Get Mystery Box with random crypto!

የክርስትና እውነቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ chtruth — የክርስትና እውነቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ chtruth — የክርስትና እውነቶች
የሰርጥ አድራሻ: @chtruth
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.10K
የሰርጥ መግለጫ

📖መጽሐፍ ቅዱሳዊ📖 የሆኑ መንፈሳዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው❗
📲Join/Subscribe📲 ብለው ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑ!👥
↪Share↩ በማድረግም "የክርስትና እውነቶችን" ለወዳጅዎ ያጋሩ!👇
https://t.me/chtruth 👈

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-16 08:21:45 'ግኙ ፈዋሽ'
ማር 1፡29-34
የኢየሱስ አገልግሎት በመንገድ ላይ ብቻ ሳይሆን ሙክራቭ እየገባም ያገለግል እንደነበር አስቀድመን አይተን ነበር። በዚህ ክፍል ውስጥ ደግሞ፤ ኢየሱስ በእነጴጥሮስና እንድርያስ ቤት ከያዕቆብና ዮሐንስ ጋር ሲገባ እንመለከታለን። የኢየሱስን አገልግሎት ለማግኘት ሰዎች ወደ እርሱ እንደሚሄዱ ሁሉ፤ እርሱም ሊያገለል ወደ ሰዎች ይሄድ ነበር። ኢየሱስ እራሱን ለሰዎች ‘ግኙ’ available ያደርግ ነበር።

ወደነ ጴጥሮስ ቤት ሲገባ የጴጥሮስ አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር። ለጌታም በነገሩት ጊዜ እጇን ይዞ አስነስቷት ወዲያው ተፈውሳ አገለገለቻቸው። ፈውሱ ቅስፈታዊ መሆኑ፣ እግዚአብሔር የሰራው ስራ ለመሆኑ ማስረጃ ነው። የፈውስ አገልግሎት ጸጋ ያላቸው ሰዎች ደግሞም በጌታ የምናምን ሁላችን ይህ አይነት ቅስፈታዊ ፈውስ ይሆን ዘንድ ማመን፣ አጥብቀንም መጸልይ ይኖርብናል። ታድያ ወደ ህመምተኞች በመሄድ! እግዚአብሔር ነገሮችን በዝግታ ሊሰራ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም፣ የሰውን ታሪክ ልክ እንደዚች ሴት በቅስፈት ቀይሮ፤ ከአልጋ ተነስታ ምግብ እንድታሰናዳ ማድረግ ይችላል።

ቁጥር 32 ‘ጸሓይም ገብቶ በመሸ ጊዜ’ ስለሚል ጌታ እስኪመሽ በነጴጥሮስ ቤት የቆየ ይመስላል። ነገር ግን የኢየሱስ ዝና ይወጣ ስለነበር፣ አመሻሽ ላይ ብዙ የታመሙና አጋንንት ያደረባቸውን ሰዎች ወደርሱ አመጡ። የከተማው ሰው ሁሉ (ግነታዊ ዘይቤ ይመስላል)፣ በነጴጥሮስ ቤት ደጅ ተሰበሰቡ፤ ኢየሱስም ከሙክራቭ መልስ፣ እነ ጴጥሮስ ቤት አገልግሎ ሳያበቃ ሌላ አገልግሎት ተጨምሮበት እንኳን በትጋት ያገለግል ነበር። የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፣ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ። አጋንንቶችን ሲያወጣ ግን የሚያስገርመው፣ ስለረሱ እንዲናገሩ አይፈቅድላቸውም ነበር። ይህም የመጣበትን አላማ እንዳይስተጓግልበት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እኛም ይህን ልምድ ወስደን ስለኛ መወራትን መከልከል እንዳለብን አስባለው። በተለይ አጋንንት ሲወጡ፣ "አንተ እኮ አስቸገርሀን፣ አንተ ላይ ያለው ቅባት አደገኛ ነው" እና ሌሎችንም ንግግሮች ልንፈቅድ አይገባም።
482 viewsGirum Difek, 05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 14:01:16
ስለ ኢየሱስ መለኮታዊ ማንነት በጥልቅ ትንታኔ ተዳሷል አውርደው ይጠቀሙ

የክርስትና እውነቶች!!
560 viewsGirum Difek, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:56:57 Miracles today
ባርባራ በነርሲንግ ቤት
ክሬግ በመጻፋቸው መግቢያ ላይ የአንድ ባርባራ የተባለች በዊልቸር የምትሄድ ሴት ታሪክ ያስነብበናል። እርሱ ራሱ ኢእግዚአብሔራዊ በነበረብት ጊዜ በተአምራት የማያምን ሲሆን፣ ወደ ጌታ ከመጣ በኋላ ግን፣ ለመጀመርያ ጊዜ ይህች ሁሌ በእግሯ መራመድ የምትሻዋ ሴት በዊልቸሯ እንዳለች፣ ዶን የተባለ የምጽሀፍ ቅዱስ አስጠኚ፣ ከተቀመጠችበት ሳባት እና “በኢየሱስ ስም ተመላለሺ!” አላት። ሁላችንም መሬት ላይ የምትፈጠፈጥ መስሎን ተሳቀን ስናይ፣ እርሷ ግን እየተንገዳገደች መቆም ቻለች። በቀጣዩ ሳምንት በክራንች መጣች ከዛ በኋላ ግን በትክክል ተፈውሳ በግሯ መራመድ ቻለች።[1]
ልትሞት የነበረችው ባርባራ
የዚች ሴት ታሪክ ደግሞ ለየት ያለ ነው። መልቲፕል ስክሌሮሲስ በተባለ በሽታ ትታመም ነበር፣ እርሱም አገረሸባት እና ከባድ ህመም ውስጥ ከተታት። በመስኮቶቿ ወደ ውጭ እያየች እንደሌላው ሰው መኪና እየነዱ ስራ እየሰሩ መኖርን ከመመኘት በዘለለ ምንም ማድረግ አልቻለችም። ነገር ጌታን በጣም የምትወድ በመሆኗ እንድትኖር የሚያደርጋት ምክንያቷ ነበር። ከ15 እስከ 31 ያለውን የእድሜዋን ክፍል ያሳለፈችው በሆስፒታል ውስጥ ነው። ሌላውን ደግሞ በቤት ውስጥ በመታከም። የፑልሙኖሪ በሽታም ከኒሞኒያ ጋር ተድምሮባት ህይወቷን አክብዷል። ዶ/ር ሃሮልድ አዶልፍ“ካጋጠሙኝ ታካሚዎች፣ ባርባራ፤ በጣም የተሰቃየች እና ተስፋ የተቆረጠባት ናት። ዲያፍራሟ ፓራላይዝድ ሁኗል። አንዱ ሳማባዋ ስራውን መስራት አይችልም፣ ሌላኛው50% ብቻ ይሰራል። ቀረቲቷም አይሰራም። ለሰባት አመታትም ምንም መራመድ አትችልም። እጆቿም አይታዘዙላትም። አይኖቿ ማየት ተስኗቸዋል። የምተነፍስበት ትርይክቶሚ ተተክሎላት ነበር። አንጀትዋ የማይሰሩ ከመሆናቸው የተነሳ ሆዷ ተነፍቷል። ” ብሏል። ከብዙ ተስፋ መቁረጥ በኋላ አንድ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ዶክተሮች ከዚህ በኋላ ሊያዩአት እንደማይችሉና ቤት እንዲወስዷት በዛም ልትሞት እንደምትችል፤ ለቤተሰቧ ነግረው ሸኟት።
ሁለት ወጣቶች ግን እርሷ ታመልክበት ከነበረችው ዌስልያን ቤተ ክርስቲያን ለርሷ የጸሎት ደብዳቤዎችን ይዞ መጥቶ ማንበብ ሲጀመር፣ ድንገት ከሰማይ“ልጄ ተነሺና ተመላለሺ!” የሚል ድምጽ ሰማች። ተሰክቶባት የነበረውን መተንፈሻ እንዲነቅሉላት፣ ፊቷን ስታሳያቸው ነቀሉላት። መናገር ቻለች፣ ድምጹን ወደ ሰማችበት ዘላ ተነሳች። እርሷን ደግፎ ከአልጋ ለማንሳት እንኳን ሶስት ደቂቃ የሚፈጅ ስራ ነበር፣ ያውም በጥንቃቄ፣ አሁን ግን በራሷ ቆመች። እጆቿ እግሯ መንቀሳቀስ ጀመሩ። አባቷ ከውጪ ሲመጣ የሰማው ድምጽ የእህቷ እንጂ የርሷ አልመሰለውም። ቤተሰቦች በመገርም፣ በደስታ ተሞሉ። የምትከታተላት ነርስ፣ ቆማ ስታያት በድንጋጤ፣ በፍርሀት ተሞልታ ጮሀች። ዶ/ር ማርሻል እርሷ እየተራመደች ወደ እርሱ ስትመጣ፣ መንፈስ መሰለችው።“ማንም አብሮት የሚሰራ ሀኪም ለዚህ ምስክር ይሆናል፤ እንደዚህ አይነት አጋጥሞን አያውቅም። ይህ በህክምና የማይቻል ነገር ነው የሆነልሽ። መፈወስሽን እኔ ፈጽሞ እመሰክራለሁ” አለ። ዲያፍራሟ ሰራ፣ ትንፋሿም ተስተካከለ። ቺካጎ ትሪቡን፣ ሌሎችም የቴሌቪዥን ጣብያዎች ይህን ተቀባብለው ዘገቡት። በዲሴምበር2015 እኔ (Keener) ራሰ ቃለ መጠይቅ አደረኩላት። ታሪኩ ካለፈ ቢቆይም፣ አሁን በሞቀ ደስታ ውስጥ ነች። ዶ/ሩም ይህን አረጋገጡልኝ።[2]
[1]Keener, Craig, miracle-today, the supernatural work of God in modern wordl, XI
[2] Keener, Craig, miracle-today, the supernatural work of God in modern wordl, XV

በግሩም ፊዳ
746 viewsGirum Difek, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 09:27:03 መንፈስ ቅዱስ እና እኛ(አማኝ)

ክርስትናን ያለ መንፈስ ቅዱስ ማሰብ ከባድ ነው።ልጅን ያለህ እናት አይነት ነው።

በጥሪ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ 1ኛ በውጫዊ ጥሪ ማለትም በሰዎች ስብከት ,አዋጅ ,ፅሁፍ .....ውስጥ ወንጌል ለሰው ልጆች እንዲደርስ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው። ደግሞ በሰሙት የወንጌል ቃል ሰዎች እንዲነኩ እንዲለወጡ የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው ይህ ደግሞ ውስጣዊ ጥሪ ይባላል ።
ሁለቱ አንድ ሰው በወንጌል አምኖ ንስሃ እንዲገባ እና ጌታን እኖዲቀበል ያደርጉታል ።በዚህ የማያበቃው የመንፈስ ቅዱስ ስራ በክርስቶስ የሚያምኑትን ዳግም እንዲወለዱ ያደርጋቸዋል (ዳግም ይወልዳቸዋል)

የወለዳቸውን አማኞች ደግሞ ዝም አይተዋቸውም ዶሮ ጫጩቶቿን አቅፋ እንደምትከባከብ እንደምታሳድግ ሙቀት እንደምትሰጣቸው ከአደጋ እንደምትጠብቃቸው ....መንፈስ ቅዱስም እንዲሁ ያደርጋል ። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስና አማኝ ጥብቅ ቁርኝነት አላቸው።

መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ

1ኛ ያድራል!! (ይኖራል)

ይህ በብሉይ ኪዳንም ሲሰጠን የነበረ ተስፋ ነው።

“#መንፈሴንም_በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።”
— ሕዝቅኤል 36፥27

“መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
— ሕዝቅኤል 37፥14

መንፈስ ቅዱስ መኖሪያውን በእኛ ውስጥ እንዲያደርግ አብ በክርስቶስ በኩል ታላቅ በረከት (ሀሉን ጠቅላይ በረከት) አድርጎ ሰጥቶናል። አሁን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያዎች ቤተ መቅደሶች ነን!!

“ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው #የመንፈስ_ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 6፥19-20

“የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16

እንዴት ያለ መታደል ነው መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖሩ ከእኛ ጋር ያለው ትልቅ አዋቂ ሃብታም ሰው አይደለም ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ሰውን የፈጠረ አምላክ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ነው ።

በውስጣችን መንፈስ ቅዱስ እንደሚኖር እያሰብን መኖር ይሁንልን አሜን!!!

ይቀጥላል....
536 viewsGirum Difek, 06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 00:14:12 በእንተ ኢሳይያስ 53

ክፍል አራት
(በወንድም ሚናስ)

በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል

ቊጥር ዐሥር

“መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ #ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”

וַיהוָה חָפֵץ דַּכְּאוֹ, הֶחֱלִי--אִם-תָּשִׂים אָשָׁם נַפְשׁוֹ, יִרְאֶה #זֶרַע יַאֲרִיךְ יָמִים; וְחֵפֶץ יְהוָה, בְּיָדוֹ יִצְלָח.

ይሁዲዎች ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ዓመታት ሥጋዊ ልጅ ስላልነበረው ኢሳይያስ 53:10ን “ዘሩን ያያል” የሚለውን ቃል፣ ሊመለከተው እንደማይችል ይናገራሉ፤ ለዚሁም በምክንያትነት የሚጠቅሱት፣ “ዘር” ( זֶרַע “ዜራዕ”) የሚለው ቃል ዅል ጊዜ የሚያመለክተው ሥጋዊ ውልደትን ስለኾነ፣ ትንቢቱ ኢየሱስን ሊመለከት አይችልም ይሉናል። ኾኖም ይህ ሙግት ግን ወንዝ የማያሻግር ድኵም ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ זֶרַע “ዜራዕ” የሚለው ቃል ሥጋዊ ብቻ ሳይኾን መንፈሳዊ ጒዳዮችን ለማመልከት በተምሳሌታዊ አገላለጽ(Metaphorical) ጥቅም ላይ ይውላልና። የተወሰኑትን በዚሁ ከኢሳይያስ መጽሐፍ ሳንርቅ የተወሰኑትን እንመልከት፦

“ኀጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች #ዘር(זֶרַע) ፥ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ፥ ወዮላችኹ! እግዚአብሔርን ትተዋል የእሥራኤልንም ቅዱስ አቃለዋል፥ ወደ ዃላቸውም እየኼዱ ተለይተዋል ።” ኢሳ 1፥4

“ምድርኽን አጥፍተኻልና ፥ሕዝብኽንም ገድለኻልና፥ከነርሱ ጋራ በመቃብር በአንድነት አትኾንም፤ የክፉዎች #ዘር(זֶרַע) ለዘለዓለም የተጠራ አይኾንም።” ኢሳ 14፥20

“የምትሣለቁት በማን ላይ ነው? የምታሽሟጥጡት ማንን ነው? ምላሳችኹንስ አውጥታችኹ የምታሾፉት በማን ላይ ነው? እናንት የዐመፀኞች ልጆች፣ የሐሰተኞች #ዘር(זֶרַע) አይደላችኹምን?” ኢሳ. 57፥4

ኢሳይያስ የገቢር ኀጢአትን በመሥራት አምላክን የሚያሳዝኑ ግለሰቦችን የኅሊና ዝቅጠትን ለመግለጽ “ዘር” ( זֶרַע “ዜራዕ”) የሚለውን ቃል እንደሚጠቀም ከላይ ከተጠቀሱት ምንባባት መረዳት ይቻላል። ይሁዲ ወገኖቻችን፣ እንደ ክፋት ፤ ዐመፅ ፤ እና ርኵሰት ያሉ መጥፎ ባህርያት ሥጋዊ ልጆች እንደ ሰው ይወልዳሉ፤ ካላሉን በስተቀር “ዘር” ( זֶרַע “ዜራዕ”) በተዘረዘሩት ምንባባት ውስጥ አካላዊ ውልደትን ሊያመለክት አይችልም።

በዐጭሩ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53 መሲሑ ስለ ኀጢአታችን መከራ በመቀበሉ የዘለዓለም ቤዛነት እንዳስገኘልን የሚያመለክት ድንቅ ምንባብ እንጂ፣ ፈጽሞ ስለ ሕዝበ እሥራኤል የተነገረ መለኮታዊ ትንቢት አይደለም፤ ይህ ተከታታይ ጽሑፋችን መሠረት አድርጐ የተነሣውም ምዕራፉ ለመሲሑ እንጂ ለብዜት አካላት የተነገረ አይደለም በሚል ነው፤ ለዚህም ይሁዲ ወገኖቻችን ለሙግት ዋቢ የሚያደርጓቸውን አራት ቊጥሮችን በተከታታይ ዐቅርበናል። ሀሼም አዶናይ ቢፈቅድ ወደፊት በምዕራፉ ላይ ያሉትን ዐሥራ ኹለቱንም ቍጥሮች የምንመለከት ይኾናል፤ ለአኹኑ ግን በዚሁ ይብቃን።
515 viewsGirum Difek, 21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 00:13:53 በእንተ ኢሳይያስ 53

ክፍል ሦስት
(በወንድም ሚናስ)

በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል

ቍጥር 9

“በአፉ ተንኰል ሳይገኝበት፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ #አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋር ኾነ።”

וַיִּתֵּן אֶת-רְשָׁעִים קִבְרוֹ, וְאֶת-עָשִׁיר #בְּמֹתָיו; עַל לֹא-חָמָס עָשָׂה, וְלֹא מִרְמָה בְּפִיו.

ይሁዲ ወገኖቻችን በዚህ ክፍል የሚያቀርቡት ሙግት בְּמֹתָיו “ቤሞታው” የሚለው ስም ብዜት ስለኾነ፣ ዕብራይስጡ የሚለን “አሟሟቱ” ሳይኾን “አሟሟታቸው” የሚል ነው፤ ስለዚህ ቊጥሩ ካንድ በላይ ለሚኾኑ አካላት የተነገረ እንጂ ነጠላ አካልን ይኸውም መሲሑን የሚመለከት አይደለም ይሉናል። ኾኖም ግን የይሁዲ ወገኖቻችን ሙግት ተቀባይነት የማያገኝበት ምክንያት፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው ዕብራይስጥ ኾነ በዘመናዊው ዕብራይስጥ ዘንድ፣ በብዙ ቍጥር የተጻፈ ቃል፣ ዐልፎ ዐልፎ አንድን አካል ብቻ ሊያመለክት የሚችልበት አግባብ አለ፤ ለምሳሌ פניו “ፓናይን”፣ רחמים “ራሓሚም”፣ הָאֲדֹנִ֑ים “ሃአዶኒም” የሚሉት ቃላት የብዜት ቃላት ቢኾኑም፣ በብዙ ቦታዎች ነጠላ የኾኑ ማጣቀሻዎችን ሲያመለክቱ ይስተዋላል። የሴማዊ ቋንቋዎች ተመራማሪ እና የነገረ መለኮት ጸሓፊ የኾኑት፣ አይሁዳዊው ሊቅ ዶክተር ማይክል ብራውን “የብዜት ቃላት ለነጠላ አካል መጠቀም፣ በቋንቋው ዓለም(በዕብራይስጥ) ዠማሪ ለኾኑ ተማሪዎች እንኳ ሳይቀር እንግዳ ያልኾነ የተለመደ የሰዋስው ሥርዐት ነው” በማለት ይናገራሉ። በማስከተልም ሊቁ “በብሉይ ኪዳን ውስጥ ‛ሞት’ የሚለው ስም በብዙ ቍጥር የተጠቀሰበት ኹለት ጥቅሶች የሚገኙ ሲኾን፤ ይኸውም ኢሳ. 53፥9 እና ሕዝቅኤል 28፥10 ናቸው፤ ታዲያ በሕዝቅኤል 28፥10 ነጠላ ሞትን (תָּמוּת “ቴሞት” ) ለማመልከት የብዜት አገላለጽን ( מוֹתֵי “ሞቴይ”) እንደተጠቀመ ማስተዋል ያስፈልጋል።” በማለት בְּמֹתָיו “ቤሞታው” የሚለው የብዜት ቃል ነጠላ አካልን ሊያመልክት እንደሚችል በስፋት ይሞግታሉ[1]

በዘመናችንም ኾነ በጥንት ዘመን በነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራት ደግሞ ይህን ጥቅስ እንዴት እንደተረዱት ጠቅለል ባለ መልኩ ደግሞ እንመልከት፡-

፩.በሙት ባሕር ጥቅሎች(መሲሑ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት የነበረ) ላይ እንደሚታየው፣ ይህ ጥቅስ የተጻፈው በነጠላ ግስ፣ “አሟሟቱ” (“בומתו”) ተብሎ ነው።

፪.የሰባ ሊቃናት ትርጕም አዘጋጆችም የዕብራይስጡ ምንባብ፣ ስለ አንድ አካል እየተናገረ መኾኑን በመረዳት፣ በነጠላ “አሟሟቱ” ( ἀντὶ τοῦ θανάτου “አንቲ ቱ ታናቱ” ) ብለው ተርጒመው አስቀምጠዋል።

፫.ታርጒም ዮናታን ቤን ዑዝኤል ወደ አረማይክ በተተረጐመው ሥራ አሟሟቱ ብሎ በነጠላ (בְמוֹתָא) ገለጸው እንጂ፣ በብዙ ቊጥር (בְמוֹתָיא) ክፍሉን አላስቀመጠውም።

ይቀጥላል።

1.Michael L. Brown, Answering Jewish Objections to Jesus, Volume Three – Messianic Prophecy Objections: ገጽ. 49-57.
399 viewsGirum Difek, 21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:07:33 ኢየሱስ ከሁለት ሺህ አመት በፊት ስለመኖሩ ታሪካዊ ማስረጃዎች

1. ጳውሎስ ተአማኒ ጽሁፎች አሉት ቢያንስ ከጻፋቸው 7/6ቱ በአብዛኛው ሊቃውንት ዘንድ ተአማኒነት አላቸው። እናም ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ ህይወት በጽሁፎቹ አስፍሯል። ከኢየሱስ የቅርብ ደቀመዛሙርት እና የስጋ ዘመዶቹ ጋር ተገናኝቶ ያውቃል። ስለ ኢየሱስ ትምህርቶችንም አስተምሯል።

2. አራቱ ወንጌላት ጥንታዊ እና ለኢየሱስ የቀረቡ፣ በአይን እማኞች የተጻፉ ዘገባዎች ናቸው። የወንጌል ጸሀፊዎች ትውፊትን ቀይረዋል ማለት ሊቻል ይችላል። ነገር ግን እነርሱን ማን ተጽዕኖ ሊፈጥርባቸው ይችላል?

3. የመጀመርያው ክፍለ ዘመን የአይሁድ የታሪክ ምሁሩ፣ ጆሴፈስ ስለ ኢየሱስ በአንቲኪዩቲው 18፡63 እና 64 የጻፈው ትልቅ ማሰጃ ነው። ( [63] Now there was about this time Jesus, a wise man, if it be lawful to call him a man; for he was a doer of wonderful works, a teacher of such men as receive the truth with pleasure. He drew over to him both many of the Jews and many of the Gentiles. He was [the] Christ. And when Pilate, at the suggestion of the principal men amongst us, had condemned him to the cross, those that loved him at the first did not forsake him; for he appeared to them alive again the third day; as the divine prophets had foretold these and ten thousand other wonderful things concerning him. And the tribe of Christians, so named from him, are not extinct at this day.)

4. አዳዲስ የእምነት እንቅስቃሴዎች ኢየሱስን አልሰረዙትም። ነገር ግን ስለሱ አስተምረዋል። ኖስቲካውያን፣ አሪዮሳውያን፣ ዶሴቲካውያን... ወዘተ

5. ኢየሱስ የለም ብለው የተነሱ አካላት፣ አጥጋቢ ትወራ ማቅረብ አልቻሉም።

6. በዚህም ዘመንና ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን በአንድ ድምጽ ይስማማሉ። ለዘብተኞች እና ኢእግዚአብሔራውያንን ጨምሮ ትንሳኤው ላይ እምነት ባይኖራቸውም፤ በሂስቶሪካል ኢየሱስ ያምናሉ። ለምሳሌ ባርት ኤርማን።

Michael Bird, Historical Jesus, early Christianity history .Jesus mysticism (paraphrased)
Flavius Josephus, Antiquities of the Jews
William Whiston, A.M.
407 viewsGirum Difek, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:06:51 በእንተ ኢሳይያስ 53

ክፍል ኹለት
(በወንድም ሚናስ)

በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል

የክርስትናን አስተምህሮ የማይቀበሉና የማያምኑ ይሁዲ ወገኖቻችን፣ ምዕራፉ ስለ መሲሑ ሳይኾን ሕዝበ እሥራኤልን ይመለከታል፤ ለማለት ምርኵዝ ከሚያደርጐቸው ምንባባት መኻከል፣ በዛሬው ጥናታችን አንዱን የምንመለከት ይኾናል።

ቊጥር ስምንት

“በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኀጢአት ተመቶ፣ ከሕያዋን ምድር #ርሱ እንደ ተወገደ፣ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?”
מֵעֹ֚צֶר וּמִמִּשְׁפָּט֙ לֻקָּ֔ח וְאֶת־דּוֹר֖וֹ מִ֣י יְשׂוֹחֵ֑חַ כִּ֚י נִגְזַר֙ מֵאֶ֣רֶץ חַיִּ֔ים מִפֶּ֥שַׁע עַמִּ֖י נֶ֥גַע #לָֽמוֹ

ከላይ በተመለከትነው ቊጥር የይሁዲ ወገኖቻችን ሙግት የሚከተለው ነው፤ ክርስቲያኖች “ርሱ” ብለው በነጠላ ተውላጠ ስም የተረጐሙት ቃል לָֽמוֹ “ላሞ” የሚል የብዜት ቃል ሲኾን ትርጒሙ “እነርሱ” ማለት እንጂ “ርሱ” ማለት አይደለም፤ ስለዚህ ትንቢቱ ለብዜት አካላት እንጂ፣ አንድን ግለሰብ ለማመልከት የተነገረ አይደለም ይላሉ። ኾኖም ግን ይህ ይሁዲ ወገኖቻችን ሙግት ቢያንስ በሚከተሉት ሦስት መሠረታዊ ምክንያቶችን ያላገናዘበ ነው።

፩. לָֽמוֹ “ላሞ” የሚለው ተውላጠ ስም ብዜትን ኾነ፣ ነጠላ ቊጥርን ሊያመለክት የሚችልበት አግባብ አለ፤ ለምሳሌ በዚሁ በትንቢተ ኢሳይያስ ክፍል לָֽמוֹ “ላሞ” የሚለው ተውላጠ ስም ነጠላ አካልን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፤ አስረጅ፦ “...ከዚሁ ጠርቦ አምላክ ያበጃል፤ ያመልከዋል፤ ጣዖትን ይሠራል፤ ወድቆም #ለርሱ(ላሞ) ይሰግድለታል።” ኢሳ.44፥15

፪.የሰባ ሊቃናት ትርጒምም “ወደ ሞት ተወሰደ” (εἰς θάνατον “ኤይስ ታናቶን”) ብሎ በነጠላ ሐረግ አስቀመጠው እንጂ፣ “ወደ ሞት ተወሰዱ” ብሎ ክፍሉን በብዜት ሐረግ አልተረጐመውም ።

፫. ዐዲሱ የአይሁዳውያን ማኅበረሰብ ኅትመት፣ በመባል የሚታወቀው በአይሁዳውያን ሊቃውንት በተዘጋጀው ቅጂ፣ עַמִּ֖י נֶ֥גַע לָֽמוֹ “ዓሚይ ኔጋዕ ላሞ” የሚለውን የዕብራይስጥ ሐረግ፣ “ስለ ሕዝቡ ተመቶ” በማለት አንድን አካል በሚመለከት መልኩ ተተርጒሞ እናገኛለን።

ይቀጥላል።
325 viewsGirum Difek, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:06:51 በእንተ ኢሳይያስ 53
ክፍል አንድ

(በወንድም ሚናስ)

በስመ እግዚአብሔር መሓሪ ወመስተሣህል

ኢሳይያስ 53 ስለ መሲሑ ሞት እና ቤዛነት የሚናገር ድንቅ ምንባብ ቢኾንም፣ በዘመነኞቹ የይሁዲ ቤተ እምነት አማኒያን ዘንድ፣ ምዕራፉ እየተናገረ ያለው ስለ መሲሑ ሳይኾን፣ ሕዝበ እሥራኤል በዓለም ስለሚደርስበት መከራ የሚመለከት ትንቢት ነው ብለው ይከራከራሉ፤ ኾኖም ግን የዚህን ትርጓሜ ትኽክለኝነት ለማጣራት ከምዕራፉ ዐውድ ውጪ ወጣ በማለት እንደ ሚሽና፣ ታልሙድ፣ ሚድራሺም...ወዘተ ያሉ ጥንታዊ የይሁዲ መዛግብቶችን ብንመለከት ትንቢቱ ስለ ሕዝበ እሥራኤል ሳይኾን፣ በተቃራኒው ስለ መሲሑ የሚናገር መኾኑን ከትበው አስቀምጠዋል። ይህ ብቻም አይደለም፣ ከመኻከለኛው ክፍለዘመን በፊት የነበሩ የአይሁድ ሊቃውንት ዘንድ ስለ ሕዝበ እሥራኤል የተነገረ ነው የሚለው አንድምታ የማይታወቅ ባዕድ ትርጓሜ ነበር ። ለምሳሌ በ1050 ዓ.ም አካባቢም ረሺ ኢሳይያስ 53፣ ስለ ሕዝበ እሥራኤል የተነገረ ትንቢት እንደኾነ ሲናገሩ፣ እንደ ማይሞኒደስ ያሉ ስመጥር የአይሁድ ረቢዎች ይህ ዐዲስ ትርጓሜ እንጂ የጥንታዊ ሊቃውንትን አንድምታ ያላገናዘበ መኾኑን በመናገር ስሕተት መኾኑን አረጋግጠዋል። ጥንታዊ ረበናተ አይሁድ ይህ ትንቢት ለነጠላ አካል እንጂ፣ ለብዜት የተነገረ አለመኾኑን ከተናገሩት መኻከል የተወሰኑትን ለመመልከት ያኽል፦

°ታርጒም ዮናታን ኢሳይያስ 53 ስለ መሲሑ መኾኑን ተናግሯል፤ (ለነጠላ አካል መኾኑን ልብ ይሏል)።

°ታልሙድ በዐውዱ የተጠቀሱትን ዐሳቦችን ከመዘርዘር ባለፈ በአንድም ቦታ ላይ ኢሳይያስ 53 ሕዝበ እሥራኤልን የሚመለከት ነው አላለም።

°የኢየሩሳሌም ታልሙድ ኢሳ. 53፥12 ለረቢ አኪቫ የሚመለከት ሲኾን(Tractate Shekalim 5:1)፣ የባቢሎናዊው ታልሙድ ደግሞ ኢሳ.53፥4 ለመሲሑ(Sanhedrin 98b)፣ ቍጥር 10 (Berakhot 5a) እና ቍጥር 12 (Tractate Sotah 14a) ደግሞ ለሊቀ ነብያት ሙሴ ይጠቀማል። ሚድራሽ ራባህ ደግሞ ኢሳ.53፥5 መሲሓዊ ትንቢት መኾኑን ሲናገር (Ruth Rabbah 2:14)፣ ዐውደ ንባቡ ሕዝበ እሥራኤልን የሚመለከት ነው አላለም።

ይቀጥላል።
318 viewsGirum Difek, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ