2022-08-12 19:37:19
ብሩክ እና ፕሮፌሰር
ቡና እየተፈላ የእጣኑ ጭስ እየተንቦለበለ ፋንዲሻው ዷ ድሽ እያለ ሙልዬ እናታችን የሰራችው አፍንጫን የሚያዞር መኣዛ ያለው ምግብ እየሸተተን ብሎም እየተፍለቀለቀ ወደ ቤት የመጣው ፕሮፌሰርን ጨምሮ ተደማምረው ቤቱን ሞቅ አድርገውታል ።
ይገርማቹሃል የሄድኩበት ቦታ ቅዝቃዜው አጥንት ይሰብራል በዛ ላይ አስሜ ተነስቶብኝ ከሞት ነው የተረፍኩት ግን ጌታ መልካም አይደል የምፈልገውን አግንቻለሁና ደስታዬ ወደር የለውም ።
ብሩክ አባ ምን አገኘህ ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ ነገር ነው ።ለበሽተኞች መፍትሄ የሚሆን ነገር አገኘህ? የነገር ጥያቄውን አስከተለ።
ብሩክ ፕሮፌሰርን በአባትነቱ ቢያከብረውም ካልመሰለው ከመጠየቅ ወደ ኋላ አይልም
አዎ አግንቻለሁ አለው ፕሮፌሰር በቅኔ መናገር ይወዳል። ይገርምሃል ለበሽታ የሚሆን መፍትሄ ለዘላለም የሚሆን ገንዘብ የሚያስገኝ ነገር አግንቻለሁ።
ዋው ደስ ይላል ግን ገንዘብ ለዘላለም አያስፈልግም ይልቅ ለጊዜው የሚያገለግል ማለፊያ ከሆነ ይበቃል ልክ ዲዮጋን( ውሃ እንደሚጠጣበት ቅል አይነት ነገር ካለ ይበቃል የብሩክ ምላሽ ናት!!
ቅሉን መስበሩን ታውቃለህ አይደል? አሉ ፕሮፌሰር ፈገግታቸውን ብልጭ እያደረጉ!!
አዎ አውቃለሁ ግን ብሎ ለምላሽ ተንደረደረ
ሙልዬ አሁን ቡናውን እንጠጣ ውይይቱን ኋላ ትቀጥላላችሁ ብላ ለማስቆም ሞከረች ብሩክ እማ ቆይ አለን !!
አባ እየውልህ በዚህ ምድር ፈታ ብለን ነው መኖር ያለብን በሃይማኖት መታሰር የለብንም ።መፅሃፍ ቅዱስ ብዙ የሚምታቱ ነገሮች አሉት ።ስለዚህ በመፅሃፍ ቅዱስም ሆነ በቅዱስ ቁርዓን መያዝ ያለብን አይመስለኝም!!
መልካም ግን ይህንን አመለካከት ከየት አገኘከው ?
ብዙ አሳብያን በዘመናት ውስጥ የሃይማኖትን ደካማ ጎን ፅፈዋል ። ይህንን ነገር አገናዝቤ የኔም አቋም አድርጌአለሁ ።ይህ አቋሜ ተመችቶኛል !!
ብሩኬ ምን መሰለህ በዘመናት ውስጥ በታሪክ ደካማ እና ጠንካራ ጎኖች ከሁሉም ጎራዎች ነበሩ ።ለፍልስፍናው አለም ብዙ ግብአት በመሆን ያገለገሉ ሃሳቦችን ያበረከቱ እንዳሉ ሆነው ሃሳባችው እሾህ ሆኖ ትውልድ ያመከኑ ሃሳባዊ ከምትላቸው ሰውች ጎራ ሞልተዋል ።ብኩን ዜጋ ግበረ ገብ የጎደለው ከእሱ ውጪ አዋቂ ያለ የማይመስለው ከንቱ ትውልድ ተፈጥሯል ።በእነሱ ሃሳብ ላይ መሰረት አድርገው የተፈለፈሉ የፖለቲካ አስተሳሰቦች እስካውን ላለው የዘመናችን ፈተናዎች ጥንስሶች ነበሩ !!አስፈላጊ ከሆነ ስማቸውን መዘርዘር ይቻላል!!
ሃይማኖት ከሚባለው ጎራም የፅድቅ መንገድ ብቻ ተጉዘዋል ብዬ ማለት አልችልም ።ጦርነት ባርከው ያስጀመሩ የሃይማኖት መሪዎችም አሉ ።
እውነታው ግን መነጋገር ያለብን በሰዎች ላይ ተንጠልጥለን ብቻ መሆን የለበትም ነው። ይልቅ እሳቤያቸው በእውነት መመዘኛ ስንመዝነው የቱ ማለፍ ይችላል የሚለው ላይ ነው።የቱ ነው በጎ አበርክቶት ያለው የቱ ነው የተሻለ ለማህበረሰብም ቢሆን መልካም ውለታ የዋለ ።ይህንን ስልህ ክርስትና በዚህ ሚዛን ይመዘን እያልኩህ አይደለም ክርስትና የራሱ እውነት አለው ስለዚህ ....
ብሩክ ፕሮፌሰርን አቋረጣቸው ያነሳው ነገር ሚያስኬደው ስላልመሰለው የሶቅራጠስን ነጥብ ማስጣያ የሙግት አካሄድ መጠቀም ፈልጓል እናም እንዲህ አለ እውነት ግን ምንድነው?
ፕሮፌሰር ፈገግ አሉ ።መልካም ብለው ሊጀምሩ ሲሉ ምግቡ ይበላ እና ትቀጥላላቹ አሁን እንፀልይ የሊያ ንግግር ነበር ።
ሁሉም አይናቸውን ጨፈኑ ብሩክ ግን የምናደርገውን እያየ ነበር!!
አባት አምላክ ሆይ መታመኛ ነህ ሰው ይታንብሃል መፅናኛ ነህ ተፅናንተንብህ እናውቃለን ጠባቂ ነህ ጥባቆትህን አንክድም !!
ጌታ ሆይ ሰለ ሁሉ እናመሰግነሃለን ከፊት ለፊታችን የቀረበውን ማዕድ ባርክልን አሜን!!
ብሩክ ትንሽ ዋስትና ያጣ ቢመስለውም ፀሎቷን ትኩረት አልሰጠውም !!
ምግብ ቀረበ ጨወታ ደመቀ ቡና ተጠጣ ደስ የሚል ድባብ ቤቱን ሞላው ሰራተኛችን ቡና ልድገም ?
አንገቴን ደፋ ቀና እያደረኩ እሽታዬን አሳወኳት ቡና እኮ ነው!!
ቡና እንደጠጣን በቀጣይ ስለምናወራው ነገር እያሰብኩ ነው።
ምን እሰማ ይሆን?
ይቀጥላል....
211 viewsGirum Difek, 16:37