Get Mystery Box with random crypto!

Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان

የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان U
የቴሌግራም ቻናል አርማ ustaz_ebin_selman — Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان
የሰርጥ አድራሻ: @ustaz_ebin_selman
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.93K
የሰርጥ መግለጫ

{ادْعُ إِلَىٰ سبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ } ۚ
[ወደ ጌታህም መንገድ በጥበብና በጥሩ ምክር ተጣራ።]
T.me/Ustaz_ebin_Selman
Comment👉 https://t.me/Kamilalhabeshiy

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2023-04-14 04:03:39
የዛሬዋ ለሊት ከሌላው ለይት ይላል። ለሊቱ ለይለተል ጁሙዓ ነው። አንድ አንድ ዑለሞች ለይለተል ጁሙዓ ከጎዶሎ ቀናት ከገጠመ ለይለተል ቀድር ነው ይላሉ።

ዛሬ 23ተኛ ለሊት ነው። ከቻላቹ ቁርኣን ተከፋፍላቹ አኽትሙ። ያሲን እየቀራቹ ዱዓ አድርጉ።

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman

ልጆቻቹ ህፃናቶቹ ወንጀል የለባቸውም። ዱዓ እያደረጋቹ አሚን አስብሉዋቸው።
453 viewsedited  01:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 23:29:48
ያ አላህ! የአንተን ውዴታ የምናገኝበትን፤ ከእሳት ድነን በጀነት የምንከብርበትን አንድ የእዝነት እይታህን እጠይቅሀለው… ያ አላህ ቤተሰቦቻችንም ወዳጆቻችንም በዱዓ አውሱን ላለን በአጠቃላይ…

ያ ረቢ…

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
621 views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 21:18:55
ዛሬ ለይለቱል ቀድር ሊሆን ይችላል። ምንድ ነው ለጌታቹ የምትጠይቁት…

ሌላው እንዲማር አካፍሉን ባረከላሁ ፊኩም ምን አልባት አንዱ አሚን ብሎ መቅቡል ይሆንላቹዋል። ሌላው ከሰራበት ደግሞ አጅር ታገኛላቹ ፃፉልን።

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
748 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 20:17:28 ቁርኣንን በየቀኑ ለማኽተም ወይም በሁለት ቀን ለማኽተም በቀላሉ አንድ ሰፍሓው ስንት ደቂቃ እንደሚወስብን እንየው። ለምሳሌ አንድ ሰፍሓ በአንድ ደቂቃ የሚጨርስ ሰው በ10 ሰዓታት ቁርኣንን ማኽተም ይችላል።

አጠቃላይ የቁርኣን ሰፍሓ 600 × በ1ደቂቃ = 10 ሰዓት  ከ24 ሰዓታት ውስጥ 10 ሰዓት ብቻ ለቁርኣን እንስጥ። ስንቀራ ሰዓት እንያዝና … በዚህ ከሄድን በቀላሉ በአንድ ቀን ማኽተም እንችላለን ማለት ነው።

ከ24 ሰዓታት 5 ሰዓት ለቁርኣን ብንሰጥ በሁለት ቀን አኸተምን ማለት ነው።

ይሄ የሚሆነው አንድ ሰፍሓ በአንድ ደቂቃ ከሆነ ነው። ከዛ በታች ከሆነ አባዝተ ድረስበት…
740 views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 19:52:24 ረመዷኑ አለቀ ውዶቼ ቁርኣን ላይ እንቸክል። ትርጉሙ ባይገባንም መቅራቱ ብቻ ቀልብን ያረጥባል። የቀልብ እድፍን ያፀዳል።

የአቀራር ፍጥነታችን ጨምረን አንድ ሰፍሐ በ40 ሰከንድ መጨረስ ጀምረናል።
714 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 09:33:40
አሚን የማለትን ዋጋ አናውቅም
آمـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــين
አሚን ማለት ተቀበለኝ (استجب) ማለት ነው። አንዳንዶች ደግሞ አሚን የአላህ ስም ነው ብለዋል።

አላህ በቁርኣን በሱረቱል ዩኑስ አንቀፅ 89 ላይ እንዲህ ይላል…
{قَالَ قَدْ أُجِيبَت دَّعْوَتُكُمَا}
ዱዓ ያደረጉት ነቢላሂ ሙሳ ናቸው። አላህ ግን የሁለታቹም ዱዓ ተቀብያለው ነው ያለው። እንዴት አንድ ሰው ዱዓ አድርጎ የሆለታቹም ይላል ሲባል… ሙፈሲሮች ነቢላሂ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም ዱዓ ሲያደርጉ ነቢላሂ ሀሩን አሚን ይሉ ነበር ይላሉ። የሁለታቹም በማለት የተፈለገው ዱዓውንና አሚኑን ነው ይላሉ።

ሙፈሲር ቁርጡቢይ አሚን ከኛ በፊት ለሙሳ እና ለሀሩን እንጂ አሚን የሚለው ቃል አልነበረም ይላሉ።

ወንድሜ እህቴ የትም ብንሆን አሚንን እንዳንዘነጋ። በማን ዱዓ በማን አሚን ቀቡልያ እንደምናገኝ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው።
آمــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــين
https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
903 viewsedited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 04:51:50
ውዶቼ … በረመዷኑ ልባቸው ከልብ በሽታዎች ታጥቦ፤ ወንጀላቸው ተምሮ፤ ዐውፍ ተብለው፤ ከእሳት ነፃ ተደርገው የአላህን ውዴታ አግኝተው ከሚሸኙት አላህ ያድርገን…

ያ አላህ…
ፎቶውን ተርጉሙት ብዙ ይናገራል

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
815 viewsedited  01:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 04:39:35
በስመላ የኸይር ነገሮች በአጠቃላይ መክፈቻ
ىســــــــــــــــم الله الرحمں الرحىــــــــــــم
ባለፈው የበስመላህ አምስት የሸሪዓ አህካሞች እፅፋለው ብዬ ነበር…
በስመላ ማለት ዋጂብ፣ ሱና፣ ሀራም፣ ከራሃ፣ ሙባህ የሆነባቸው ቦታዎች አሉት።
1, ዋጂብ … በስመላህ ማለት ግዴታ የሚሆነው ሶላት ላይ ነው። ፋቲሃ ሲቀራ ድምፅ ከፍ ተደርጎም ይሁን ዝቅ ተደርጎ ብቻ በስመላን መቅራት ይኖርበታል።
2, ሱና … በስመላህ ማለት ሱና የሚሆንባቸው ቦታዎች በጣም ብዙ ናቸው። ልብስ ስንለብስ ስናወልቅ ምግብ ሲበላ ወዘተ…
3, ሀራም… በስመላህ ማለት ሀራም የሚሆነው ሀራም ነገር በሚሰራበት ወቅት ነው። ለምሳሌ አላህ ይጠብቀንና ኸምር ሲጠጣ፣ ዚና ሲሰራ… እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ከባድ ወንጀሎች ናቸው። በነዚህ ተፈትኖ የወደቀ ካለ ሲተገብራቸው ቢስሚላሂ ቢል ሌላ ተጨማሪ ወንጀል ይሆንበታል።
4, ከራሃ… በስመላህ ማለት የሚጠላው የሚጠሉ ተግባሮች በሚፈፅም ጊዜ ነው።
5, ሙባህ… በስመላህ ማለት የሚፈቀደው ማንኛውም ሀላል በሆነ ነገር ላይ ብንል ይቻላል።

ከወደዳቹት የልብ ምልክትዋን ይጫኑና ሼር ያድርጉት …

በቀጣይ የበስመላ ትርጉም…

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
823 viewsedited  01:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 23:51:26 አላህ ሆይ! በውዴታህ የምንከብርበት የራህመት እይታህን…

ያ አላህ…
812 viewsedited  20:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 22:52:04
ረመዷን ጓደኛ ለመምረጥ ያግዘናል።

ጥሩ ያልሆኑ ሰዎችን ከተጎዳኘህ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መቀየርህ አይቀርም።

ውሎዋችን እናስተካክል…

https://t.me/Ustaz_ebin_Selman
1.0K viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ