Get Mystery Box with random crypto!

Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان

የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان U
የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان
የሰርጥ አድራሻ: @ustaz_ebin_selman
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.93K
የሰርጥ መግለጫ

{ادْعُ إِلَىٰ سبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ } ۚ
[ወደ ጌታህም መንገድ በጥበብና በጥሩ ምክር ተጣራ።]
T.me/Ustaz_ebin_Selman
Comment👉 https://t.me/Kamilalhabeshiy

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-26 08:33:59 ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተከተለ ወደ አላህ መድረስን አይከጅል

ከሱፍዮቹ ንግግር…
536 views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 07:18:08 ክፍል አራት ሒጃብ እና ኒቃብ
የሀናቢላ መዝሀብ ዑለሞች
ሴት ልጅ ፊትና እጅዋ መሸፈን ግዴታ ነው አይደለም የሚል ሁለት አይነት ዘገባ ከኢማም አህመድ መጥቶዋል። አንዳንድ ሀናቢላዎች ፊትዋና እጅዋ ጨምሮ ሙሉ ሰውነትዋ መሸፈን ግዴታ ነው ብለው ከሳቸው አውርተዋል። ከፊሎቹ ደግሞ ተከታዩን ከኢማም አህመድ ዘግበዋል።
በ"አትታዕሊቅ አልከቢር" አንደኛ ሙጀለድ ገፅ 143 ላይ (ኢማም አህመድ የሴት ልጅ ፊትና መዳፎችዋ ሲቀር ሙሉ ሰውነትዋ ዐውረት ነው ወደ ሚለው አዘንብለዋል።) የሚል ተቀምጦዋል።
በሀርብ ና በሙሀመድ ቢን አቢ ሀርብ አልጀርጃኢይ ዘገባ ደግሞ (ሴት ልጅ ሻጭ ጋር መጥታ ፊትዋና መዳፎችዋ ቢያይ አሮጊት ከሆነች እሺ ወጣት ከሆነች ግን ለሸህዋ ትታሰባለች። እኔ ይሄን እጠላለው አሉ። የዚህ ንግግራቸው ግልፅ ትርጉሙ የሴት ልጅ ፊት እና መዳፍ ዐውረት አለመሆናቸው ነው። ምክንያቱም አሮጊት ከሆነች ወደ እርሳዋ ማየትን አብቅተዋል። በተጨማሪም የወጣትዋንም እጠላለው አሉ እንጂ ሀራም ነው አላሉም። ሀራም ነገር ላይ አሮጊት ሆነች ወጣት ለውጥ የለውም።
ኢብኑ ቁዳማህ በ"ሙግኒ አንደኛ ሙጀለድ ገፅ 431 ላይ (ከፊል የመዝሀባችን ዑለሞች የሴት ልጅ ሙሉ አካልዋ ዐውረት ነው ብለዋል። ምክንያቱም ከነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ሴት ዐውረት ናት) የሚል ሓዲስ ቲርሚዚይ ዘግበዋል። ሀዲሱም ሀሰኑን ሰሂሁን ብለውታል። ነገር ግን ፊታቸውን እና መዳፋቸውን እንዲከፍቱ አግራሩላቸው። በመሸፈናቸው መሸቃ /መቸገር/ ስላለባቸው።
በ"ሸርሁል ከቢር" ሶስተኛ ሙጀለድ በገፅ 206 እና 207 ላይ (ነፃ ሴት ፊትዋ ሲቀር ሙሉ ሰውነትዋ ዐውረት ነው። በመዳፎችዋ ሁለት አይነት ዘገባ አለ።) የነፃ ሴት ፊትዋ ያለ ምንም ኺላፍ በሰላት መክፈት ይበቃላታል። ዘገባዎቹ የተለያዩት በመዳፎችዋ ነው። መከፈታቸው እንደሚበቃ ከኢማም አህመድ ተዘግቦዋል ይሄ ደግሞ የማሊክም የሻፊዒይም አቋም ነው። ምክንያቱም ከኢብኑ ዐባስና ከሲቲና ዓኢሻህ
{{ ولا يبدين زينتهن إلا ما ظهر منها }
[[ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለፁ]]]
በሚለው ቁርአን መዳፍ እና ፊት ብለዋል። እንደዚሁም ለሀጅ ወይም ለዑምራ በሃረመች ሴት ፊትዋን መሸፈን እና መዳፎችዋን በጓንት መሸፈንዋ ሀራም ነው። በብዛት ግልፅ የሚወጡ ናቸው። በተጨማሪም በመሸጥ እና በመግዛትም ጊዜ መከፈታቸው ግድ ይላል።) ብለው ይዘረዝራሉ
መርዳዊ ከኢብኑ ተይሚያ ይዘው በ"ኢንሳፍ" በስምንተኛው ሙጀለድ በገፅ 28 ላይ (ወደ አጅ ነብይ ሴት ያለ ምክንያት ማየት ይቻላልን? ከኢማም አህመድ ሁለት ዘገባዎች አሉ አንደኛው ይጠላል ሀራም አይሆንም የሚል ነው። ኢብኑ አቂል ፊትናን ካልፈራ ወደ አጅ ነብይ ሴት ማየቱ ሀራም አይሆንም ብለዋል።) ይሄ ከኢብኑ ተይሚያ የተዘገበው ነው።
ኢማም አልመርዳዊይ ይህን የኢብኑ ተይሚያ ንግግር ሲያብራሩ (ይህ ለሰዎች ከዚህ ውጪ አይመችም በተለይ መህረም ካልሆኑ ዘመድ አዝማድ፣ አብሮዋቸው ያደገና የኖራቸው ወዳጆች፣ ጎረቤቶች ጋር መራራቅን ያመጣል።
ይሄ በመዝሀበ ሻፊዕይም እንደዚሁ ነው።) በማለት አብራርተውታል።

የሀንበሊያዎቹ ንግግር ሲጠቃለል የሴት ልጅ መዳፎችዋ እና ፊትዋ ዐውረት አለመሆናቸው እና አብሮ የኖራቸው ማህበረሰቦች ውስጥ ያሉ አጅ ነብይ የሆኑ ሴቶችን ያለ ምንም ምክንያት ቢያይ ሀራም አለመሆኑን እና ፊትናን ያልፈራ ከሆነ እንደማይጠላም በሰፊው አስቀምጠዋል።
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
561 views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 06:41:53 ፈትዋ እና ዒልም ልዩነታቸው
እኔ የኢብኑ ተይሚያም ሆነ የተከታዮቹ ንግግር አልሰራበትም መንገዴም አይደለም። ነገር ግን አንዳንድ መንገዱ ለጠፋቸው በሚያምኑት በሸሆቻቸው ንግግር እናስረዳቸው ከገባቸው።
ዛሬ ላይ ሰው በዓሊም እና በሙፍቲ መሀከል ያለውን ልዩነት ባለማወቁ፤ አንዳንድ ቀራሁ ባዮች ደግሞ በፈትዋ እና በዒልም መሀከል ያለውን ልዩነት ሳይገባቸው ሁለቱም ተያይዘው ገደል ይገባሉ።
ዓሊም ማለት በአጭሩ በኪታቦች የተቀመጠውን እያንዳንዱ ብይን በዝርዝር በጥልቀት የሚያውቅ ማለት ነው። ሙፍቲ ግን ከዚህም ባለፈ ብዙ መለያዎች አሉት። አሁን እሱን አልዘረዝርም
ኢብ ረጀብ አል ኢስቲኽራጅ ሊአህካሚል ኸራጅ በተሰኘው ኪታባቸው ገፅ 89 ላይ (በሰሒሑ ፈትዋ ቢሰጥ መፍሰዳ የሚኖር ከሆነ ሰሒሑን ትቶ በደዒፉ ፈትዋ ይሰጣል።) ይላሉ።
ኢብኑ ተይሚያ በመጅሙዐል ፈታዋ 22ተኛ ሙጀለድ ገፅ 345 ላይ (ተበላጩ ቀውል በላጭ ለሆነ ጉዳይ በላጭ የተሻለ ሆኖ ይገኛል።) ይላል።

አስፈላጊ ከሆነ የጉድ አዘንበዋለው። ለሚመራ ሰው ጥቂትም ይበቃዋል። እዚህ እየተማማርን ያለነው የሸሪዓዊ ህግጋትን እንጂ ፈትዋ አይደለም። ፈትዋ ከሙፍቲዎች ሄዳቹ መጠየቅ ነው። እኛ ግን ሸሪዓችን ያዘዘንን በዝርዝር እንማራለን።

ለአንዱ ሰው የተሰጠ ፈትዋ ለሌላኛው የማይሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው።

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
480 viewsedited  03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 05:04:13

464 views02:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 04:47:34 ክፍል ሶስት ሒጃብና ኒቃብ
የሻፊዒያ መዝሀብ ዑለሞች

በ"አልሙሀዘብ" አንደኛ ሙጀለድ ገፅ124 ላይ (ነፃ ሴት ፊትዋና ሁለት መዳፎችዋ ሲቀር ሙሉ ሰውነቷ ዐውረት ነው። በቁርኣን
{ولا يبدين زينتهن إلا ما ظهر منها}
[[ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለፁ]]]
ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ሲፈስሩት ፊትዋ እና መዳፎችዋ አሉ። ነብዩም ሰዐወ ለሀጅ ኢህራም ላይ ለሴቶች ጓንትንና ኒቃብን ከልክለዋቸዋል። ዐውረት ቢሆኑ ኖሮ መሸፈናቸው ሀራም አይሆንም ነበር። እንደዚሁም ስትገዛና ስትሸጥ መስጠት መቀበል ላይ ግልፅ ስለሚሆኑ ዐውረት አልተደረጉም።) ይላሉ

በ"አትተህዚብ" ነፃ ከሆነች ከሷዋ ከፊትዋና ከመዳፎችዋ ውጪ ምንም ነገር ማየት አይችልም አውረት ነውና
(ولا يبدين زينتهن إلا ما ظهر منها)

በ"መጅሙዕ" ሶስተኛ ሙጀለድ/በገፅ167 ላይ (ነፃ ሴት ፊትዋና መዳፎችዋ ሲቀሩ ሙሉ ሰውነትዋ ዐውረት ነው። ولا يبدين زينتهن إلا ما ظهر منها ኢብኑ ዐባስ ፊትዋና መዳፎችዋ ብለዋል። ነብዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሀጅ የሀረመች ሴትን ጓንትንና ኒቃብን ከልክለዋታል።) የሚል ያስቀምጣሉ።

የሻፊዒያዎች ንግግር ሲጠቃለል ሴት ልጅ መሸፈኑ ግዴታ የሚሆንባት ከፊትዋ እና ከእጆችዋ ውጪ ያለው ሰውነትዋ ነው። ኒቃብ ሸሪዓ አትልበሱ ያለበት እንጂ ልበሱ ያለበት ቦታ የለም።

ይቀጥላል…
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
527 views01:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 00:09:16
Razi Tube አናመሰግናለን ጀዛከ አላሁ ኸይር
#ኒቃብ
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
567 viewsedited  21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 19:56:53 ክፍል ሁለት ዱሩሱ ተውሒድ

ደርሱን የምትከታተሉ ኮሜንት ላይ ደርሶዋል ብላቹ ፃፉ

ጥያቄ ካላቹ በኮሜንት አስቀምጡልኝ
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
666 viewsedited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 18:07:35 ክፍል ሁለት ሒጃብ እና ኒቃብ
ሴት ልጅ እጅዋና ፊትዋ ሲቀር በሀነፊያዎች ደግሞ እግሮቿ ሲቀር ሁሉም አካልዋ መሸፈን ግዴታ በመሆኑ ዑለሞች ዘንድ ኺላፍ የለም። እንደዚሁም የምትለብሰው ልብስ ሰፊ ፣ የሰውነት ቅርፅ የማያሳይና ቀጭን ያልሆነ በመሆኑም ኺላፍ የለም። ፀጉሯ ጆሮዋን ጨምሮ እንዲሁም ደረትዋን፣ አንገትዋን እና ክንዶችዋን መሸፈን ዋጂብ በመሆኑም ኺላፍ የለም።
ይህም በአራቱም መዝሀቦች ያለውን አቋም በኪታቦቻቸው እንይ

ከሀነፍያ ዑለሞች ኪታብ
"በሙኽተሰር ቁዱሪይ" ገፅ 20 ላይ (የሴት ልጅ ፊትዋ መዳፎችዋ እግሮችዋ ሲቀሩ ሰውነቷ በአጠቃላይ ዐውረት ነው።)
የ"ዒናያህ" ፀሀፊ በአንደኛው ሙጀለድ በገፅ 259 ላይ ያለፈውን የቁዱሪይን ንግግር ሲያብራሩ (እግርን ያላስገቡት ከራሳቸው ነው። ሀሰነል በስሪይ ከአቡ ሀኒፋ እንደ ዘገቡት እግር ዐውረት አይደለም። ኢማም ከርኽይም እንዲህ ነው የሚሉት) በማለት አስቀምጠዋል። ==አስከትለውም (ይሄ ነው ሰሂሁ። ምክንያቱም እግራዋ ስትሄድ ጫማ ላታገኝ ትችላለች ወይም ነጠላ ጫም ከለበሰች እግርዋ ተከፍቶ ስለምትቸገር መሸፈኑ ግዴታ አይደለም። እንደዚሁም ፊትዋ መሸፈ ግድ ካልሆነ እግር ደግሞ ባለመሸፈን የበለጠ ነው።) በመለት አብራርተዋል።

የ"ሉባብ ፊ ሸሪሂል ኪታብ" ባለቤት (በሰሂሁ ነፃ  የሆነች ሴት ፊትዋና መዳፎችዋ ውስጣቸውም ውጫቸውም ሲቀር ሙሉ ሰውነቷዋ ዐውረት ነው። "ሸርሁል መንያ" ላይ እንደተጠቀሰው በ"ሂዳየህ" ደግሞ ይሄ ገለፃ እግር አውረት ነው በሚለው ነው የተቀመጠው። አሰህ በሆነው ዘገባ የሴት ልጅ እግር ዐውረት አለመሆኑ ነው።)ብለው አስፍረዋል።

የሀነፊያዎቹ ንግግር ጠቅለል ሲደረግ፦ የሴት ልጅ ፊትዋ መዳፎችዋና እግሮችዋ የመሸፈን ግዴታ የለባትም ነው።

የማሊኪያ ዑለሞች
ቃዲ ዐ/ወሀብ በ"አልኢሽራፍ"1/262 ላይ (የሴት ልጅ ፊትዋ እና መዳፎችዋ ሲቀር ሙሉ ሰውነቷዋ ዐውረት ነው። ደሊላችንም…
{وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلاَّ مَا ظَهَرَ مِنْهَا}
[[ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ]]  ግልፅ የሆነው ማለት ፊት እና መዳፎች ነው ተብሎዋል። እንደዚሁም ፊትዋ እና መዳፎችዋ ለሀጅ ኢህራም ላይ መክፈት ግዴታ ስለሚሆንባት ፤ ዐውረት ቢሆኑ ኖሮ እንደ ሌላውም አካል መሸፈን ግድ ይሆንባት ነበር።) በማለት አጠናክረው አስቀምጠዋል።
በ"አልመዑነህ ዐላ መዝሀቢ ዓሊሚል መዲነህ" ገፅ 228 ላይ (ነፃ ሴት ፊትና እጆችዋ ሲቀር ሙሉ ሰውነቷ ዐውረት ነው። ከሁለቱ ውጪ ሙሉ መሸፈን ግዴታ ይሆንባታል።
በ"ኢርሻዱል መሳሊክ ኢላ አሽረፊል መሳሊክ"1/15 (ነፃ ሴት ሁሉም ነገርዋ ዐወረት ነው ፊትና መዳፎችዋ ሲቀሩ

የማሊኪያዎች ንግግር ጠቅለል ሲደረግ፦ የሴት ልጅ ፊትዋና መዳፎችዋ መሸፈን ግዴታ አይደለም።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል…
ሼር
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
1.1K views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 09:33:45 ወላሂ በዚህ ዘመን ሂጃብ እና ኒቃብን ለማብራራት መገደድ በራሱ ያሳዝናል። ሰው ከአካሉ የት ድረስ መሸፈን እንዳለበት ካላወቀ፤ የአንድ ሀገር የባህል አልባሳት እና የእስልምና ድንጋጌ ከተደባለቀበት…  እመነቱ ያሰጋል። በሰማው መነዳት እንጂ ነገሩን ከስር መሰረቱ ለማጥናት ዝግጁ አይደለም። አንድ ሀሳብ ሲነሳ ከምን አንፃር፡ በምን ሁኔታ ብሎ ከማጣራት ይልቅ ለመሳደብ ለመዛለፍ ነው የሚሄደው። ታድያ ይሄ ነው እስልምና

የሂጃቡ እና የኒቃቡ በዝርዝር በአላህ ፍቃድ ከሙሉ መረጃ ጋር አስቀምጣለው። መጀመሪያ ሂጃብ ማለት በቋንቋ ትርጉሙ እና በሸሪዓዊ ትርጉሙ፤  የወንድ እና የሴት ሂጃብ በአራቱም መዝሀብ ዝርዝር በኪታቦቻቸው እያጣቀስኩ አስቀምጣለው።
የነብዩ ሰዐወ ሚስቶች እና ሌሎች ሴቶች ለውጥ አላቸው?
ኒቃብ የዐረቦች ባህል ወይስ የእስልምና?
በእስልምና ኒቃብ መልበስ የተከለከለባቸው ቦታዎች አሉ? … እነዚህን በየተራ በዝርዝር ለማየት እሞክራለው። ምን አልባት እዚህጋር ባስቀመጥኩት ቅደም ተከተል ላልጠብቅ እችላለው። ፅሁፉን ስጀምር እንደ አስፈላጊነቱ አስኬደዋለው።

ለመጀመር ያህል ሂጃብ ማለት ምን ማለት ነው።
ሂጃብ በቋንቋዊ ትርጉሙ /حائل/ ግርዶሽ ወይም /ساتر/ ሚሸፍን ማለት ሲሆን ለተለያዩ ጉዳዮች ልንጠቀመው እንችላለን። ለምሳሌ ፦
ሂጃብ ማለት <ግርዶሽ> በሁለት ነገሮች መካከል የሚለይ ማለት ለመሆኑ ከቁርአን  {{فَاسْأَلُوهُنَّ مِنْ وَرَاءِ حِجَابٍ}}
[[በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቁዋቸው።]]
በቁርአን ሳቲር የሚሸፍን ብሎ ሂጃብን ፈስሮታል።
 {{وَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ جَعَلْنَا بَيْنَكَ وَبَيْنَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ حِجَابًا مَّسْتُورًا}}
[[ቁርኣንንም ባነበብክ ጊዜ በአንተ እና በእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም በማያምኑት ሰዎች መካከል የሚሸሸግን ግርዶሽ አድርገናል።]]

ከነዚህ ውጪ ለማዕናዊይ ነገሮች ሂጃብ ይባላሉ። ለምሳሌ፦
ለፀሀይ ብርሀን حجاب الشمس ብርሀንዋ ማለት ነው።
በአላህ እና በባሪው ዱዓ መሀከል ያለው ግርዶሽ ሂጃብ ይባላል። በሀዲስ  َاتَّقِ دَعْوَةَ الْمَظْلُومِ فَإِنَّهُ لَيْسَ بَيْنَهُ وَبَيْنَ اللهِ حِجَابٌ 
[[የተበዳይን ዱዓ (እንዳያገኝህ) ተጠንቀቅ በሱና በአላህ መሀከል ግርዶሽ የለም።]]
ሱፍያዎች ከሁሉም ነገር አለያይቶ ወደ አላህ ብቻ የሚያደርስን ነገር ሂጃብ ይሉታል። ከአላህ ውጪ ካለ ነገር ስለሚጋርድ
መጠበቂያ ሂርዝ ሂጃብ ይባላል። كتب لها الفقيه حجابا ፈቂሁ መጠበቂያ ሂጃብ ፃፈላት ሲባል ሂጃብ ማለት ሂርዝ ወይም መጠበቂያ ማለት ነው። እንደዚሁም አረቦች علقت لولدها حجابا ለልጅዋ ሂጃብ አንጠለጠለችለት ካሉ መጠበቂያ ሂርዝ ማለት ነው።
በተጨማሪም በውስጣችን በደረት እና በሆድ መሀከል የሚለይ ለመተንፈስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው አካል ሂጃብ ይባል። ሴት ልጅ ጭንቅላትዋ አንገትዋ እና ደረትዋ የምትሸፍንበት ነገር ሂጃብ ይባላል። እንደ አጋጣሚ ፊትዋ የምትሸፍንበት ነገር ሂጃብ ሊባል ይችላል።

ውድ የኢስላም ልጆች ይህ እጅግ በጣም አጠር ብሎ የሂጃብ ቋንቋዊ ትርጉሙ ነው። በሸሪዓዊ ትርጉሙ በቀጣይ እንመለስበታለን።

ምንጭ የአረብኛ ቃሙሶችና አል አደቡል ዓረቢይ

ይቀጥላል…
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
898 views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 00:08:00 የነብዩ ሰለላሁ ዐይሂ ወሰለም የተከበረው ዘራቸው በእናታቸው ቡኩል
الام
آمنة بنت وهب بن عبد مناف بن زهرة
እናታቸው አሚነቱ ቢንት ወህብ ቢን ዐብዲ መናፍ ቢን ዙህረህ ቢን ኪላብ

የአባታቸውና የእናታቸው ዘር የሚገናኘው በኪላብ ነው።

ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
879 views21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ