Get Mystery Box with random crypto!

Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان

የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان U
የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان
የሰርጥ አድራሻ: @ustaz_ebin_selman
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.93K
የሰርጥ መግለጫ

{ادْعُ إِلَىٰ سبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ } ۚ
[ወደ ጌታህም መንገድ በጥበብና በጥሩ ምክር ተጣራ።]
T.me/Ustaz_ebin_Selman
Comment👉 https://t.me/Kamilalhabeshiy

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-04 11:14:57 አሰላሙአለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ ውድ የቻናላችን አባላቶች በሙሉ ከኸይር ስራዎች እና በላጩ ተግባራት ሰዎችን ወደ ኸይር መንገድ ማመላከት ናቸው። በቻናላችን ላይ ሰዎችን በከፍተኛ ቁጥር አድ በማድረግ ያስመዘገበ ሳምንታዊ የኢንተርኔት ያለገደብ ጥቅል በስጦታ የምናበረክት ይሆናል። 

አድ አድ አድ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶ የኸይር ነገራቶች አመላካች በመሆን  የኢልምን መንገድ በማመላከት የበኩሎን አስተዋፅዎ ያበርክቱ።

አድ ማድረግያ ግሩፕ
https://t.me/SchoolOfDaralHijratayn
https://t.me/SchoolOfDaralHijratayn
368 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 23:18:11 ፂም መላጨት ክፍል አንድ

#ፂምን መላጨት #ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑ ይቅርና ጭራሽኑም #ወንጀል አይደለም። የሚላጭ ሰውም ምንም አይነት ቅጣትም የለበትም። መላጨቱ ሀራም ነው የሚል ኢጅማዕም የለም።

አው መቼም የማይዋሸው ነገር ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፂምን በመልቀቅ አዘዋል። ይህን የሚክድ አንድም ሰው የለም። ነገር ግን #ትዕዛዞች በአጠቃላይ ግዴታ መሆንን ያመለክታሉ  ያለው ማን ነው

በቁርኣንም በሐዲስም ውስጥ ያሉ ትዕዛዛት በአጠቃላይ ለግዴታ ነው የሚል አንድም ዓሊም አታገኙም። ስለዚህ ፂም ማሳደግ ግዴታ ነው አይደለም የሚለው ዝርዝር ውስጥ ከመግባታችን በፊት በቁርኣንና በሐዲስ ውስጥ ያሉ የትዕዛዝ አይነቶችን እንመልከት።

1, ለዋጅብ/ ግዴታነት የሚያስረዱ አሉ።
{وأقيموا الصلاة وآتوا الزكاة}
እዚህ ጋር ሰላት እና ዘካ ዋጂቦች ግዴታዎች ናቸው። ትዕዛዙ ግዴታነትን ስለሚያስረዳ።
2, ትዕዛዝ ሆነው የተፈቀደ /ጃኢዝ/ መሆኑን የሚያመለክቱም አሉ። ለምሳሌ፦
{وإذا حللتم فاصطادوا} {فإذا قضيت الصلاة فانتشروا في الأرض وابتغوا من فل الله}
እነዚህ አንቀፆች የሚያስረዱት መፈቀድን ብቻ ነው። መቼም ሀጅ እንዳለቀ ለማደን ጫካ የሚገባ የለም ግዴታነው ብሎ። የተፈቀደ ማለት መስራቱም መተውም እኩል የሆነ ማለት ነው። ትዕዛዝ ነው። ነገር ግን በመስራትም አጅር የለውም። በመተውም ቅጣት የለውም።
3, ትዕዛዝ ሆኖ ማመላከትን የሚያስረዳ አለ። ለምሳሌ፦
{إذا تداينتم بدين إلى أجل مسمى فاكتبوه}
እዳ መፃፉ ግዴታ አይደለም። ምክንያቱም እዚሁ ቦታ ወረድ ብሎ …
{فإن أمن بعضكم بعضا فليؤدي الذي اؤتمن أمانته}
በማያሻማ ሁኔታ ግዴታ አለመሆኑ ፍንትው አድርጎ አስቀምጦታል። እዚህ ቦታ ትዕዛዙ ምንድ ነው? ከተባለ፤ ለማመላከት ለኦርሻድ ነው ይባላል።

በቁርኣንና በሀዲስ ትዕዛዝ የሚመጣው ለግዴታ እና ለሱና ብቻ አይደለም። በቁርኣን ወይም በሀዲስ ውስጥ ትዕዛዝ ካየህ ከሚከተሉት አንዱ ነው።
ለዋጂብ፣ ለሚወደድ ነገር፣ ለማመላከት፣ አደብ ለማስያዝ፣ ለምርጫ፣ ለምኞት፣ ለማሳነስ፣ እኩል ለማድረግ፣ ለማስፈራራት፣ ለዱዓ፣ ለምክር፣ ለኢልቲማስ፣ ለማስቃት፣ ለማላገጥ፣ ለማዋረድ፣ ለመዘውተር፣ ለመግሰፅ፣ ለቁጭት፣ ለማስጠጋት፣ ለመንገር እና ለሌላም።

እዚህ ቦታ የማወራው ስለ አምር ስለትዕዛዝ ስላልሆነ ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት ምሳሌዎች በቂ ናቸው። የትኛው ዝዕዛዝ ለምን እንደሆነ ሊረዱት የሚችሉት ዑለሞች ብቻ ናቸው። ማንም የተንጣጣ ሁሉ ሊያውቀው አይችልም።

ከዚህ በመነሳት ጺም በማሳደግ የመጣው ትዕዛዝ ለዋጅብ አለመሆኑና ለተኽዪር ወይም ለሱና መሆኑን ማወቅ እንችላለን። በምን መልኩ የሚለው በቀጣይ የምዳስሰው ይሆናል።

እያንዳንዱ ንግግር በቁርኣንና በሀዲስ መረጃ የተደገፈ ነው።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል…



1.5K viewsedited  20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 16:44:50
ከዑለሞች ንግግር…
አንዴ የሆኑ ሰዎች በጀማዓ ሰግደው ከማእሙሞች መካከል አንዱ እረሳ። ኢማሙ ከሩኩዕ ቀና ካሉ ቡኋላ ሩኩዕ ያልወረዱ መሰለውና ኢማሙን ለማስታወስ
(واركعوا مع الراكعين)
የሚለውን ቀራ።
ማእሙእሞቹም
{كلا لا تطعه واسجد واقتب}
የሚለውን ቀሩ። የመልስ ምት መሆኑ ነው።

منقول


752 viewsedited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 06:43:54 ያ አላህ ከነ ወንጀላችን ከጅለንሀል አታሳፍረን…

ያ ረብ
806 views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 21:03:10 ክፍል ሶስት የዱረሱ ተውሒድ ኪታብ ደርስ የሚዳስሰው ስለ ሑክም ነው።

ሑክም ማለት በቋንቋዊ እና በኢስጢላህ ፍቺውን አስቀምጫለው።

የሑክም መስደሮች (ምንጮች) ሶስት መሆናቸውንና እነሱም እነማን እንደሆኑ አብራርቻለው።

ሑክም ዓዲይ የሚባለው በአራት ሁኔታ እንደሚገደብ ከነምሳሌው በአጭሩ አስቀምጫለው።

ደርሱን ከሰዓት አንፃር እጅግ አሳጥሬ በአጭሩ ነው ያስቀመጥኩት።

ከደርሱ ጋር ማንኛውም ጥያቄ ካላቹ ማንሳት ትችላላቹ።

ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ሼር እናድርግ።




883 viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 14:51:19 ሼር በማድረግ ደርሱ ለሁሉም እናዳርስ



897 viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 04:09:54
ከአቂዳው ደርሳችን ጎን ለጎን እንደተለመደው የተለያዩ የፊቅህ ትምህርቶች መፅሁፍ የምንቀጥል ይሆናል።

ከዚህ በፊት ስለ ኒቃብ አንስተን በቂ በሆነ ሁኔታ በአምስት ክፍል አብራርተናል።

አሁን ደግሞ በአላህ ፈቃድ #ፂም ማስረዘም ወይም #መላጨት በኢስላም እንዴት ይታያል። ማለትም ፂም ማስረዘም ግዴታ ነው? ወይስ የተወደደ ሱና ተግባር? እንደዚሁም ፂም መላጨት ሀራም ነውን? ወይስ የተፈቀዳ ጃኢዝ?

በአላህ እገዛ ይሄንን #ከቁርኣንና #ከሀዲስ መረጃ በማጣቀስ በሰፊው የምዳስሰው ይሆናል። በተጨማሪም በዓለማችን በተለያየ የምድር ገፅ ላይ የነበሩ ዑለሞች ንግግር በቪዲዮ ለመረጃነት የማቀርብ ይሆናል።

የሸሪዓ ህግጋት ዑለሞች ተረድተውት ለህብረተሰቡ የሚያስምሩት እንጂ ማንም አሊፍ ያለ በሙሉ የሚረዳው አይደለም።

አላህ በሀቅ መንገድ ላይ ያፅናን

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
985 viewsedited  01:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 23:24:14 በተለያዩ ሀጃዎች ሆኜ ተቋርጦ የነበረው የዓቂዳ ደርስ በአላህ ፍቃድ በዚህ ሁለት ቀን ይጀመራል።

አላህ ተውፊቁን ይስጠን
891 views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 21:01:22
ሌላውን እንተወውና የዑለማ ስጋ በቅንፍ (ዑለማን ማማት እንኳን) ገዳይ መርዝ ነው።

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
1.0K viewsedited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 01:47:50
1.5K views22:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ