Get Mystery Box with random crypto!

ናብ ከአልጋ አላላቅቅ ብሏት ተኝታለች። ሰዓቱን ስትመለከት ሶስት ሰዓት ገደማ ስለሆነ እንደምንም ብ | ወግ ብቻ

ናብ ከአልጋ አላላቅቅ ብሏት ተኝታለች። ሰዓቱን ስትመለከት ሶስት ሰዓት ገደማ ስለሆነ እንደምንም ብላ ተነስታ ወደ
ማርያም ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ሳያልቅ ለመድረስ ተጣድፋለች። በዚያ ላይ
ከልጆቿ መካከል አራቱን የወለደችው በባለወልድ ቀን ስለሆነ ለባለወልድ የተለየ ስሜት አላት። "አዬ የኔ ጉድ፣ ለዛውም በባለወልድ ቀን እንዲህ ላርፍድ?" እያለች ነጠላዋን ተከናንባ ከወጣቷ ልጇ ሚሚ ጋር አውራ መንገዱን ተሻግረው ወደ ማርያም የሚያስገባውን መንገድ ሲጀምሩ ከአንድ ግቢ ውስጥ የሚጮኹ፣ የሚንጫጩ፣ የሚተራመሱ ሰዎች ሲመለከቱ በድንጋጤ እየተጣደፉ ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሁለቱም በአይናቸው ያዩትን ማመን አልቻሉም…
÷÷÷

ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Tilahun abebe