Get Mystery Box with random crypto!

"ቃለ እግዚአብሔር "

የቴሌግራም ቻናል አርማ kaleegziabeher — "ቃለ እግዚአብሔር "
የቴሌግራም ቻናል አርማ kaleegziabeher — "ቃለ እግዚአብሔር "
የሰርጥ አድራሻ: @kaleegziabeher
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.12K
የሰርጥ መግለጫ

"ጥበብን ማግኘት ምንኛ ከወርቅ ይሻላል! ማስተዋልንም ማግኘት ከብር ይልቅ የሚመረጥ ነው።" ምሳ 16
"ሥጋችን ምግብ ሲያጣ እንደሚደክም ሁሉ ነፍስም ምግቧን የእግዚአብሔርን ቃል ስታጣ ትደክማለች።" - ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ

በመንፈሳዊ ህይወት ዙሪያ ጥያቄ ካላችሁ ለመምህራችን በ @henokasrat3 መላክ ትችላላቹ።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-19 08:51:04 ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ

ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/Dnabel
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
1.1K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 00:24:31 ​ደጉ ሳምራዊ ሆይ እንደ መንገደኛው በወደቅሁበት በረሃ ማለፍህን እየተጠባበቁ አሁንም በኢያሪኮ ጎዳና ቁልቁለቱ መካከል ላይ ነኝና አትለፈኝ፡፡ ጌታ ሆይ ከእኔ ተሽለው ያልወደቁት ቢያዩኝም ትተውኝ አለፉ እንጂ ሊያነሡኝ አልቻሉም፡፡ እንደ ቀደሙት መንገደኞች ፈርተው አይመስለኝም፡፡ ይልቁንስ ሸተተን ብለው ሳይሆን አይቀርም፡፡ ደጉ ሳምራዊ ሆይ መበላሸቴ እውነታቸውን ነውና እባክህን አንተ ወደእኔ ተመለከት፡፡ ከወደቅሁበት ዛሬም አንሣኝ፡፡ እንደ ወንጌሉ በፍጹም ትሕትናህ በአህያህ ላይ ጫነኝ፡፡ ሰው መሆንን ወድደህ ሰው አለመሆንን ጠልተህ ስለእኔም ጭምር ሰው ሆነህ እንደ አህያ ደካማ የሆነ ባሕርያችን ገንዘብ አድርገሃልና ከወደቅሁበት አንሣኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ ስለእኔ ሰው ሆነሃልና በፈቃዴ ከሰውነት ባሕርይ ተራቁቼ ከእንስሳነትም ወርጄ በጠባዬ አውሬ የሆንኩትን እኔን ለሰውነት መዓርግ አብቃኝ፡፡

ናከደበነፆርን ግብሩን አይተህ አረአያውን ለውጠህ አውሬ ካደረግኸው በኋላ ወደስውነነት እንደመለስከው እኔንም በጠባዬ አውሬ የሆንኩትን ስለእኔ ሰው መሆንህን አስበህ ለሰውነት አብቃኝ፡፡ ስለእኔ በበረት ራቁትህን በብርድ ተወልደሃልና፤ የኃጢአት ብርዴን አርቅልኝ፡፡ ስለእኔም ጭምር ብለህ በከብቶች እስትንፋስ ተሟሙቀሃልና፤ በሙቀተ መንፈስ ቅዱስ እኔን ከኃጢአት ብርድ አላቅቀኝ፡፡ ስለእኔ ቅጠል ለብስሃልና አውልቄ የጣልሁትን ወንበዴዎቹም የዘረፉኝን የልጅነት ልብሰ ጸጋዬን መልሰህ አልብሰኝ፡፡

ጌታዬ ሆይ የጠፋነውን ወደመንጋህ ለመመለስ አንተ ስለእኛ ተሰደሃልና አቤቱ እኔን መልሰኝ፡፡ የጠፋ በግህን ከቅዱሳን ኅብረት ከቅድስና ጉባኤህ ከመንጋህ ደርበኝ፡፡ እንርሱን አንድ ጉባኤ አንድ አካል ላደረገ ለቅዱስ ሥጋህና ለክቡር ደምህም አብቃኝ፡፡

ጌታዬ ሆይ አቤቱ በአዲስ ዘመን ዋዜማ በአጠገቤ እለፍና አንሣኝ፡፡ ዘይትና ወይን ባልካቸው የመሥዋዕት ደምህ ቁስሌን ጥረግልኝ፡፡ ጨርቅ በተባለ ፍቅርህም ግጥም አድረገህ እሰርለኝና ከጥላቻ፣ ከከንቱነት፣ ከግብዝነት፣ ከለፍላፊነት፣ ከኩራትና ከትዕቢት፣ ከዝሙትና ከርኩሰት ቁስሌ ማገገምን ስጠኝ፡፡ በአገልጋይህ በኩል ስበህ የእንግዶች ማደሪያ ወዳልካት ቤትህ አስጠጋኝ፡፡ ጌታዬ ሆይ እባክህን ለእኔ ለምስኪኑ ዛሬም ዲናርህን ክፈልልኝ፤ አቤቱ ሁለቱ ዲናሮችህ በተባሉ በብሉይና በሐዲስ እጅግ የደከመች ቁስለኛ ነፍሴን መግበህ አድንልኝ፡፡

የነፍሴ እረኛ ሆይ በአንተ ዘንድ ዝለት መሰልቸት የለምና የእኔ መቅበዝበዝ አይተህ ቸል አትበለኝ፤ ጠባቂዬ ሆይ በኃጢአቴ ምክንያት ካገኘኝ ደዌ ሥጋ ደዌ ነፈስ ፈውሰህ ሰው አድርገህ አቁመኝ፡፡

ስለእኔ የእሾህ አክሊል የደፋኸው ጌታ ሆይ የአንተ ራስ ስለእኔ ተወግቷልና ኅሊናዬን ከሚወጋኝ የሀሳብና የኃጢአት እሾህ አድነኝ፡፡ በውኑ አንተ ለእኛ ብለህ ካልሆነ በከንቱ ተወግተሃልን? ስለዚህ ጌታ ሆይ ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆሜ እየጸለይኩ እያስቀደስኩ ሳይቀር እሾህ ነገር እያሰወጋ ከሚያቆስለኝ ክፉ ሀሳብ ስለደፋህልኝ የእሾህ አክሊል ብለህ እኔን አድን፡፡ አቤቴ እረኛዬ ሆይ በዘመነ ሥጋዌህ ኃጢአትህ ተተወልህ፣ ኃጢአትሽ ተተወልሽ እንዳልካቸው ኃጢአትህ ተትቶልሃል የሚለውን ድምጽህን አዲሱ ዘመን ከመግባቱ በፊት አሰማኝ፡፡ የልጆችን ለውሾች መስጠት አይገባም እንዳልካት ሴት ፈውስ ባይገባኝ እንኳ ጌታ ሆይ ውሾችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ ስትለህ እምነቷን አይተህ እንደፈወስክላት እኔንም በእምነት ፍጹማን ከሆኑት የተረፈውን የፈውስ ፍርፋሪ አቅምሰኝ፡፡ ቤዛዬ ሆይ ስለእኔ ተገርፈሃልና በመገረፍህ ቁስል ፈውሰኝ፡፡ በሙሴ ፊት ብርሃን በሳልከበት በአንተ ፊት ላይ አይሁድ የረከሰ ምራቃቸውን ሲተፉብህ የተጋሰከው ቤዛዬ ሆይ ዛሬም እኔ በየቀኑ በአንተ ፍጡር ላይ የምተፋውን አይተህ አላጠፋኸኝም፣ ነገር ግን ርኩሱን ምራቅ በብርሃናዊ ፊትህ ላይ ስለመቀበልህ እኔን ከርኩሰቴ አንጻኝ፡፡

አንተ ስለእኛ ስለሁላችን ተከሰህ በጲላጦስ ፊትህ ቀርበህልናልና አቤቱ ጌታ ሆይ እኛ ስለኃጢአታችን አንከሰስ አንወቀስ፤ በአንተ መከሰስ እኛ እንፈወስ እንጂ፡፡ ጌታ ሆይ ስለአንተ መንገላታታ የምእመናን መንገላታት ይበቃ፡፡ ስለአንተ መናቅ እኛ በድነቁርናና ባለማሰብ፤ ባለማቀድና ባለመሥራት የገጠመን መናቅና መገፋት በአዲሱ ዐመት ይከልከልልን፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ መስቀል ተሸክመህ ሦስት ጊዜ ወድቀሃልና፣ በግል በሠራነው ኃጢአት ከወደቅንበት ውድቀት፣ እንደተቋምም ተሰነካክለን ከወደቅንበት አዘቅት፣ የአባቶችን ገድልና ትሩፋት ይዘን ስለወደቅንበትም ታሪካዊ ውደቀት የአንተ መውደቅ ቤዛ ሆኖን እንነሣ፤ አቤቱ አንሣን፣ ቀጥ አድርገህም አቁመን፡፡ ተነሣ አልጋህን ተሸክመህ ተመላለስ እንዳልከው፤ ተነሡ ወንጌል እውነት ይዛችሁ፣ የተኛችሁበትን የታሪክ፣ የገድልና የፍቅር አልጋ ይዛችሁ በአገልግሎት ተመላለሱ ብለህ በኃጢአትና በድከመት የሰለሉ እግሮቻችንን አጽና፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ ተቸንከረሃልና ከተቸነከርንባቸው የጎሰኝነት፣ የድንቁርና የጥቅመኝነትና የአድሎ ችንካሮች አልላቀን፡፡ አቤቱ ጌታ ሆይ ስለእኛ የሆምጣጤውን መራራ ጽዋ ቀምሰሃልና በምትኩ ከፍቅርና ከይቅርታ፣ ከዕወቀትና ከምሕረት ጽዋ እኛን አቅምሰን፡፡ ሳይገባህ ስለእኛ ተገንዘህ ተቀብረሃልና አቤቱ ከድንዛዜ መግነዝ ፍታን፣ ከጥልቅ የድንቁርና መቃብርም አውጣን፡፡ ስለ ልዩ ትንሣኤህ ትንሣኤ ልቡና ወኅሊና አድለን፡፡ ስለ ቅድስት ዕረገትህም ዕርገተ ኅሊናና አልዕሎ ልቡናን አሳድርብን፡፡ ስለ ዳግም ምጽአትህም በቀኝህ የሚቆሙ ወዳጆችህ የሚሠሩትን ምግባረ ሃይማኖት ለመሥራት አብቃን፡፡

ጌታ ሆይ በዚህች በዿግሜ ኢዮብን በዮርዳኖስ ወንዘህ አጥበህ እንደፈወስነው እኛን ኢትዮጵያውያንን ከሚያጸይፍ ቁስለ ነፍሳችን ፈውሰን፡፡ እጠበን እንጠራለን፤ አንጻንም እንነጻለን፡፡ ጌታ ሆይ ስለእኛ አይደለም መምጣትህን አስቀድመው ይነግሩ ዘንድ ስለነገርሃቸው አርእሰተ አበውና ነቢያት፣ መርጠህ አስተምረህ ሾመህ ዐለምን ወደአንተ ይመልሱ ዘንድ መስቀል መከራ ሞትን አሸክመህ ስለላክሃቸው ሐዋርያት፣ ኑፋቄ ዘርቶ መንጋውን ከአንተ ለመለየት የተጋውን የዲያብሎስን ሽንገላ ተቃውመው ሃይማኖትን በንጽህ ስለጠበቁ ሊቃውንት፣ ፍትወታትን ድል ነሥተው በተጋድሏቸው ያለደም መፍሰስ ሰማዕትነትን ስለተቀበሉ ጻድቃን፣ የነገሥታትን ማስፈራራትና የሚያደርሱባቸውን መከራ ሳይሰቀቁ ነገሥታተ አሕዛብን ድል ስለነሡ ሰማዕታት፣ በንጽሕ እና በትጋት ሆነው ያለመታከት አንተን ስለሚያገለግሉ ሊቃነ መላእከትና ሠራዊተ መላእክት ብለህ ይልቁንም ደግሞ ከሁሉም በላይ ስለሆነች ከእርሷ ሰው ትሆን ዘንድ ስለመርጥካት የንጽሕና መሠረት የባሕርየ አዳም መመኪያ ስለሆነች ስለንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል እናትህ ብለህ ጌታ ሆይ በወደቅሁበት አዘቅት እለፍና እኔን ምስኪኑን ቁስለኛ የዲያብሎስ ምርኮኛ ከወደቅሁበት አንሣኝ፤ በሚቀጥለው ዐመትና በመጪዎቹ ዘመናትም አንተን በመከተል ሕግህን በመጠበቅና ፈቃድህን በመፈጸም አንሣኝ፡፡ ለፈቃዴ አሳልፈህ አትሰጠኝ፣ ይልቁንም ለፈቃድህ የምገዛበትን ልቡና ሥጠኝ፡፡ አቤቱ አትተወኝ አትጣለኝም፣ አሜን፡፡

ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ

@KaleEgziabeher
1.9K views21:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 00:23:37

ከዲያቆን ብርሃኑ ሳታነቡት አትለፉ

አቤቱ በእኔ በኩል እለፍ ፡፡

ጌታ ሆይ በኢያሪኮው መንገደኛ በኩል እንዳለፍህ ይህች ዐመት ከማለቋ በፊት እባክህን በእኔም በኩል እለፍ፡፡ የጠፋውን በግ አዳምን የፈለግኸው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ እኔንም ፈልገኝ፤  ባገኘኸውም ጊዜ እንደተሸከምኸው እኔንም ተሸከመኝ፡፡ የቀደመ ፍጥረትህን አዳምን ቸል እንዳላልከው ከእርሱ አብራክ የተገኘሁ እኔ ደካማ ልጁንም  ቸል አትበለኝ፡፡ ይልቁንም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንድ ሰው የተባለ አዳምን እንደተሸከምከው እኔንም ተሸከመኝ፡፡
አዎን ጌታ ሆይ በመንገድ ላይ የወደቀው ስም የለሽ አንድ ሰው እኔ እንደሆንኩ አውቂያለሁ፡፡ ከኢየሩሳሌም ልዕልና ነፍስ ወደ ኢያሪኮ የኃጢአት ቁልቁለት የወረድሁት እኔ እንደሆንኩ ገብቶኛል፡፡ አንተ ለእኔ ድኅነት የሠራኸውን አሸቀንጥሬ ጥዬ እኔን ካስቀመጥክበት ከፍታ ተንደርድሬ ለእኔ ፍላጎት ወደሚስማማው ቁልቁለት የወረድሁት በወንበዴዎች እጅም የወደቅሁት የኢያሪኮው መንገደኛ እኔ ነኝ፡፡ በምሥጢራት ከሚኖርበት ተግባራዊ የክርስትና ከፍታ በማስመሰልና በውድድር ወደሚኖርበት ዝቅታ የወረድሁት ስም የለሽ መንገደኛ እኔ ነኝ፡፡ በእውነትና በፍቅር ከሚኖርበት የወንጌል ተራራ ጥቅሶችን ወደፍላጎታችን ወደሚለጥጥ ገደል የወረድሁት የተመታሁ መንገደኛ እኔ ነኝ፡፡ አንተን በሕይወቴ አሳድሬ አንተ በእኔ እንድትሠራ ከሚያደርግ ከፍታ እራሴን ለአንተ የሚሠራ ወታደር ወደሚያስመስል የሕይወት አዘቅት አውርጄ የጣልኩት የቁልቁለት መንገደኛው እኔ ነኝ፡፡ ሰለወደቀው በማዘን ስለእርሱም በመጸለይ እውነተኞቹ ልጆችህ ከኖሩበት ከፍታ ሁሉንም ወደሚያስንቅና ወደሚያስተች ዝቅታ የወረድሁት መንገደኛ እኔ ነኝ፡፡ ነገሮችን በመንፈስና በአስተውሎት ከመመርመር በስሜትና በግብታዊነት ወደማበላሽበት ጉድጓድ የወረድሁትም እኔ ነኝ፡፡ በእቅድና በጥበብ ከመሥራት በትችትና በነቀፌታ በእልህና በብስጭት ወደመናገር ብቻ የወረድሁት ከንቱ በእውነት እኔ ነኝ፡፡ ጥቂቶቹን ልዘርዝር ብዬ እንጂ ጌታ ሆይ እኔ ያልተውኩት ሰገነት፣ ያልወደቅሁበትም አዘቅት ምን አለና፡፡

ስወርድ ደግሞ እንደተጻፈው ወንበዴዎቹ አገኙኝና ደበደቡኝ፡፡ የነበረችኝንም ሁሉ ቀሙኝ፡፡ ጌታ ሆይ እየወረድኩም ይዠው ከነበረው ያልቀሙኝ ምንም የለም፡፡ መጀመሪያ የቀሙኝ ስንገዳገድ የምደገፍባትን፤ አቀበት ቁልቁለት የማቋርጥባትን፤ አራዊትን የማርቅባትን፣ ሰንቅና ጓዜን የምሸከምባትን አንዷን ዘንጌን ጸሎቴን ቀሙኝና ድጋፍ አልባ አደረጉኝ፡፡ ተነሥቼ ልጸልይ ስቆም አካሌ እንደ ሐውልት ቆሞ ነፍሴን ይዘዋት ይዞራሉ፡፡ አንዳንዴ ጥርሴን ያስነክሱኛል፡፡ አንዳንዴ ስለአንተ ተቆርቋሪ አስምስለው ጦርነት ውስጥ ይከቱኛል፡፡ ሌላ ጊዜ በአንተ በኩል ማግኘት የሚገባኝን ጥቅም ያሳስቡኛል፡፡ ሌላ ጊዜ አንተ የማያስደስቱ የሚመስሉኝን እንድትቆርጥ እንድትጥል ያሳስቡኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ የተረሳ ዘመድ ወዳጅ፣ የሞተ የጠፋ ቤተሰብእ ሳይቀር እያሳዩ ተመስጦ በሚመሰል ሕይወት ውስጥ ያጃጅሉኛል፡፡ የቀረ ሥራ የከሰረ ሀብትም አሳስበው ያናድዱኛል፡፡ ብቻ ነፍሴን የማይወስዱበት ቦታ የለም፡፡ ብሞት እንኳ መልአከ ሞት ነፍሴን ሊየንገላታት የማይችለውን ያህል ነፍሴን ያንከራትቷታል፡፡ ጸሎቴን ቀምተው ነፍሴን ማረፊያ ያጣች አሞራ አስመሰሏት፡፡ ስለዚህም የውስጥ ሰላሜ ተነጠቀ፡፡ እንኳን ከሌላው ከትዳር አጋሬ ከወላጅ ከቤተሰቤ በሰላም መነጋገሬን ሁሉ አከታትለው ቀሙኝ፡፡

ትዕግሥቴን ነጥቀዉ እንደ ፍየል ለፍላፊ፣ እንደ ጉጉት ጯሂ አደረጉኝ፡፡ ለሚናገረኝ ካልመለሰኩለት፣ የሚመለከተኝን ካልገላመጥኩት የተጠቃሁ እያስመሰሉ በመልካም የመመለስ ሀብቴን ዘረፉኝ፡፡ ይባስ በለው ልዩነቴን በእወቀት ከማስረዳት፣ ለመግባባት ከመወያየት አፋትተው የተለየለት ግልፍተኛ ተሳዳቢ አደረጉኝ፡፡ አሁንማ ካልተሳደብኩ ዐለም መሸነፌን አውቆ  የሚስቅብኝ እያስመሰሉ እንኳን ይቃረኑኛል ለምላቸው በሀሳብ ይቀርቡኛል የምላቸውንም በእኔ መንገድ ስላልተናገሩ ብቻ የማላደላ ጀግና በማስመሰል እንድወርፋቸው ያደርጉኛል፡፡

ወደ ቀደመ ሕይወቴ እንዳልመለስም መንገዱን አጠሩብኝ፡፡ ጉባኤ ሔጄ እንዳልማር ጊዜ የማባክን ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ መምህራንንም በትችት ስላስናቁኝ የመቀመጥ ትዕግሥቴ ራሱ የት እንደገባ አላውቅም፡፡ በጓደኛ ተጽእኖ ስቀመጥም ለእኔ ብሎ ከመስማት ይልቅ ይህ ለእነ እገሌ ነበር የሚያስፈልግ ያሰኘኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዛሬም ይህን ይሰብካል እንዴ ያሰኘኛል፡፡ እኔ በማዘወትረው ኃጢአት ሳላፍር መምህሩ የሚታወቅ ትምህርት አስተማረ ብሎ አያፍርም ወይ ያሰኘኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚነገረውም አሽሙርና የማይረባ ያስመስልብኛል፡፡ እዚህ ከምማር በቃ ቤቴ ተቀምጬዬ አነብባለሁ ብሎ ካስተዋኝ በኋላ ቤቴ ስገባ ቴሌቪዥን ጋር ያፋጥጠኛል፡፡ እርሱ ሲሰለቸኝ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ የወጣ ነገር እንድመለከት በጓደኞቼ በኩል ያስደውልብኛል፡፡ እንደምንም ታግዬ ላነብብ ስነሣ እንቅልፍ እንደበረዶ ያዘንብብኛል፡፡

በቃ በጎው ነገር ካመለጠኝ በኋላ አልያዝ አልጨበጥ አለኝ፡፡ ምክር እንዳልጠይቅ ትልቅና አዋቂ ሰው ነው በሚባል የገጸ ባሕርይ ካባ ሸፍነው አሳፍረውኛል፡፡ ከዚህ ሁሉ የተነሣ በነፍሴ ሕመም ሥጋዬም ታማሚ ሆነ፡፡ እንደወፈረኩ ደከማ፣ እንደጠገብኩ ልፍስፍስ አደረጉኝ፡፡ እንዳልጾም ሰውነቴ ሁሉ እንቢ አለ፡፡ እንዳልሰግድም ጉልበቴ ሁሉ ተብረከረከ፡፡ በሁሉ ባዶ ሆኜ ቁጭ አልኩ፡፡

የነፍሴ መድኃኒት ጌታዬ ሆይ አፍ ማብዛቴን፣ ነገር መውደዴን አይተህ ነው መሰል አፍን በማስክ የሚያስይዝ የተግሣጽ ደዌ ብታመጣም የእኔ ነፍስ ግን አሁንም አላስታዋለችም፡፡ እጆቼ ማስኩን አፌ ላይ ቢያደርጉም ምላሴን ሊያስቆሟት ግን አልቻሉም፡፡ አንተ ለደቀመዛሙርትህ እንዳልከው አፍን የሚያረክሰው ከውጭ የሚገባው ሳይሆን ከውስጥ የሚወጣው ነውና ከነፍሴ ቁስል የተነሣ በአፌ የሚወጣው የነገር ጠረን አካባቢውን አሸተተው፡፡ እንኳን ለሌላው ለእኔም እየተሰማኝ ቢሆንም ነፍሴን የደበደቧት ወንበዴዎች ግን እንድነቃ አልፈቀዱልኝም፡፡ ስለዚህ ጌታ ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልብና የኅሊና ማስክ እዘዝልኝ፡፡ እንደ ዳዊት ወዳጅህ ለአፌ ጠባቂ ሹምለት፤ ከንፈሮቼንም እንደ ቤተ መቅደስህ በር በምሕረትና በእውነት የሚከፈቱ አድርግልኝ፡፡ ጌታ ሆይ አሁን ችግሬ ገብቶኛል፤ ማስክ የሚያስፈልገኝ ለውጨኛው ሳይሆን ለውስጠኛው የኅሊና አፌ ነው፡፡ ጸረ ተሐዋሲ መድኃኒትም ከሥጋዬ ይልቅ ለነፍሴ እጆች እንደሚያስፈልጋቸው ገብቶኛል፡፡ አቤቱ ሰነድ በመደለዝ፣ ደም በማፍሰስ የረከሱ እጆቻችን በምን ይነጻሉ? የሐሰት ትርክት በመተረክ፣ የበለው ግደለው ቅስቀሳ በመጻፍ የዋሆችን በማነሣሣት ደም ያፈሰሱ የምሁር እጅ ነኝ የሚሉ የነፍስ እጆቻችንስ ቤትኛው ሳኒታይዘር ይነጻሉ? ጌታ ሆይ ዘንድሮ ሁሉንም ችግሮቼን ነግረኸኛል፡፡ በተለይ ርቀት ያለመጠበቅ፣ ቦታዬንም ያለማወቅ ችግር አስታውሼው አላውቅም ነበር፡፡ የእኔማ የተለየ ነው፡፡ እንኳን በሾምካቸው በጳጳሳት በካህናት በአንተ ወንበር ተቀምጬ ስፈርድ፣ ስገድል ሳድን፣ ስሰጥ ስነሣ ነው የኖርኩት፡፡ በወንጌል አልገባ ቢለኝ በበሽታ አስመስለህ ርቀትህን ጠብቅ ብትለኝም ልመለስ አልቻልኩም፡፡ ግን ወድቄያለሁና ተነሥቶ መቆም ርቀቴንም መጠበቅ እንዳይቻለኝ ደርገው ወንበዴዎቹ አጋንንት ስወርድ አግኝተው ደብደበውኛልና ተመልሶ መቆም ተሣነኝ፡፡
1.5K views21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 13:11:25 መንፈሳዊጉባኤ አባላት በሙሉ ልበ አምላክ ዳዊት “በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ፤ ምድረ በዳውም ጠልን ይጠግባል” (መዝ.፷፬.፲፩) በማለት እንደ ዘመረው ቸርነቱ ወሰን የሌለው አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን በሰላምና በጤና አሸጋገረን። እጅ ለእጅ ተያይዘን በመተባበር ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ለመፈጸም ራሳችንን የምናዘጋጅበት፣ በአንድ አሳብ አቅደን በመሥራት፣ “ዘመኑን ዋጁ” ተብሎ የተነገረንን በተግባር ለመፈጸም የምንዘጋጅበት ዘመን ያድርግልን


"የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኃጢኣት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምወዳችሁ መንፈሳዊ እህትና ወንድሞቼ በቸርነቱ ስላደረሰን አዲሱ አመት በማስቀደስ አምላካችንን ምስጋና እናቅርብ
እህት ውንድሞቼ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በውስጥ መስመር እንኳን አደረሰን እንባባል ውስጥን ያድሳል
አዲሱ አመት አምላክ የውስጣችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ ከልቤ እውዳችኃለው



መልካም አዲስ አመተ
665 views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 06:42:40 በ2014 ዓ.ም የትኛው ተራ ቁጥር ነው ውስጥህን ውስጥሽን ንስሀ ሳንገባ ወደ2015 ዓ.ም እንደሂሳብ የዞሩት ኃጢያት የትኞቹ ናቸው እስቲ በግል በውስጥ መስመር እናውራበት ከካህናት ጋር መፍቴ እንፈልግላቸው
1 ቅንነት አለመኖር
2.ፍቅር አለመስጠት አለመቀበል
3.ትህትና ልቤውስጥ አለመኖር
4.መንፈሳዊ ህይወት ማጣት
5. መንፈሳዊ ስሆን የማይመጥነኝ ቦታ መገኘት
6.ግትር አውቃለው ባይ መሆን
7.ተንኮል ማሰብ እና መተግበር
8. ዝሙት በመስራት መኖር እና እንደ ጽድቅ መቁጠር
9 ሌባ ሳልባል ግን ሌባ መሆን
10.ንስሀ አለመግባት
11 መዝፈን መጨፈር እና መንፈሳዊ መሆን ማጣመር
12 የፈጣሪን ስም እየጠሩ ማጭበርበር
13.በትዳር ላይ መዘሞት እንደትክክል መቁጠር
14 ለትዳሩ ወይም ለትዳሯ የማትመች
15.ለሰይጣን ልብን መክፈት
16.ወላዋይነት
17.ንስሀ አባትን ለራስ ጥቅም ማመቻቸት
18 .አስራት አለማውጣት
19.ንስሀባት አለመያዝ
20 በሁሉም ሀጢያት ውስጥ መኖር
21 ስስት በልብ ውስጥ ማደግ
22 ንስሀን እየገቡ ሀጢያትን መደጋገም
23 ጸሎት ለመጸለይ መቸገር (ከጸሎቱ ይልቅ የውስጥ ሀሳብ ማየል)
24 ሁሌ ንስሀ አባት ጋር መሄድ ንስሀ መግባት በህይወት ለውጥ አለመኖር(አለመቁረብ)
25 ቅዳሴ አለማስቀደስ (ቤተክርስቲያን አለመሄድ)
ሌላም ሌላም ባንቺ ባንተ ውስጥ የትኛው ተራ ቁጥር ተቸገርክበት በውጥ መስመር ግለጹ አምላክ ከምንሰራው በደልና ኃጢያት ይገላግለን በአዲሱ ዓመት
801 views03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 18:24:02 ​#ሩፋኤል
#ጳጉሜ_3

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወርኀ ጳጕሜን የዓለም ፍጻሜ መታሰቢያ ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ በዚህ የተነሣ ምእመናን በጾምና በጸሎት (በሱባዔ) ያሳልፏታል፡፡ በተለይም በቅዱስ ሩፋኤል ዕለት ሰማያት የሚከፈቱበት (ርኅዎተ ሰማይ) መኾኑን በማመን ምእመናን ጸሎታቸውን ከምንጊዜውም በበለጠ ያቀርባሉ፡፡ ወደ ወንዞች በመሔድና በሚዘንበው ዝናብ ይጠመቃሉ፡፡ ወርኀ ጳጕሜን የጌታችን ምጽአት የሚታሰብባት በመኾኗ የሚዘመረው መዝሙር፣ የሚነበቡ ምንባባትና ቅዱስ ወንጌሉ እንደዚሁም የሚሰበከው ምስባክ ይህንኑ ምሥጢር የሚያሳዩ ናቸው፡፡

በወርኀ ጳጉሜን ከሚታሰቡ እና ከሚከበሩ በዓላት መካከል በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል በዓሉ የሚከበርባቸው ምክንያቶችም ሁለት ናቸው፤ እነርሱም አንደኛው በዓለ ሢመቱን ምክንያት በማድረግ ሲኾን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤቱ ነው፡፡ ‹ሩፋኤል› የሚለው የስሙ ትርጓሜ ‹ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ› ማለት ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያለ ማቋረጥ ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት አንዱ ነው፡፡ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› እንዲል (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቍስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ ‹‹በበሽታ ዅሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል (ሄኖክ ፲፥፲፫)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ‹‹በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዳለ ሄኖክ (ሄኖክ ፮፥፫)፡፡ ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው፤ ላረገዙ ሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ (ኗ በማኅፀን እያለ (ች) ተሥዕሎተ መልክዕ (በሥላሴ አርአያ መልኩ /ኳ/ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል በጥበቃው አይለያቸውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀልላቸዋል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል (ጦቢት ፫፥፰-፲፯)፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ‹‹ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው›› ተብሎ እንደ ተጻፈ (ሄኖክ ፫፥፭-፯)፡፡ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው (ሄኖክ ፪፥፲፰)፡፡ የጦቢትን ልጁ ጦቢያን በሰው አምሳል ተገልጦ ከተራዳው በኋላ ወደ ሰማይ በሚያርግበት ጊዜ ራሱን ሲገልጥ ‹‹የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነትም ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ አላቸው›› (ጦቢት ፲፪፥፲፭)፡፡

በቅዱስ ሩፋኤል ተራዳዒነት ከተደረጉ ተአምራት መካከል በእስክንድርያ አቅራቢያ በምትገኝ ደሴት በታነጸች ቤተ ክርስቲያኑ ያደረገው ተአምር አንደኛው ነው፡፡ በመጽሐፈ ስንክሳር እና በድርሳነ ሩፋኤል እንደ ተጻፈው ብዙ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈጽማ ተናወጠች፤ ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና፡፡ የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ዓሣ አንበሪው ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው፡፡ ምእመናኑም ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔር በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ ‹‹እግዚአብሔር አዝዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጥ ጸጥ ብለህ ቁም!›› ባለው ጊዜ አንበሪው ጸጥ ብሎ ቆሟል፡፡ በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገልጠዋል፡፡ ለሕሙማንም ፈውስ ኾኗል፡፡ የቅዱስ ሩፋኤል ተራዳዒነት አይለየን፡፡

በዲያቆን ዮሴፍ ይኵኖአምላክ
ጳጕሜን ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

@KaleEgziabeher
1.2K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:40:11 የስሙንም ትርጉም ስንመለከት ‹‹ሩፋ›› ማለት ሐኪም ማለት ነው፡፡ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለትነው፡፡ ሌላው መልአከ ሰላም ወጥዒና ወይም የሰላም እና የጤና መልአክ ይባላል፡፡

የሰው ልጆችን ከተያዙበት ከተለያዩ በሽታውች በጸሎቱ፣ በአማልጅነቱ እንዲፈውስ ስልጣን እና ጸጋ የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው፡፡
ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለት መሆኑን ነብየ

እግዚአብሔር ቅዱስ ሄኖክ በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 10 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በበሽታ ሁሉ ላይ፣ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ፤ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዲሁም እዛው መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 6 ቁጥር 3 ላይ

‹‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መልእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› በማለት እግዚአብሔር ለቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የወጣውን፤ ቁስል እና ደዌ፤ ይፈውስ ዘንድ ስልጣን እንደሰጠው፣ ሐኪም እንዳደረገው ነግሮናል፡፡

እንዲሁም ፈታሄ ማሕፀን ይባላል፡፡ እንኳን በምጥ የተያዙትን ሴቶች፣ እናቶች፤ ቀርቶ እንስሳት እንኳን ምጥ ሲፀናባቸው፣ ስሙን ከጠሩት ይፈታቸዋል፡፡ ይህ መልአክ በተለይ ለሴቶች እጅጉን ረዳታቸው ነው፡፡ ከፀነሱበት ጊዜ አንስቶ እስኪወልዱ አይለያቸውም፡፡

በተለይ በእርግዝናቸው ጊዜ ስሙን እየጠሩ፣ መልኩን እየጸለዩ፣ ጸበሉን እየጠጡ እየተዳበሱ፣ ከተማጸኑት ጭንቀታቸውን ያቀላል፣ በሰላም ያዋልዳቸዋል፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ስለ ቅዱስ ሩፋኤል እንዲያሳውቃቸው፣ ክብሩን እንዲገልጽላቸው ጠየቁት፡፡ ጌታም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንደሚመጡ አዘዛቸው፡፡ እነሱም መጡ፡፡

ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ስለ ራሳቸው ከተናገሩ በኃላ ጌታም ቅዱስ ሩፋኤልን ‹‹ክብርህን ንገራው›› አለው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምስጢር ነገራቸው፡፡

በተለይም ስሙን ለሚጠሩ፣ መታሰብያውን ለሚያደርጉ፣ በጸሎቱ ለሚማጸኑ፣ እንደማይለያቸው፣ እንደሚረዳቸው፣ ክብር እንደሚያሰጣቸው ለሐዋርያት ነግሯቸው ወደ ሰማያት አርጓል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም በወቅቱ ወንጌልን ሲያስተምሩ፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል ክብር እና በእሱ የሚገኘውን መልአካዊ እርዳታ፣ ለምዕመናኑ በደንብ አስተምረዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ፤ ባለ መድኃኒት ፈዋሽ፤ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው፤ በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ፤ የሰውንም ይሁን እንስሳን ማሕፀን የሚፈታ፤ አዋላጅ፣ ምጥን የሚያቀል፣ ታላቅ መልአክ ነውና እንጠቀምበት፡፡

ስለዚህ የቅዱስ ሩፋኤል ቀን የዘነበውን ዝናብ በዕቃ ቀድታችሁ አስቀምጡ፡፡ ያንንም ጸበል ቤታችሁን፣ ደጃችሁን፣ እንዲሁም የሥራ ቦታችሁን እርጩበት፣ እየቆጠባችሁ እህል ስታቦኩ አብኩበት ጠጡት ተጠመቁበት፡፡ ብዙ በረከት እና ፈውስ ታገኙበታላችሁ፡፡

እህል እና ገንዘብ የሚሰልብባችሁን የሰላቢ መንፈስ ያርቅላችኃል፡፡
ውጭ ሀገር ያላችው እህት ወንድሞቼ ጸበል መጠመቅ ስለማይመቻችሁ፤ ውኃ አቅርባችሁ፣ ያስለመዳችሁትን ጸሎት ውሃው ላይ ጸልያችሁ ‹‹አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል›› ባርክልኝ ብላችሁ ቤት ውስጥ ተጠመቁ ጠጡት፡፡

ጳግሜን መጠመቅ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የነበረ እና በየአመቱ ጳግሜን መጠመቅ የሚናፈቅ ጊዜ ስለሆነ ተጠቀሙበት፡፡ በዚሁ አጋጣሚ እኛም እንጦጦ ማርያም ጳግሜን የጸበል አገልግሎት ስለምንሰጥ መጥታችሁ መጠመቅ ትችላላችሁ፡፡

#ጳግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያትይከፈታሉ_ጸሎታችን_በሙሉ_ያርጋል፡፡

ጳግሜ ሦስት ርህወተ ሰማይ ይባላል፡፡ ርኅወተ ሰማይ ማለት የሰማይ መከፈት ማለት ነው፡፡ ይህም የሰማይ መስኮቶች ወይም ደጆች የሚከፈቱበት እለት ነው፡፡ ርኅወተ ሰማይ ወይም የሰማይ መከፈት ሲባል፤ በሰማይ መከፈት እና መዘጋት ኖሮበት ሳይሆን፤

ቅዱሳን መላእክት የሰውን ልጆች ጸሎት፣ ልመና፣ ያለ ከልካይ፤ ወደ እግዚብሔር የሚያሳርጉበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገበ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ ነው ርኅወተ ሰማይ የተባለው፡፡

በእርግጥ በንስሐ ሆኖ ለሚጸልይ ሰው ለእርሱ ሁሌም የሰማይ ደጅ የተከፈተ ነው፡፡ ከዓመት ተለይታ ጳግሜ ሦስት የሰማይ መስኮቶች፤ ወይም ደጆች በሙሉ ተከፍተው፣ የምዕመናን ጸሎት በተለየ ሁኔታ የሚያርግበት ጊዜ እንደ ሆነ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስትያንም ይነግሩናል፡፡

ስለዚህ በዚህም ቀን ማለትም ጳግሜ ሦስት ያስለመድናቸውን ጸሎቶች፤ አንዳንዶቻችንም ያቋረጥናቸውን ጸሎቶች፤ በርትተን ብንጸል ቅድመ እግዚብሔር ይደርሳል፡፡

በዚህችም ቀን የጸለይነውን ጸሎቶች፤ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅዱሳን መላእክት ቅድመ እግዚብአብሔር ያሳርጉልናል፡፡ በዚህችም እለት የእግዚአብሔር ምህረት እና ቸርነት ለሰው ልጆች የሚወርድበት ታላቅ እለት ነው፡፡

አባቶቻችን እንደሚነግሩን ከሆነ፤ ጳግሜ ሦስት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ፤ ያስለመዱትንና ሌሎችንም ጸሎቶች ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ እነሱ ማድረግ ባንችል፤ የበረታን ሌሊት ስድስት ሰዓት፤ የቻልን ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተን ጸሎት ልንጸልይ ይገባናል፡፡

#ጳግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደምታውቁት ያለንበት ጊዜ አጋንንት ተፈቶ የተለቀቀበት፣ ሰው በክፋት ከአጋንንት ያልተናነሰበት አንዳንዴም የሚበልጥበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ በተለይ ብዙ ምዕመናን በመተት በድግምት እድላቸው ተወስዶ፣ ሕይወታቸው ባዶ እየተደረገ ነው፡፡

አጋንንት ጎታቾች እና መተት መታቶች ጳግሜን በሰው ላይ የሚመትቱትን መተት የሚያድሱበት ስለሆነ ጸበል በርትተን ብንጠመቅ እድሳታቸው ይሽራል፣ መተታቸውም ይከሽፋል፡፡ ስለዚህ በዚህ በወርኃ ጳግሜ በመተት እና በድግምት የምትሰቃዩ ወገኖቼ በርትታችሁ ጸበል ተጠመቁ ጠጡ፡፡

ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ በእድላችን ሲመተት ወደ እና ሕይወት ሲጎተት የነበረው አጋንንት ጳግሜን በርትተን ከተጠመቅን አጋንንቱ አዲሱን አመት አይሻገርም፡፡

በተመተተብን መተት እና በበላነው ድግምት ውስጣችን በተለይ ሆዳችን፣ እንዲሁም መላ አካላታችን ላይ ደዌ ሆኖ የተቀመጠው አጋንንት ይለቀናል፣ ውስጣችን ያለው የደዌ መተት ይሻራል፡፡
እንዲሁም በአውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን በቅዱስ ዮሐንስ ስም አስታከው ዛር አንጋሾች፤ ለዛር ደም የሚያፈሱበት፣ የሚገብሩበት ጊዜ ነው፡፡

አዲሱን አመት ደም በማፍሰስ፣ ለዛር በመገበር ስለሚቀበሉ ጸበል መጠመቁ ከእዚህ ችግር እናመልጣለን፡፡ በተለይ ቤተሰባችሁ በቅዱስ ዮሐንስ የሽፋን ስም ‹‹ለዓውደ ዓመት ነው፣ ለአድባር ነው፣ አዲስን ዓመት ለመቀበት ነው፣ የእናት አባታችን የአያቶቻችን አምላክ እንዳይጣላን ነው፣

በአዲሱ ዓመት ጠላታችን ደሙ እንዲፈስ ነው፣ ደም የምናፈሰው የእኛን ጦስ ይዞ እንዲሄድ ነው›› በማለት ገብስማ፣ ወሰራ፣ ባለ ነጠላ ዶሮ፤ ነጭ፣ ቀይ በግ እያሉ ያረዱትን እንዳትበሉ፡፡

አውቃችሁ በዮሐንስ ስም ለዛር የተገበረለትን ብትበሉ በደም የገባውን ዛር፤ በጸበል ለማስወጣት ትቸገራላችሁ፡፡ በቤታችሁ፣ በአከባቢያችሁ እንደዚህ አይነት ክፉ ልማድ ካለ ተቃወሙ፣ ለማስተው ሞክሩ፡፡ የእነሱ እዳ ነው ነገ ለእናንተ የሚተርፈው፡፡

በተረፈ ይህችን ወርኃ ጳግሜን እንደ አባቶቻችን እንድንጠቀምባት አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል ይርዳን፡፡
754 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 07:40:11 መንፈሳዊ ጉባኤ:
Henok:
#ጷግሜን_ለምን_እንጾማለን?

#ጷግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_የምናገኘው_ጥቅም_ምንድን_ነው?

#ጷግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል፡፡

#ጷግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያት_ይከፈታሉ ጸሎታችን በሙሉ ያርጋል፡፡

/ዩ ትዩብ ላይ የለቀኩትን ትምህርት በጽሑፍ ቃል በቃል አቅርቤላችኃለሁ/

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደሚታወቀው ወርኃ ጳግሜ፤ ኢትዮጲያን ብቸኛዋ ባለ አሥራ ሦስት ወራት ሀገር ያደርገች ልዩ ወር ናት፡፡ ታዲያ ይህችህ በሦስቱ ወንጌላውያን አምስት ፣ በዘመነ ዮሐንስ በአራት ዓመት ስድስት ቀን የምትሆነው ጳግሜ፣ ብዙ ምስጢር እና ልዩ ጥቅም የላት ወር ናት፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጾማለን?

የጳግሜ ወር በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የዓለም ፍጻሜ መታሰብያ ወር ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ጳግሜ የዓመታት መሸጋገሪያ፤ ጨለማው የክረምት ወቅት፤ ወደ ማብቂያው እና የሚያልፍበት፤ እንደ ሆነ ሁሉ፤

ዳግም ምጽዓትም ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፤ ከጊዜያው ወደ ዘላለማዊ መሻጋገሪያ በመሆኑ ጳግሜ የእለተ ምጻት ምሳሌ የሆነችው፡፡ በዚህም ምክንያት የኦርቶዶክስ አማኞች የጳግሜን ወር በሱባኤ በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ፡፡ በገዳም ያሉ አባቶች ጳግሜን በዝግ ሱባኤ ያሳልፋሉ፡፡

በእግርጥ ጳግሜ ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ባትካተትም፤ ጳግሜን በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ብንጾም የበረታን ሱባኤ ብንይዝባት፣ የቻልን በታቅቦ ብናሳልፋት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡

አንደኛ በፈቃዳችን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በሱባኤ ብናሳልፍ ጸጋና በረከት ያሰጠናል፡፡ ሁለተኛው ጳግሜ የአዲስ ዓመት መቀበያ የዋዜማ ቀናት በመሆኗ፤ አዲሱን ዓመት በጾም፣ በጸሎት በሱባኤ ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት፣ የረድኤት ይሆንልናል፡፡

አዲሱን ዓመት በተለይም በዋዜማው በመዝናናት፣ በመጨፈር፣ በመጠጣት እና በመዘሞት ከምንቀበል፤ በጸሎት ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት ዓመት፣ ያሰብነው ያቀድነው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሳካበት ይሆናል፡፡

ቅድም እንዳልኩት የገዳም አባቶቻችን የጳግሜን ወር፤ መንፈሳዊ ጥቅም ስለሚያውቁ፤ በፈቃዳቸው በታላቅ ሱባኤ ሆነው ስለ ሀገር፣ ስለ መጪው አዲስ ዓመት መልካምነት ፈጣሪን ይማጸኑበታል፡፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን እና፣ እነሱ የሄዱበትን መንገድ ተከትለን፤ እንደ እነሱ ልንጠቀም ያስፈልጋልና፤ ወርኃ ጳግሜን በጾም በጸሎት እና በሱባኤ ብናሳልፍ እንጠቀማለን፡፡

በተለይ በአሁኑ ጊዜ እኛም፣ ሀገራችንም ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንም የገጠመን ፈተና፣ እጅጉን ከባድ ነውና እግዚአብሔር እንዲታረቀን፣ ገጸ ምህረቱን እንዲመልስልን፣ ወረርሽኙን እንዲያጠፋልን፣ ለቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንና ለሀገራችን ጽኑ ሰላም እና አንድነት እንዲሰጥልን ወርኃ ጳግሜን እንደ በፊቱ በመብላት በመጠጣት ሳይሆን በጾም በጸሎት ብናሳልፍ ጥቅሙ ለእኛው ነው፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

እንደሚታወቀው ብዙዎቻችን ወርኃ ጳግሜን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜን የምንጠመቅበት ዋናው ምክንያት ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር የተያያዘ ነው፡፡

በዚህ በጳግሜ ወር በዓለም ላይ ያሉ ውቅያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች ጸበሎች በአጠቃላይ ውሃዎች ሰማይ ተከፍቶ፣ በመላክእት የሚባረኩበት ስለሆነ፤ ጳግሜን የቻልን ጸበል ቦታ ሄደን፣ ወይም በአከባቢያችን ጸበል ካለ እዛም ሄደን፤ መሄድ ባይመቸን፣ ቤታችን ውስጥ ባለው ውኃ ብንጠመቅ እንባረክበታለን፣ ከበሽታችንም እንድንበታለን፡፡

በጳግሜ ጸበል፣ እንኳን የሰው በሽታ፤ በሽታ ያለው እህል፣ በሽታው ይለቀዋል፡፡ ገበሬው ከጳግሜ ወዲያ ነው የሚጠፋውንና የማይጠፋውን እህል የሚለየው፤ በተለይ ዘንጋዳ ጳግሜ ላይ ነው በደንብ የሚያስታውቀው፡፡

በአባባልም ‹‹ዘንጋዳ እና ቡዳ ከመስከረም ወዲያ›› ነው የሚያስታውቀው ይባላል፡፡ የሚገርመው አባቶቻችን ጳግሜ ሦስት ሌሊት ስድስት ሰዓት በተለይ ፏፏቴ ያለው ወንዝ፤ ውሃው ሲቆም ያዩታል፡፡

ቀድሞ አባቶቻን ይህንን ተአምር ለማየት ጳግሜ ሦስት ሌሊት በተለይ ፏፏቴ ያለበት፣ ትልቅ ወንዝ ዳር ሄደው ያድሩ ነበር፡፡ ውሃው ቀጥ ብሎ ሲቆም ሰማይ ሲከፈት ያዩ ነበር፡፡ ጳግሜን በተለይም ጳግሜ ሦስት፣ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በአሉ ስለሆነ፤

በዚህ ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ውሆችን የሚባርክበት፤ እና ለሰው ልጆች በፈጣሪው ጸጋ፤ ድህነት እና ፈውስ የሚያሰጥበት ቀን ስለሆነ ብንጠመቅ ከበሽታችን እንድናለን፡፡

በመጸሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራ 5 ቁጥር 4 ላይ ‹‹አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ፣ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኃላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር›› ይላል፡፡

የጌታ መልአክ ‹‹ውኃውን ያናውጥ ነበር›› የተባለው፤ ከሰማይ ወርዶ ውኃውን ይባርከው ነበር ለማለት ነው፡፡ ውኃውም የሚናወጠው የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርከውና እና በመጠመቂያው፣ ለፈውስ ደጅ የሚጠኑት፣ ህሙማን ውሃው በመልአኩ መባረኩን የሚያውቁት ውኃው ሲናወጥ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ቀድሞ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል፤ በዓለም ላይ ያሉትን ውሃዎች ሁሉ ስለሚባርካቸው፤ ብንጠመቅባቸው እንፈወሳለን፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅዱሳን መላእክትም ውኃውን ይባርኩታል፡፡

ጳግሜ ሦስት ይህ ብቻ አይደለም ሊቀ መልአኩ ያስለመደን ነገር አለ፡፡ ይህም ሁል ጊዜ ጳግሜ ሦስት ሌሊት፣ ጠዋት፣ ከሰዓት አልያም ማምሻ ላይ ይዘንባል፡፡ ይህ ከሰማይ የሆነ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ጸበል ነው፡፡

በልጅነታችን ጳግሜ ሦስትን ‹‹ሩፋኤል አሳድገኝ›› እያልን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜ ሦስት በዘነበው ውኃ መጠመቅ ትልቅ መታደል እና ፈውስ ነው፡፡ በደዌ ይሰቃይ የነበረው ኢዮብም በዚህ ሳምንት ነው ተጠምቆ ነው የዳነው፡፡

የሚገርማችሁ በዚህ በከተማ ብዙም ስለማይታወቅ ነው እንጂ፤ በገጠር እና በክፍለ ሀገር የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነው ዝናብ በእቃ ይቀዳና ይቀመጣል፡፡ በተቀዳው ጸበል ቦሃቃው ይረጭበታል፣ በውሃው እህሉ ይቦካበታል፣ ቤቱ ደጁ ይረጭበታል፡፡

ይህም የሚሆነው የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነበው ውኃ የሰላቢ መንፈስን ስለሚያርቅ ነው፡፡ የሰላቢ መንፈስ ከቤታችን የእህል በረከት የሚያሳጣ፣ ለአንድ ወር ያሰብነውን ለሳምንት የማያዳርስ፣ ለዓመት ያልነው በሦስት ወር እንዲያልቅ የሚያደርግ፤ ክፉ መንፈስ ስላለ ይህን ያርቅልናል፣ በጸበሉ በረከት እህል አስቤዛውን ያበረክትልናል፡፡

እንደምታውቁት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ በመጀመሪያዋ እለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክት ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው

ቅዱስ ሩፋኤል ራማ ላይ ነው ከነ ሠራዊቱ ያረፈው ወይም የከተመው፡፡ በራማም መናብርት ተብለው ለሚጠሩት አሥሩ ነገድ አለቃ ወይም መሪ ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሟል፡፡ በኃላም መጋብያን በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ተሹሟል፡፡

ስለዚህ ጳግሜ ሦስት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሲመት ወይም የሹመት በዓሉ ነው፡፡

ይህንንም እራሱ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በመጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15 ላይ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡
740 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:40:40 ሰዎች ባዩት ነገር እየተደነቁ ልባቸውን ለእግዚአብሔር ይከፍቱ ነበር። ጆሮአቸውን ለወንጌል ይከፍቱ ነበር። ብዙዎች ጌታችንን አምነው ነበር። ብዙዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ይጨመሩ ነበር። ሐዋርያትም በተአምራቱ የተከፈተውን የሰዎችን ልብ ተጠቅመው፣ ወዲያው ወንጌልን ይዘሩ ነበር። እግዚአብሔር በብዙ ድንቅና ተአምራት ቃሉን በመካከላቸው ያጸና ነበር። ዛሬም ምናልባት እግዚአብሔር በእጃችን ድንቅና ተአምራቶችን ያደርግ ይሆናል። እነዚህ ተአምራቶች ግን ለራሳችን የሰዎችን ትኩረት መሰብሰቢያዎች እንዳናረግ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። ይልቁንም ትንሽም ሆነ ትልቅ እግዚአብሔር በእኛ ተጠቅሞ የሰራው ነገር ካለና የሰዎችን ትኩረት እግዚአብሔር ከሰጠን፣ ቶሎ ብለን ስለ ተአምራት አድራጊው መናገር፥ እኛን ስለወደደበት ፍቅር የሰው ልጆችን ሁሉ ከኃጢያት በሽታ ለማዳን መሰቀል መሞቱን፣ ሞትና አገንንታዊ አሰራርን ድል አድርጎ መነሳቱን ለሰዎች መመስከር ይኖርብናል። የእግዚአብሔር የልቡ ትርታ ሰዎች ከጨጉዋራ በሽታ መፈወሳቸው አይደለም። ስለ ምድራዊ ፈውሶቻችን ግድ የሚለው አምላክ ቢሆንም፣ ዋናና ትልቁ አላማው ግን ሰዎችን ከኃጢያት በሽታና ዘላለማቸውን ከሚያሳልፉበት ከዘላለም ጨለማ አውጥቶ ወደ ዘላለም መንግስቱ ማስገባት ነው።

ታዲያ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚሰጠው ቦታ እጅግ በጣም ትልቅ እንደሆነ ከተረዳን፣ ስኬት ከእግዚአብሔር እይታ አንጻር ምንድነው? ስኬት ከዘላለም አንጻር ሲታይ ወይንም፣ 70 እና 80 አመታቶችን አልፎ ማየት በሚችለው መነጽራችን ስናየው ምንድነው? እግዚአብሔር አንድን ሰው የተሳካ ህይወት ነበረው የሚለው ያ ሰው በምድር ላይ በተሰጠው ጥቂት ዘመናቶች ምን አይነት ህይወት ሲኖር ነው? ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ እንግዲህ፣ ከእኔ ተማሩ ያለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ከኖረባቸው ስኬታማ አመታቶች በላይ ሌላ ሊያስተምረን የሚችል ነገር የለም። ቅዱሳን አባቶቻችንም በተሰጣቸው በጣም አጭር አመታቶች እያንዳንዱን የተሰጧቸውን ጊዜያቶች በትክክል በመጠቀም ስኬታማ ሆነው ያለፉና እኛም አሁን እየኖርን ላለነው ህይወት ትልቁ ምሳሌዎቻችን፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና ቅዱሳን አባቶቻችን በምድር ላይ የኖሩባቸው አመታቶች ናቸው። አባቶቻችን በኖሩባቸው ጥቂት አመታቶች ውስጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ አምልኮት የነበራቸውና በትክክል የሄዱ፣ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚያውቁ ማድረግ ላለባቸው ነገሮች በሙሉ ትክክለኛውን ጊዜ እያወቁ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ነገር የሚያደርጉ ሁልጊዜ ተልኮ እንዳላቸው የማይረሱ፣ የቀንና የለሊት ሀሳብና ምኞታቸው የእግዚአብሔር የአባታቸውን ፈቃድ መፈጸምና ማገልገል ነው። ጌታችንም ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን፣ ልክ እንደ እኔና እንደ እናንተ ፈታኝ የሆነውን ስጋ ለብሶ በምድር ላይ የተመላለሰ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ታዲያ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን መጨረሻ ላይ፣ የሰጠኸኝን ስራ ፈጽሜ አከበርኩህ በማለት በነበረበት ዘመን መስራት ያለበትን ሁሉ ሰርቶ ጨርሶ ስኬታማ የሆነ ሰው ንግግርን ሲናገር እንሰማዋለን። ከዚህ ንግግሩ፣ ሊሰራ የተሰጠው ስራ እንደነበረ ወይንም እንደመጣ መረዳት እንችላለን። ታዲያ ቃሉን ስታነቡ፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊሰራ ባሰበው የምድር ቆይታው ውስጥ አንድ እየደጋገመ የሚናገረውና ሁልጊዜ ትኩረት የሚሰጥበት አንድ ነገር ነበር።
የእግዚአብሔር ፈቃድ። ፈቃዴን ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ነው የመጣሁት ይላል። አካባቢው ላይ ያሉ ሰዎችን ፈቃድም አያደርግም። ጊዜያዊ ጥቅም ሊያስገኙለት የሚችሉትን ጥሩ ጥሩ እድሎችና አጋጣሚዎችም አይጠቀምባቸውም። ሰዎች ተሰብስበው እናንግስህ ሲሉትም አልፈልግም እያለ ጥሎዋቸው ይሄዳል። የእሱ ልብ ያለው ከፍታም ዝቅታም ጋር አይደለም። ልቡ ያለው የተላከበትን ወይንም ወደ ምድር የመጣበትን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መኖርና ማገልገል ላይ ብቻ ነው። ከተላከበት አጀንዳ ትንሽ ፈቀቅ የሚያረገው አጋጣሚም፣ እድልም፣ ከፍታም ዝቅታም አልነበረም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የልቡ ምኞት ደግሞ የላከውን የአባቱን ፈቃድ መፈጸም እንደነበረ፣ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለው ብሎ ልኮናል። የላከን ደግሞ የእሱን ሀሳብና ፈቃድ እንድንኖርና እንድናገለግል ነው። እሱ የኖረውን ህይወት እንድንኖር ነው። በዚህ በተላክንበት ህይወት ውስጥ፣ የመጀመሪያው ሀላፊነታችን እንደ ተላከ ሰው ማሰብ መጀመር ነው። የሆነ ነገር ለመስራትና ለማገልገል የተላኩ ሰዎች ነን። በየቀኑ የምንሰራውና የምናደርገው ደግሞ የላከንን ሀሳብና ፈቃድ ነው። ከላከን ጋር በጸሎትና ቃሉን በማንበብ ያነበብነውን ደግሞ ለመኖር በመሞከር ውስጥ የጠበቀ አንድነት አለን። በዚህ አንድነታችን ውስጥ የሚሰጡንን ምሪቶች በመቀበል በየቀኑ እንኖራቸዋለን። የየቀኑ ኑሮአችን በእግዚአብሄር ፈቃድ ውስጥ የተጠበቀ ነው። የምናገለግለውም፥ አገልግሉ ተብለን የተላክንበትን መልእክት ብቻ ነው። በዚህ ውስጥ እግዚአብሄር እኛን ያውቀናል። ዋናውና ትልቁ የህይወት ስኬታችን ይሄ ብቻ ነው። የልቡን ሀሳብ መኖርና ማገልገል። ሳይፈጥረን በፊት ስለ እኛ የጻፈውን በየቀኑ መኖር። ልክ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን ዋጋ የምንከፍልበትን ህይወትና አገልግሎት ለእግዚአብሔር እንደ መስዋእት ማቅረብ። ፈቃዳችንን በሙሉ ለፍቃዱ ማስገዛት። ለዘላለም የእርሱ ባሪያዎች በመሆን ውስጥ ያለውን ዘላለማዊ ክብር ማግኘት። እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ዝቅ ብሎ፣ በዘላለም ውስጥ ከፍ ማለት። ከምናልፍበት የምድር ውጣ ውረድ፣ ስቃይና መከራ ጋር የማይወዳደረው ዘላለማዊ ክብር ውስጥ መግባት። በመድኃኒታችን ውስጥ ያገኘነውን ልጅነት ጠብቆ የእግዚአብሔርን የመንግስቱ ተካፋዮች መሆን፣ በዘላለም እረፍት ውስጥ ለዘላለም መኖር። ይሄ ነው የእኛ ግብ። ይሄ ነው የእኛ ስኬት። 2014ዓ ም እንዴት አለፈ ምን አሳካን? ስኬታችንስ በምን ይመዘን? መጪውን ዓመት ስኬት ብለን ማቀድ ያለብን ምድራዊ ነገሮችን በማሳካት ሳይሆን በዋነኝነት ስለዘለዓለማዊ ህይወታችን በማሰብ፣ የላከንን፣ የፈጠረንን አምላክ ፈቃድ መፈፀም ላይ ትኩረት እናድርግ።

ቀሲስ ሳሙኤል አያልነህ

@KaleEgziabeher
180 viewsedited  04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:40:40 ስኬት

ስኬት ስለሚለው ቃል ስናስብ መቼም ሁላችንም ልብ ውስጥ የሚመጡ ይሄን ይሄን ባሳካ ብለን በልባችን ውስጥ የምናስባቸው፣ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስኬቶች ይኖሩናል። ከዚያም በተጨማሪ ደግሞ በአካባቢያችን ላይ የምናውቃቸው ወይንም በsocial media ገጾቻችን እነሱ እንኳን ሳያውቁን እኛ የምናውቃቸውና የምንከተላቸው፣ በየቀኑ የሚያወጡትን ፎቶዎች እያየን የስኬት ምሳሌዎች ያረግናቸው ሰዎችም ይኖራሉ። ስኬት ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም ያለውና በህይወት ዋጋ ከምንሰጣቸው ነገሮች ጋር የተያያዘ ነገር ነው። ለአንዳንዱ በልፋቱ የሚያገኘው ደሞዝና ዋጋው ነው። ለሌላው ደግሞ ትምህርቱን ጨርሶ ያሰበውን ስራ መያዝ ማግባትና መውለድ ሊሆን ይችላል። ለሌላው ደግሞ አካባቢው ባሉ ሰዎች ወይንም በብዙሀኑ ዘንድ በሰራው ስራ እውቅናና ዝናን ማግኘት ሊሆን ይችላል። “ለእኔ በጤናና በሰላም ስራዬን ሰርቼ የቀን ለቀን ውሎዬን በሰላም ካለፍኩ ስኬት ነው” የሚሉ ሰዎችም አሉ። እነዚህ ሁሉ ከላይ የዘረዘርናቸው ነገሮች ምንም ክፋት የሌለባቸው፣ እንዲያውም በዚህች ምድር ላይ ስንኖር ሊያስፈልጉን የሚችሉና የምንጠቀምባቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ግን ደግሞ ልክ እንደ አንድ ክርስቶስን በህይወቱ አምኖ ለመኖር እንደወሰነ ሰው ሆነን ህይወትን ስናየው ከሌሎች ክርስቶስን ከማያምኑ ሰዎች ለየት ያለ የስኬት ትርጉም ሊኖረን እንደሚገባ እናስተውላለን። ለመማር፣ ለማግባትና ለመውለድ የክርስቶስን አማኞች መሆን አይጠበቅብንም። እንዲያውም፣ ስኬትን በእነዚህ ነገሮች ከተረጎምነው፣ ከእኛ በላይ በብዙ እጥፍ የተሳካላቸው ብዙ በጌታችን ኢየሱስ በክርስቶስ የማያምኑ ሰዎች በምድራችን ላይ አሉ። ታዲያ ከተጠራንበትና ነገሮችን በሙሉ ልንመዝንበት ከተሰጠን ህይወት አንጻር ስኬትን እንዴት እናየዋለን?

እኛ ስኬትን ለየት ባለ መንገድ እንድናየው የሚረዳን የውስጥ አይኖቻችን ተከፍተው ከዚህች አጭር 70 እና 80 አመት ቀጥሎ የሚጀምር ዘላለም የሚባል ቁጥር የማይወስነው ዘላለማዊ የሆነ ህይወት እንዳለ መረዳታችን ነው። አያችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የማያምኑ ሰዎች ስኬትን የሚተረጉሙት አይናቸው ሊያይ እስከሚችለው 70 እና 80 አመት ርቀት ብቻ ነው። ህይወታቸውን የሚያቅዱት በዚህች ምድር ቆይታ ላይ ብቻ ተመስርተው ነው። ስለዚህ ስኬት ለእነሱ አብዛኛውን ጊዜ የተያያዘው፣ ከዚህች ምድር ምቾት ጋር ብቻ ነው። እኛ ግን ስኬትን የምናየው፣ ከዚህች በጣም አጭር የምድር ቆይታ አልፈን እንድናይ እግዚአብሔር በሰጠን ሰፊ እይታ ውስጥ ሆነን ነው። ስለዚህ በጣም የምንጨነቀው ለዚህች ምድር አጭር ቆይታችን አይደለም። ለዘላለም ነው። የእግዚአብሔርን ቃል በስፋት እያነበብን ስንመጣ፣ በቃሉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሐሳብ እና ፈቃድ እየተረዳነው እንመጣለን። ሀሳቡን እያወቅነው፣ ከሚናገራቸው ንግግሮች፣ ከሚሰጣቸው ምሳሌዎች፣ ደጋግሞ ትኩረት ከሚሰጥባቸው ሀሳቦች፥ ዋጋ የሚሰጠው ምን ላይ እንደሆነ፣ የሚያተኩረው ምን ላይ እንደሆነ፣ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ እየተረዳን ወይንም እያወቅነው እንመጣለን። ታዲያ እስከዛሬ ድረስ ካነበብነው ወይንም በስብከትና በትምህርት ከሰማነው አስተውለን ካየነው፥ እግዚአብሔር ከምንም ነገር በላይ፥ ትኩረት ወይንም ቅድሚያ የሚሰጠው ዘላለም ለሚባለውና ይህቺን አጭር የምድር ቆይታ ስንጨርስ ስለምንጀምረው ህይወት ነው። እግዚአብሔር ስሙ ወይንም መጠሪያው የዘላለም አምላክ፣ መንግስቱና ዙፋኑ የዘላለም፣ ምህረትና ፍቅሩ የዘላለም፣ ለእኛ የሰጠንም ህይወት የዘላለም ነው። ወንጌል በጣም አስፈላጊና የእግዚአብሔርን ልብ የያዘ ነገር የሆነው የሰዎችን የዘላለም አድራሻ ወይንም የዘላለም መኖሪያ የሚቀይር ነገር ስለሆነ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር የልቡ ትርታ ዘላለም ከሚለው ቃል ጋር በጣም የተሳሰረ ነው። ይሄ አሁን እየተነጋገርንበት ያለነውን ነገር የሚያጠናክርልንንና በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 18 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተናገራቸው ነገሮች ውስጥ እስኪ አንዱን እንመልከት። አንድ ጊዜ ስለ ማመንዘር ትምህርት ሲሰጣቸው እንዲህ አለ። ቀኝ አይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት ሙሉ ሰውነትህ በገሀነም ከሚጣል፣ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻልሀልና። ቀኝ እጅህም ብታሰናክልህ ቆርጠህ ከአንተ ጣላት፣ ሙሉ ሰውነትህ በገሀነም ከሚጣል ይልቅ፥ ከአካላትህ አንድ ቢጠፋ ይሻላልና አላቸው። አያችሁት ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እይታ ብዙ ጊዜ እኛ ስንቀልድ እንኳን፥ በአይኔና በዚህ ሰው ቀልድ አላውቅም እያልን እንናገራለን። እውነት ነው አይን በጣም አስፈላጊ ከምንላቸው የሰውነት ክፍሎቻችን አንዱ ስለሆነ ነው። እንደ ጌታችን ንግግር ከሆነ ግን፥ በጣም አስፈላጊ ነው ከምንለው ከአይናችን በላይ ሌላ በጣም አስፈላጊ ነገር አለ። እሱም ደግሞ ዘላለማችንን የምናሳልፍበት ቦታ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ በሆነ እይታ ውስጥ ሆኖ ሲያየው፣ በምድር ላይ አስፈላጊ የምንለውን ነገር አጥን ዘላለማችንን ከእርሱ ጋር ብናሳልፍ ነው ያተረፍነው። በምድር ላይ አስፈላጊ የምንለው ነገር ዘላለማችንን ካሳጣን የጌታችን ፍርድ ይሄ ነው አውጥታችሁ ጣሉት ወይንም ቆርጣችሁ ጣሉት። በጣም ይጠቅመኛል ብለን የያዝነው ነገር፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ህብረት ካበላሸብን፣ አውጥተን ጥለነው እግዚአብሔርን ወይንም ዘላለማችንን በጥንቃቄ ብንጠብቀው ትልቅ ማስተዋል ነው። ከአይናችን በላይ ልንጠብቀውና ልንንከባከበው የሚገባን ነገር ቢኖር፥ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ልጅነት እና ዘላለማችንን ነው።

እግዚአብሔር ዘላለም ለሚባለው ህይወታችን የሚሰጠውን ቦታ በድርጊት ወይንም በስራ ካየንባቸው ነገሮች ዋነኛው፣ የእኛን የዘላለም አድራሻ ይቀይር ዘንድ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር መላኩ ነው። መዳናችን፣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ በመስቀል ላይ የሰራውን ስራ በማመን ብቻ ያገኘነው ስጦታ እንደሆነ እናውቃለን። ሁልጊዜ መርሳት የሌለብን ግን፣ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ እንጂ፣ ጌታችንን ግን ያላስከፈለው ዋጋ አልነበረም። ነጻ ስጦታ የሆነው ለእኛ ብቻ ነው። ጌታችን ግን እያንዳንዱን የውርደት ጥግ ያየባቸው አሰቃቂ 33 አመታቶች ናቸው። እኛ ሰዎች ስለሆንን ለእኛ ሰው መሆን ቀላል ነው። መጽሐፉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲነግረን ግን በሰው ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፣ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ ይለናል። መድኃኒዓለም ራሱን ማዋረድ የጀመረው፥ የሚሰቀልበት ሰአት ሲደርስ አይደለም። መስቀል ላይ ሲውል አይደለም። ራሱ ከምድር አፈር የሰራውን ሰው ለመሆን ሲወስን ነው። ራሱን ሰው ለማድረግ ከመወሰኑ አንስቶ፣ በምድር ላይ አለ በተባለው ውርደት ስቃይና መከራ ውስጥ የማለፉ ምስጢር፥ እግዚአብሔር ዘላለም ለሚባለው ህይወት ያለውን ቦታ በትክክል ሊያስረዳን ይችላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እያለ የተለያዩ ሰዎችን በመፈወስ፣ ከሰይጣን እስራት ነጻ በማውጣትና በተለያዩ መንገዶች የሰው ልጆችን የረዳ ቢሆንም ዋናው የመጣበት አላማ ግን የእኛን ዘላለም ለማስተካከል ነው። እንዲያውም በምድር ላይ የሰራቸው እያንዳንዱ ተአምራቶች ወደ ምድር የመጣበትን የዘላለም ህይወት ጉዳይ ሰዎች እንዲሰሙና እንዲረዱ ልባቸውን ለማግኘት የተጠቀመባቸው መንገዶቹ ነበሩ። ከጌታችን በሁዋላ የሐዋርያትንም አገልግሎት ስታዩ፣ በሐዋርያቱ እጅ እጅግ ብዙ ድንቅና ተአምራቶች ይደረጉ ነበር። የሚገርማችሁ ግን፥ የትኛውንም ተአምራት ስታነቡ፣ ከእያንዳንዱ ተአምራት በኋላ፥
170 views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ