2023-04-26 11:03:11
ክፍል አምስት ሒጃብ እና ኒቃብ በአጠቃላይ የሴቶች ፊት እና መዳፎቻቸው ዐውረት አለመሆናቸውና ፊትናን ካልፈራ ወደ ሁለቱም ማየት የሚፈቀድ መሆኑን ከሁሉም የኢስላም ዑለሞች ተምረናል። ከፊትዋ እና መዳፎችዋ ውጪ ሙሉ ሰውነቷዋ ዐውረት መሆኑ ከአጠቃላይ ዑለሞች መጥቶዋል። ኢማም አህመድ ግን በአንደኛው ሪዋያቸው ከራሀ እንጂ ሀራም አለመሆኑ ያመለክታል።
ከዚህ በመነሳት በተከታዩ እንሰበስበዋለን ማንኛውም ሙስሊም ለሆነች ሴት ከፊት እና አጆችዋ ውጪ በፍፁም ልትከፍት አይፈቀድላትም።
እህቴ ፁጉርሽን ስለከፈትሽው አይምሮሽ አይሰፋም። ስለሸፈንሽውም አይጠብም። ይልቁንስ ሂጃብ አስተዋይ ያደርግሻል። በሄድሽበት እንድትከበሪ ያደርግሻል።
እህቴ ፀጉርሽ ዳርዳሩ ግንባርሽ አካባቢ ፣ ጆሮሽ አካባቢ ፣ አንገትሽ፣ ደረትሽ፣ ክርኖችሽ ስለገለጥሽ እንዲሁም የሚያጣብቁ ልብሶች ስለለበስሽ ባል አይመጣልሽም። ቆንጆም አትሆኝም። ስልጡንም አትባይም። ይልቁንስ
ከመልካም #ወንዶች
ልብ ትወጫለሽ። ለባለጌዎች መሳለቂያ ትሆኛለሽ!!! እህቴ በመሸፈንሽ በመሰተርሽ ከአላህ ወሰን የሌለው እራህመት ይመጣልሻል።
በነፃነትና በስልጣኔ በማሳበብ ወደ መገላለፅ ዳዕዋ ማድረግ የሸይጣን ጥሪ ነውና አላህ የእህቶቻችን ዐይን እንዲከፍት እንለምነዋለን።
የሴት ልጅ ፊትዋ እና መዳፎችዋ መሸፈኑ ግዴታ ነው ማለት የሰሀባ ሴቶች ሳይቀር የኢስላም ሴቶችን ያለ መረጃ በወንጀል መፈረጅ ነው።
ታድያ ኒቃብ ዋጅብ አይደለም ማለት ኢስላማዊ አይደለም ማለት አይደለም። ከኢስላም ከአምስቱ ህጎች በሁለቱ ይካተታል። ከፊል ዑለሞች ሙባሕ ጃኢዝ ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ሱና ነው ብለዋል።
አንዲት ሴት ኒቃብ ብትለብስ ሱና ነው። በዚህ ፊትና በበዛበት ዘመን ስሜትዋን አሸንፋ ከመገላለጥ መሸፋፈንን ከመረጠች ልትበረታታ፣ ልትደገፍ ይገባል። ነገር ግን በፈለጉ ሰዓት ማውለቅ መብታቸው መሆኑ፤ በፈለጉ ሰዓት መልበስ መብታቸው መሆኑ በግልፅ ሊነገር ይገባል። ዛሬ ለብሳ ነገ ብታወልቀው ምንም ችግር የሌለው መሆኑና የስዋ መብት መሆኑን ልናሳውቃት ይገባል። በአጠቃላይ ኒቃብ በሸሪዓችን ለሴቶች የሚወደድ ሱና መሆኑ አብዛኛዎቹ ዑለሞች አስቀምጠዋል።
ኒቃብ ለብሳ የተጣበቀ የሰውነት ቅርፀጿን የሚያሳይ ውጥርጥር ያለ ልብስ ከምትለብስ ኒቃቡን ትታ ሰፋ ያለ ልብስ ይሻላታል። ምክንያቱም የሰውነት ቅርጿ የሚያሳይ ልብስ መልበስ ሃራም ነው ያሉ አሉ።
መሰተር/መሸፈን እንዲሁም ሀያእን መላበስ እስልምና የመተግበር ምልክት በመሆኑ ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ይህ የአንዲት ሴት የኢማንዋ መለኪያ አይደለም። ምን አልባት ኒቃብ ለብሳ የባል ሀቅ የጎረቤት ሀቅ ማትወጣና መጥፎ ልትሆን ትችላለች። ምን አልባት የተገላለጠችው ደግ ቸር አመለ ሸጋ ከአላህም ከሰውም ጥሩ ነገር ሊኖራት ይችላል። እንደዚሁም በተቃራኒው ኒቃብ ለብሳ አላህን ፈሪ ሰውን አክባሪ ትሁት ልትሆን እና የራቆተችዋ በተቃራኒ ልትሆን ትችላለች። ስለዚህ በዛሂር ኒቃብ ስለለበሰች ዲነኛ ስለተጋላለጠች ከዲን የራቀች አድርጋቹ አትፍረዱ።
ከኛ የሚጠበቀው ሁላቸውም ተሰትረው መልካም እንዲሰሩ መምከር ነው።https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
614 views08:03