2023-05-13 12:42:31
የዚህች ህፃን ልጅ ፎቶ አንዳንድ ሙስሊሞች ያለ አግባብ እየተራገሙና ስርኣት በጎደለው ሁኔታ ሲፖስቲት አይቻለው። በተቃራኒ ፎቶው ያነሳት ሰው ሙስሊም ባይሆንም ለልጅቱ መልካም ለመስራት ሲራራጥ አይቻለው።
ይህ ምን ያህል የአቂዳ መበላሸት ውስጥ እንዳለን ነው በፖስቶቻቸው የተረዳውት። እኛ እንደ ኢስላም ማንም ፈልጎ የሚወልድ የለም። ልጅ ከአላህ የሚሰጥ ልዩ ስጦታ ነው። አላህ ሊፈጥረው የፈለገውን ነፍስ አልወልድም ስላልክ አትመልሰውም። አላህ እንዲፈጠር ያልፈለገው ነፍስ አለምን ብትሽከረከር ልትወልድ አትችልም። አላህ በቁርኣን
{{لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثاً وَيَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ الذُّكُورَ (49)أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ }}(50)
[የሰማያት እና የምድር ንግስና የአላህ ነው። የሚሻውንም ይፈጥራል። ለሚሻው ሰው ሴቶችን (ልጆች) ይሰጣል። ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል። ወየወም ወንዶችና ሴቶችአድርጎ ያጠናዳቸዋል። የሚሻውን ሰው መካን ያደርገዋል። እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና።]
እምነታችን ልጅ የአላህ የስጦታ እንጂ የማንም ፍላጎት አይደለም። አላህ የሚፈልገውን በሚፈልገው ቦታ ያለ ማንም ከልካይ ይፈፅማል።
ሌላው ልጅ የሚረዝቀው አላህ እንጂ እናንተ አይደላቹም። ልጃቹ ወደ ዱንያ ሲመጣ የራሱን ሲሳይ ይዞ ነው የሚመጣው። ማንም የማንንም ሲሳይ ሊበላ አይችልም። አላህ በቁርኣን…
{ وَلَا تَقْتُلُوا أَوْلَادَكُمْ خَشْيَةَ إِمْلَاقٍ ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُهُمْ وَإِيَّاكُمْ ۚ إِنَّ قَتْلَهُمْ كَانَ خِطْئًا كَبِيرًا} (31)
[ልጆቻችሁንም ድኽነትን በመፍራት አትግደሉ። እኛ እንመግባቸዋለን። እናንተንም (እንመግባለን)። እነርሱን መግደል ታላቅ ሀጢያት ነውና።) ሱረቱል ኢስራእ
በሱረቱል አንዓም ላይ ደግሞ
{ولا تقتلوا أولادكم من إملاقٍ نحن نرزقكم وإياهم﴾
[ልጆቻችሁንም ከድህነት አትግደሉ። እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና።]
በነዚህ ሁለት አንቀፆች ሁለት ነገር አስቀምጦዋል። አንቀፆቹ ካያቹዋቸው ትንሽ ለውጥ አላቸው። የሱራቱል ኢስራእ ላይ አባቱቹ ድሃ አይደሉም። ነገርግን ድህነትን ይፈራሉ። ለዛም አላህ ከልጆቹ ጀመረና [እኛ እንመግባቸዋለን። እናንተንም (እንመግባለን)] አለ። በሱረቱል አንዓም ግን አባቶች እራሳቸው ድሃዎች ናቸው። ለዛም አላህ በራሳቸው በአባቶቹ ጀምሮ [እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና።] ይላል።
የአንተም ሆነ የልጆችህ ሲሳይ በአላህ ነው። ልጅ የመፈጠር ያለመፈጠር ጉዳይም የአላህ ነው። የማንም ምርጫ ፍላጎት አይደለም። አላህ ልጅ መፈጠሩን ከፈለገ <አንተ ፈለግክም አልፈለግክም ይፈጠራል።> አላህ እንዲፈጠር ካልፈለገ <አንተ ብትፈልግም ባትፈልግም> ወፍ የለም።
አላህ ልጅ ላጡት ሷሊህ ልጆች ይስጣቸው። ላገኙትም ሷሊሆች ያድርግላቸው። የሲሳዩ ጉዳይ የሱ ነውና ሲሳዩንም ይለግሳቸው።
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
1.1K views09:42