2023-04-28 19:43:19
ሙሽሪኮች እና ኩፋሮች በአላህ ሩቡብያነት (رب) ከሀዲዎች ናቸው።ክፍል ሶስት…
መረጃችን እዛው ቁርኣን አድርገን እንቀጥላለን።
(وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ )
[ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና "ጌታችሁ (رب) አይደለሁምን" ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)።
ይህ ገና በዓለመ ዘራ ላይ ነው። እንደነሱ ከሆነ ጥያቄው መሆን የነበረበት (አለስቱ ቢረቢኩ) ሳይሆን (አለስቱ ቢኢላሂኩም) ነበር መሆን የነበረበት።
ሰይድና ኢብራሂም ዐለይሂ ወዓላ ነቢያና አፍደሉ ሰላቲ ወተስሊም ለዛ ለአንባ ገነኑ ንጉስ
(ربي الذي يحي ويميت قال أنا أحيي وأميت)
[ኢብራሂም "ጌታዬ (رب) ያ ሕያው የሚያደርግና የሚገድል ነው" ባለ ጊዜ "እኔ ህያው አደርጋለሁ እገድላለሁም አለ።]
በዚህ የተከበረው አንቀፅ አይደለም በሩቡብያ ሊያምኑ ጭራሽ ሩቡብያነቱ ለራሱ አስጠጋው። እኔ ነኝ ህያው የማደርገው የምገለው ብሎ አረፈው።
በተመሳሳይ ፊርዓውንም ይህን አይነት ሙግት ነበረው…
(فقال أنا ربكم الأعلى)
[አለም፦ እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ] አላህ ስለፊርዓውን ሲያወራ በሩቡብያ እና በኡሉሂያ ምንም አይነት ለውጥ እንደሌለው አስርድቶናል። በሌላ ቦታ
(ما علمت لكم من إله غيري)
በዚህ ረብም ኢላህም ምንም ለውጥ የሌላቸው አንድ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
ከሀዲስ አንድ ሁለት እንጨምር
የሞተ ሰው ቀብር ውስጥ የሚጠየቀው (መን ረቡከ) ተብሎ ነው። ታድያ እናንተ እንደምትሉት ሙሽሪኮችና ኩፋሮች በሩቡብያ (በአላህ ረብነት) የሚያምኑ ከሆነ ጥያቄው መሆን የነበረበት (መን ኢላሁከ) ነበር። ምክንያቱም ጥያቄው አማኝ እና አማኝ ያልሆኑትን ለመለየት ነው የተዘጋጀው።
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠቅላይ የሆነ ምክርን ለጠየቃቸው ሰሀብይ ሲመክሩት
{قل ربي الله ثم استقم}
[ጌታዬ (رب) አላህ ነው በልና ከዛ ቀጥ በል።] ሙሽሪኮችም በረብ የሚያምኑ ከሆነ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዚህ ሰሃባ እንዴት ረቢየላህ በል ይሉታል እንደናንተ ከሆነ ማለት የነበረባቸው (ኢላሂየላህ) ነበር። ሰይደል ውጁዱ በተውሒድ ሩብብያ ተብቃቁ። ምክንያቱም ኡሉሂያም ሩቡብያም ለውጥ የለውም።
የሀቂቃው ረብ እሱ እራሱ ነው የሃቂቃው ኢላህ። በአንዱ ሙእሚን በአንዱ ካፊር የሚባል ነገር የለም።
ከቁርኣን መረጃችን ይቀጥላል…
የቻናሉን ሊንክ ሼር በማድርግ እናዳርስ http://T.me/Ustaz_ebin_Selman
975 views16:43