን አልባው ፍቅርሽ ፣ ጠብቆኝ
በስስት ፣ አድርጎኛልና መንገዴን እንዳልስት።

ለአንኳኳለት ሁሉ ልቤ አይከፈትም ፣
እንኳንስ አካሌ ሃሳቤ አይሸፍትም።. . . ..
. . . "

ይኼን ሙዚቃ እንደ ዛሬ ብቻዬን ሳልቆዝምበት በፊት………ጮክ ብለን ዘፍነነዋል . . . ተለጣጥፈን አዳምጠነዋል. . . ተገባብዘነዋል. . . ትዝታ ፅፈንበታል. . . . .

ያኔ ……

ጥር ከመግባቱ በፊት ሳውቀው. . .

"ምወደው ጫካ አለ" አለኝ የመጀመርያ የአብሮነት ምሳችንን እየበላን ነበር. . .

"ትወስደኛለህ "

"ከፈለግሽ ደስ ይለኛል "

ካለንበት ዕሮብ ለቀጣዩ ዕሮብ አቀድን. . .

ፍቅሩን አንዴ ነው የጠጣሁት ለዚህም ነው አሁንም እንደ አማልክት ምኖረው. . .

የዓለምን ምስጢር የገለጠልኝ እውነት ነበር. . . ሚሆነውም እሱ ነው. .

አስፈሪው ጫካውን ሲያሳየኝ አልፈራውም ፣ አልደነገጥኩም. . . . አልተጨነኩም. . . . ነፍሴ ስትዘል . . . ስታመሰግን አየዋት . . . ያኔ ነው ያፈቀረችው መሰለኝ . . አክብራው ስታጎነብስ አይቻታለው. . . ነፃነቷን ሰቷት ነበር እና. . . .

ከዛ ቀን በኃላ ከንፈናል . . . ያለሱ ሚታየኝ ውበት፣ የሚጣፍጠኝ ስም አጣው. . . በረርኩ . . ልቡ ውስጥ ፣ ነፍሱ ውስጥ ፣ አዕምሮው ውስጥ . . በፍቅር ፈቀደልኝ. . .

ለኔ ደክሞት ፣ሰንፎ አያውቅም. . . ያፈቅረኛል!!
ፍቅሩን መላው አካላቱ ይናገራሉ. . .


ሊመሽ ሲል ከመለያየታችን በፊት መንገድ ዳር ሻይ እንጠጣለን. . . እኔ ችፕስ ወዳለው . . . እሱ ጨጓራውን ያመዋል . . . ቢሆንም ይበላልኛል. . .ቦታውን ወዶት እኮ አደለም ሚቀመጥልኝ እኔ ስላልኩት ነው. . . .

ማይወደውን ፣ ማይፈልገውን ሁሉ ለኔ ፣ ለፍቅራችን ሲል ፈልጎት ነበር . .

* * *


ዛሬ…………

ደክሞት ፣ ደክሞኝ ጠፍተናል. . . የዘረጋነውን እውነት በመቆሳሰል ደብቀነዋል. . . ያቀፈኝ ክንዱ ተሰብስቦዋል ፣ ጥጉ ፣ ጥጌ ላይ ነኝ. . . ህልሞቻችን ከቀኖቻችን ጋር ተኳርፈዋል . . . የራሱ ልብ ውስጥ ፣ የራሴ ነፍስ ውስጥ ተወታትፈናል. . . . ደምኖብናል . . .

እራሴን ጠይቃለው " ፍቅራችን እውነት አበቃ ?"

ይቆጨኛል. . . ሚቆጨኝ ስለሌለ ሳይሆን ያልነገርኩት ስላለ ነው. . .

"ያልኖርኩልክ የቀረኝ ሂወት አለኝ. . . ያላሳየሁክ ያልሆንኩልክ እውነት አለኝ ፣ ውሃን ልወልድልህ ፈልጋለው ፣ እስከ እድሜዬ አመሻሽ አንተን ነው ምፈልገው ፣ እንደ ደነስናቸው ዳንሶች ፣ እንደነበሩን ፀሃይና ጨረቃ ፣እደተሳሙት ከንፈሮቻችን ፣ እደተራመድንባቸው ጓዳናዎች ፣ እዳለቀስንበት ምሽት ፣በጅብ እንደፈራንበት ቀን ፣ እንደ ደበደበን ዝናብ ፣ እዳቃጠለን ሀሩር ፣ እንደ ጉርሻችን ፣ እንደ ሰጠከኝ አበቦች . . ተው ትዝታ አንሁን . . " ልለው ፈልጋለው!

"ከአንተ ጋር የአንዲት ሰዓት ሐሴት ዘላለማዊ ውድ ቅርፅ ነው።. . . ፍቅራችን ከዘመናት በፊት የጠፋውን ማሙዝ እንዲሆን አልፈልግም. . . የሳትነውን መንገድ እንመለስበት፣ ኑርልኝ፣ ልኑርልህ ፣ ና ፣ ልምጣ " ልለው እፈልጋለው

. . . . ግን አልለውም

አንዳንድ እውነቶች መነገር አይፈልጉም ፣ ቁጭትን እየወለዱ ቢሆን እንኳን በመደበቅ ይፀናሉ. . .

ቢሆንም ናፍቆትህ ዝም ብሎ ይናፍቀኛል ፣ ናፍቆ ያሰኘኛል. . . እንዳልመጣም ፣ እንድመጣም
ይመክረኛል!!

/ትዝታ /


|❀:✧๑♡๑✧❀|

@wegoch
@wegoch
@wegoch