Get Mystery Box with random crypto!

ፂም መላጨት ክፍል አንድ #ፂምን መላጨት #ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑ ይቅርና ጭራሽኑም #ወንጀል | Ustaz kamil Selman أستاذ كامل سلمان

ፂም መላጨት ክፍል አንድ

#ፂምን መላጨት #ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑ ይቅርና ጭራሽኑም #ወንጀል አይደለም። የሚላጭ ሰውም ምንም አይነት ቅጣትም የለበትም። መላጨቱ ሀራም ነው የሚል ኢጅማዕም የለም።

አው መቼም የማይዋሸው ነገር ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፂምን በመልቀቅ አዘዋል። ይህን የሚክድ አንድም ሰው የለም። ነገር ግን #ትዕዛዞች በአጠቃላይ ግዴታ መሆንን ያመለክታሉ  ያለው ማን ነው

በቁርኣንም በሐዲስም ውስጥ ያሉ ትዕዛዛት በአጠቃላይ ለግዴታ ነው የሚል አንድም ዓሊም አታገኙም። ስለዚህ ፂም ማሳደግ ግዴታ ነው አይደለም የሚለው ዝርዝር ውስጥ ከመግባታችን በፊት በቁርኣንና በሐዲስ ውስጥ ያሉ የትዕዛዝ አይነቶችን እንመልከት።

1, ለዋጅብ/ ግዴታነት የሚያስረዱ አሉ።
{وأقيموا الصلاة وآتوا الزكاة}
እዚህ ጋር ሰላት እና ዘካ ዋጂቦች ግዴታዎች ናቸው። ትዕዛዙ ግዴታነትን ስለሚያስረዳ።
2, ትዕዛዝ ሆነው የተፈቀደ /ጃኢዝ/ መሆኑን የሚያመለክቱም አሉ። ለምሳሌ፦
{وإذا حللتم فاصطادوا} {فإذا قضيت الصلاة فانتشروا في الأرض وابتغوا من فل الله}
እነዚህ አንቀፆች የሚያስረዱት መፈቀድን ብቻ ነው። መቼም ሀጅ እንዳለቀ ለማደን ጫካ የሚገባ የለም ግዴታነው ብሎ። የተፈቀደ ማለት መስራቱም መተውም እኩል የሆነ ማለት ነው። ትዕዛዝ ነው። ነገር ግን በመስራትም አጅር የለውም። በመተውም ቅጣት የለውም።
3, ትዕዛዝ ሆኖ ማመላከትን የሚያስረዳ አለ። ለምሳሌ፦
{إذا تداينتم بدين إلى أجل مسمى فاكتبوه}
እዳ መፃፉ ግዴታ አይደለም። ምክንያቱም እዚሁ ቦታ ወረድ ብሎ …
{فإن أمن بعضكم بعضا فليؤدي الذي اؤتمن أمانته}
በማያሻማ ሁኔታ ግዴታ አለመሆኑ ፍንትው አድርጎ አስቀምጦታል። እዚህ ቦታ ትዕዛዙ ምንድ ነው? ከተባለ፤ ለማመላከት ለኦርሻድ ነው ይባላል።

በቁርኣንና በሀዲስ ትዕዛዝ የሚመጣው ለግዴታ እና ለሱና ብቻ አይደለም። በቁርኣን ወይም በሀዲስ ውስጥ ትዕዛዝ ካየህ ከሚከተሉት አንዱ ነው።
ለዋጂብ፣ ለሚወደድ ነገር፣ ለማመላከት፣ አደብ ለማስያዝ፣ ለምርጫ፣ ለምኞት፣ ለማሳነስ፣ እኩል ለማድረግ፣ ለማስፈራራት፣ ለዱዓ፣ ለምክር፣ ለኢልቲማስ፣ ለማስቃት፣ ለማላገጥ፣ ለማዋረድ፣ ለመዘውተር፣ ለመግሰፅ፣ ለቁጭት፣ ለማስጠጋት፣ ለመንገር እና ለሌላም።

እዚህ ቦታ የማወራው ስለ አምር ስለትዕዛዝ ስላልሆነ ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት ምሳሌዎች በቂ ናቸው። የትኛው ዝዕዛዝ ለምን እንደሆነ ሊረዱት የሚችሉት ዑለሞች ብቻ ናቸው። ማንም የተንጣጣ ሁሉ ሊያውቀው አይችልም።

ከዚህ በመነሳት ጺም በማሳደግ የመጣው ትዕዛዝ ለዋጅብ አለመሆኑና ለተኽዪር ወይም ለሱና መሆኑን ማወቅ እንችላለን። በምን መልኩ የሚለው በቀጣይ የምዳስሰው ይሆናል።

እያንዳንዱ ንግግር በቁርኣንና በሀዲስ መረጃ የተደገፈ ነው።

ክፍል ሁለት ይቀጥላል…