Get Mystery Box with random crypto!

እውነት ለሁሉ [truth for all]

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnet_lehulum — እውነት ለሁሉ [truth for all]
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewnet_lehulum — እውነት ለሁሉ [truth for all]
የሰርጥ አድራሻ: @ewnet_lehulum
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.95K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ዓላማው በማስረጃና በመረጃ በመታገዝ እውነትን ከውሸት በመለየት፣ በአላህ ፈቃድ በጨለማ የሚኖሩ ወገኖችን ብርሃን ወደሆነው ኢስላም መጣራት ነው።
قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ
[ ሱረቱ ሰበእ - 49 ]
«እውነቱ መጣ፡፡ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ)» በላቸው፡፡

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-24 12:55:52 የፈጣሪ ቃል ወይስ የግል ደብዳቤ !

ትዝብት ከብዙ በጥቂቱ

1ኛ ቆሮንቶስ 16 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ እስጢፋኖስ፣ ፈርዶናጥስና አካይቆስ በመምጣታቸው ደስ ብሎኛል፤ ምክንያቱም እናንተ እዚህ ባለመኖራችሁ የጐደለኝን አሟልተዋል፤


¹⁹ በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል።
²⁰ ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።

2ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።

ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ እንዲሁም ወንድሜን፣ የሥራ ባለደረባዬንና አብሮኝ ወታደር የሆነውን፣ በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲንከባከበኝ የላካችሁትን፣ የእናንተ መልእክተኛ የሆነውን አፍሮዲጡን መልሼ እንድልክላችሁ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
²⁶ እርሱ ሁላችሁንም ይናፍቃልና፤ መታመሙን ስለ ሰማችሁም ተጨንቆአል።
²⁷ በርግጥም ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ምሕረት አደረገለት፤ በሐዘን ላይ ሐዘን እንዳይደራረብብኝ፣ ለእኔም ጭምር እንጂ ለእርሱ ብቻ አይደለም።

2ኛ ጢሞቴዎስ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ለጵርስቅላና ለአቂላ፣ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ።
²⁰ ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቶአል፤ ጥሮፊሞስም ስለ ታመመ በሚሊጢን ትቼዋለሁ።
²¹ ከክረምት በፊት እዚህ ለመምጣት የተቻለህን አድርግ። ኤውግሎስና ጱዴስ እንዲሁም ሊኖስ፣ ቅላውዲያና ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።

1ኛ ቆሮንቶስ 16 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በመቄዶንያ በኩል ማለፌ ስለማይቀር፣ መቄዶንያ ከደረስሁ በኋላ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
⁶ ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጒዞዬ እንድትረዱኝ፣ እናንተ ዘንድ እቈይ ይሆናል፤ ምናልባትም ክረምቱን ከእናንተ ጋር እሰነብት ይሆናል።
⁷ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጐበኛችሁ አልፈልግም፤ ጌታ ቢፈቅድ ረዘም ላለ ጊዜ እናንተ ዘንድ ለመሰንበት ተስፋ አደርጋለሁ።


¹² ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፣ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።

2ኛ ጢሞቴዎስ 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ፣ ትቶኝ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአልና። ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶ ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፤
¹¹ ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎቴ ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋር ይዘኸው ና።
¹² ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ።
¹³ ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።


ከዛም ይሉሀል የፈጣሪ ቃል ነው ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ነው እንዲህ ብሎ የፃፈው !

ፍርድ ለህሊና

በወንድም ሀቢብ

https://t.me/ewnet_lehulum
634 views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 06:12:09
ለክርስቲያኖች መልስ የሚሰጥበት እና ዐይናቸው በጌታ አምላክ ፍቃድ የሚከፈትበት አዲስ ቻናል በብርቱ ወንድሞች ተከፍቶ አገልግሎቱን "ሀ" ብሎ ጀምሯል። ከእናንተ የሚጠበቀው ሊንኩን ተጭኖ መግባት ብቻ ነው።

t.me/answeringchristianity
351 views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 13:15:42
@ewnet_lehulum

ጉዳዩ ማርቆስ 16 ይመለከታል

መጽሐፍን(bible) ከፍቼ ሳነብ ያገኘሁን ላጋራቹህ ብዬ ነው ከዚህ ቀደም በብዙ ወንድሞች በተለይም በወንደም ሳላህ
<< ተጫን >> በጉዳዩ ላይ ርዕስ ሰጥተው ጽፈዋል ከላይ ሊንካቸውን አስቀምጫለሁ ገብታቹህ ኮምኩሙ ።

ከላይ በላኩት ፎቶ ላይ ታድያ የኛው ሀገር የመጽሐፍ ጸሀፊያን ይሄን ሀቅ ፍንትው አድረገው በመፅሀፉ የግርጌ ማስተዋሻ ላይ አስፍረዋል።

ክርስቲያን ወገኖች ለናንተ ያለኝ መልዕክት እባካቹሁ ነገርን ጠበቅ አድርጋችሁ መጠየቅ ጀምሩ ፊደል መቁጠር ሀቅን ለማወቅ ፋይዳ ከሌለው መማሩ ምን ጠቀመ ?

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራቹህ

ወሰላሙ አለይኩም

በወንድም ሀቢብ

https://t.me/ewnet_lehulum
759 viewsedited  10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 08:39:33 ለምኖ ምላሽ ያጣው አምላክ !

መዝሙር 37
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁹ የጻድቃን መድኃኒታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።
⁴⁰ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከኃጢአተኞችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋል፥ በእርሱ ታምነዋልና።

ማርቆስ 14 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስንም ይዞ ሄደ፤ እጅግ ያዝን ይጨነቅ ጀመር።
³⁴ ደግሞም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ እዚሁ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።

አምላክ ነብሱ እስክትወጣ ይጨነቃል ያዝናል ?! ምክንያቱም ሊገድሉት እና ሊሞት ስለሆነ ?!

ጥያቄ

ከሶስት ቀን ሶስት ለሊት በኋላ ክርሰቲያኖች እንደሚያስቡት ሞትን ድል አድርጎ እንደሚያርግ ኢየሱስ አላወቀም ነበር ? ምንድን ነው ያስደነገጠው ያስጨነቀውስ ያሳዘነው ፍላጎቱ ወደዚች ምድር ሰው ሆኖ መጣ የምትሉን ለሰው ልጆችን ሀጢያት ሊሞት ሊቸነከር ሊሰቀል አልነበር ?

³⁵ ጥቂት ዕልፍ ብሎም በምድር ላይ በመውደቅ ቢቻል ሰዓቱ ከእርሱ እንዲያልፍ ጸለየና፣

“አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።”
— ማርቆስ 14፥36

“እንደ ገናም ሄዶ መጀመሪያ የጸለየውን ደግሞ ጸለየው።”
— ማርቆስ 14፥39 (አዲሱ መ.ት)

ከቀጣዩ ክፍል እንደምንረዳው የርሱ ፍላጎት ተዋርዶ ተቸንክሮና ተሰቅሎ መሞትን ከርሱ እንዲነሳ ነበር "ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ" ደጋግሞም የሚለምነው ይሄንኑ ነው ።

ኢየሱስ ለምኖ ጠይቆ ምላሽን ያገኝ ነበርን ?!

ዮሐንስ 11 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴¹ ኢየሱስም “አባት ሆይ፤ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ * ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ * ፤ ይህን መናገሬ ግን በዚህ የቆሙ ሰዎች አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ ነው።”

ሁልጊዜም እንደሚሰማ መናገሩ ይሰመርበት!

“ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋር አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ * ተሰማለት *።”
— ዕብራውያን 5፥7 (አዲሱ መ.ት)

ፍላጎቱ ጸሎቱ "ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ" ነበር

“ኢየሱስም እንዲህ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን? አላቸው፤ “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማእዘን ራስ ሆነ፤’”
— ማቴዎስ 21፥42 (አዲሱ መ.ት)

መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ { *አልሞትም* } በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
¹⁸ መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።
¹⁹ የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
²⁰ ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ ወደ እርስዋ ጻድቃን ይገባሉ።
²¹{ *ሰምተኸኛልና* }፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
²² ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤


وَقَوْلِهِمْ إِنَّا قَتَلْنَا الْمَسِيحَ عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ رَسُولَ اللَّهِ وَمَا قَتَلُوهُ وَمَا صَلَبُوهُ وَلَٰكِن شُبِّهَ لَهُمْ ۚ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِيهِ لَفِي شَكٍّ مِّنْهُ ۚ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

«እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን» በማለታቸውም (ረገምናቸው)፡፡ አልገደሉትም አልሰቀሉትምም፡፡ ግን ለእነሱ (የተገደለው ሰው በዒሳ) ተመሰለ፡፡ እነዚያም በእርሱ ነገር የተለያዩት ከእርሱ (መገደል) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራቹህ እኛንም ያጽናን
አሚን!

በወንድም ሀቢብ

@ewnet_lehulum
1.0K viewsedited  05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 13:20:24
ንቁ !

ጳጳስ ቦኒፌስ VIII

" ልብ በል ሁሉም መለኮታዊ ህጎች ተብለው የሚታሰቡት የሰዎች ፈጠራ ነበሩ ተራውን ህዝብ በመልካም ባህሪ ለመጠበቅ ሰዎችን በገሀነም ቅጣት ለማስፈራራት የነበሩ ናቸው፤ እግዚአብሔር በተመሳሳይ ሰዐት አንድና ሦስት መሆኑን ማመን ወይም ድንግል ልጅ እንደወለደች ወይም አምላክ ሰው ሆነ ወይም ኅብስት ወደ ክርስቶስ ሥጋ ሊለወጥ እንደሚችል ወይም በዚያ ይሆናል ብሎ ማመን “ጅልነት” ነው። በቀጣይም ሕይወት ይሁን ። " እኔ የማምነው የማስበው እያንዳንዱ የተማረ እውቀት ያለው ሰው እንደሚያምነው እንደሚያስበው ነው" ነገር ግን እውቀት አልባ የሆኑ በሌላ ያምናሉ ።"መናገር ያለብን እውቀት አልባ እንደሆኑት ነው፣ የምናምነውና የምናስበው ግን እንደ ጥቂቶች ነው"

( Age of faith (chap. XXIX),
the story of civilization, by durant)

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራችሁ እኛንም ያጽናን
አሚን !

ወንድም ሀቢብ

@ewnet_lehulum
722 viewsedited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 23:41:39 ነጥብ ሁለት
"አካል ጉዳተኞች"

ወዳጄ ፈጣሪ ሲፈጥርዎት የማታማርጧቸው ነገሮች ቢኖሩ እንዲህ አይነት ነገሮችን ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ሠው ወዶና ፈቅዶ ሴት ወይም አካል ጉዳተኛ የሚሆን የለም። ታዲያ ፈጣሪ በመረጠልን ሁኔታ እንዴት መገለልና የበታችነት ስሜት እንዲሰማን ይደረጋል? እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ከሄድን እውር፣ አንካሳ፣ አፍንጫ ደፍጣጣ(ምናልባት ጥቋቁሮችን)፣ ትርፍ አካል ያለው፣ ጎባጣ፣ ድንክ፣ አይነ መጭማጫ(ቻይናና ጃፓኖችን)፣ እከካም፣ ቋቁቻም……እነዚህን ሁሉ በግልፅ ያገላቸዋል፦

ዘሌዋውያን 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
¹⁷ ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ።
¹⁸ ዕውር፥ ወይም አንካሳ፥ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ፥ ወይም ትርፍ አካል ያለው፥
¹⁹ ወይም እግረ ሰባራ፥ ወይም እጀ ሰባራ፥
²⁰ ወይም ጐባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዓይነ መጭማጫ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም ጃንደረባ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ።
²¹ ከካህኑ ከአሮን ዘር ነውር ያለበት ሰው የእግዚአብሔርን የእሳት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ፤ ነውረኛ ነው፤ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ።

ወዳጄ ምናልባት እርስዎም በሆነ አጋጣሚ ብልትዎ ቢቀጠቀጥ ወይም ቢቆረጥ ከአምላክዎ ቤት ድርሽ ማለትም ሆነ መጸለይ አይችሉም፦

“ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።”
— ዘዳግም 23፥1


እንዴት ነው ነገሩ ሆሆ!? ፀሎትም በብልት ሆነ እንዴ ማለትዎ አይቀርም ነገር ግን ነገሩ ወዲህ ነው። የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሐፊ አካል ጉዳተኞችን ከማበረታታት ይልቅ እንድንፀየፍ ስለፈለገ ነው።

የሠው ልጅ ፈጣሪው ዘንድ በውበትና በአካል ቁመናው ነው መለካት ያለበት ወይስ ለአምላኩ በታዛዥነቱና በቀናነቱ? ወዳጄ እርስዎም ምናልባት አፍንጫዎ ደፍጠጥ ያለ ይሆናል፣ አይንዎም ተመጫምጮ ሊሆን ይችላል፣ ኧረ ድንክየም ሊሆኑ ይችላሉ፣ ብልትዎም ላይ አደጋ አጋጥምዎት ሊሆን ይችላል። ታዲያ እርስዎ በእንደዚህ አይነት ሠዎች ቦታ ቢሆኑና ቢገለሉ ምን ይሰማወታል? በኢስላም ግን የሠው ልጅ የሚበላለጠው በመልክና በውበቱ ሳይሆን ፈጣሪውን በመፍራቱ ብቻ ነው፦

The Prophet (s) also said: Surely all of mankind – from the time of Adam until our time – are like the teeth of a comb (all equal to one another) and there is no greatness for an Arab over a non-Arab and no greatness for a red-skinned person over a black-skinned person, except due to one’s consciousness of Allah. (Ikhtisās, p. 341; volume. 22, p. 347)

ነብዩ "ﷺ" እንዲህ ብለዋል፡- ከአዳም ጀምሮ እስከ ዘመናችን ያሉ የሰው ልጆች በሙሉ እንደ ማበጠሪያ ጥርስ እኩል ናቸው። ለአረብ ዐረብ ባልሆነው ሰው ላይ ምንም ብልጫ የለውም። ነጭ የቆዳ ቀለም ያለው ከጥቁሩ በላይ ምንም ብልጫ የለውም በአላህ ፍራቻ ቢሆን እንጂ። (ኢኽቲሳስ፣ ገጽ 341፣ ቅፅ 22፣ ገጽ 347)


ነጥብ ሦስት
"ሕፃናት"

ሕፃናት ማለት ምንም የማያውቁ ንፁህና ከኃጢአት የፀዱ ናቸው። ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ አይነት ነገር አይቀበልም ይልቁንስ አንድ ሕፃን በማያውቀው ነገር ይወነጀላል ይፈረጃል። ለምሳሌ አንዲት ሴት ደቅላ ልጅ ብትወልድ ያ ሕፃን እንዴት ተጠያቂ ይሆናል? ምክንያቱም የሚያወቀው ነገር ስለሌለ ተጠያቂዎቹ ወላጆቹ ብቻ መሆን አለባቸው። ነገር ግን ባይብል በዚህ መልኩ የተወለደ ሕፃንን ወደ እግዚአብሔር ጉባዔ አይግባ እንደውም እስከ አስረኛው ትውልዱ ድረስ መግባት የለበትም ይለናል፦

“ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።”
— ዘዳግም 23፥2

ህፃናቶች በአለት ላይ ይፈጥፈጡም ይላል፦

“ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው።”
— መዝሙር 137፥9

ልጁን በበትር የማይመታ ሠው ልጁን አይወድም ስለዚህ በበትር ይገስፀው በማለት ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትናና የሞራል ውድቀት እንዲደርስ ያበረታታል።

“በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጻዋል።”
— ምሳሌ 13፥24

ከላይ እንዳየነው መፅሐፍ ቅዱሱ የዚህን ያህል ሴቶችን፣ ሕፃናቶችንና አካል ጉዳተኞችን "Marginalized" ያደርጋል ወይም ያገላል። መቼም እርስዎ በእነሱ ቦታ ቢሆኑ ምን ያህል እንደሚሰማወት መገመት አይከብድም። እና ወዳጄ አሁን ይህን መፅሐፍ መለኮታዊ ነው ብለው ይቀበሉት ይሆን?


Kedir Ibnu Muhammad

https://t.me/ewnet_lehulum
1.3K views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 23:41:39 መገለል(Marginalization) በባይብል!

ወዳጄ ዛሬ ከእኔጋ በመሆን ውሃን ከጡሩ ነገርን ከስሩ ነውና መገለል ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን እንዲሁም ባይብልስ በምን አይነት መነጠር ይመነጥረዋል ወይስ ያስጠረጥረዋል የሚለውን ከስር መሰረቱ እንመለከተዋለን።

"Marginalization" የሚለው ቃል "Margo" ከሚለው የላቲን ቃል የመጣ ሲሆን የተለያዩ ፍቾችን ይወስዳል። ለምሳሌ ጠርዝ፣ ጫፍ፣ ዳርቻ…… የሚሉ ትርጉሞችኝ ይዟል። ነገር ግን በ1928 አሜሪካዊው ሶሺዮሎጂስት "Robert Park" የሚባል ሠውዬ ይህን ቃል ግለሰቦችን ወይም ትንሽ ማህበረሰቦችን በባህል፣ በፆታ፣ በዕድሜ እንዲሁም በአካል ጉዳተኝነትም ቢሆን ከማህበረሰቡ የበታችነት ስሜትን አስይዞ ከቁጥር አለማግባት ወይም የበታች አድርጎ ማግለልን ያመለክታል ብሎ ደምድሟል።


ወዳጄ ማግለል የሚለውን ቃል በዚህ ልክ በወፍ በረር ለቅምሻ ያህል ከስር መሠረቱ ከዳሰስን ዘንዳ ወደ አንኳር ነጥባችን ብንመለስ መቼም ቅር አይልወትም አይደል!? መፅሐፍ ቅዱስ ሴቶች፣ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞችን ማግለልን ያበረታታል። በተለይ ሴቶችና አካል ጉዳተኞችንማ አይጠይቁኝ እንደ ርኩስ ይፀየፋቸዋል ነው ምልዎት! እርስዎ የፀባይ ባለቤት ከሆኑ ብቻ ነጥብ በነጥብ ለማየት እንሞክራለን።

ነጥብ አንድ
"የሴቶች መገለል"

ሴቶች በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተጠቀሰው ደካማና ከወንድ በታች የሆኑ ፍጥረት ናቸው። ይሄን የምልዎት ከባዶ ሜዳ ተነስቼ ሳይሆን በቂ መንደርደሪያዎች ላይ በመንተራስ ነው። እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ከሆነ ሴት ልጅ የወር አበባ ከፈሰሳት እርኩስ ስለሆነች ትገለል ይለናል። አለበለዚያ እርሷን የነካ ሁሉ እንደ ዘመን አመጣሹ ኮረና በሽታ እርኩስነትዋ ስለሚተላለፍበት መፍትሄው መገለል ነው ይለናል፦


ዘሌዋውያን 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።
²⁰ መርገምም ስትሆን የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው፤ የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።
²¹ መኝታዋንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።
²² የምትቀመጥበትንም ነገር ሁሉ የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።
²³ በመኝታዋም ላይ ወይም በምትቀመጥበት ነገር ላይ ቢሆን ሲነካው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።
²⁴ ማንም ከእርስዋ ጋር ቢተኛ መርገምዋም ቢነካው፥ ሰባት ቀን ርኩስ ነው፤ የሚተኛበትም መኝታ ሁሉ ርኩስ ነው።
²⁵ ሴትም ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ ከመርገምዋ ወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ ርኩስ ናት።
²⁶ ደምዋም በሚፈስስበት ወራት ሁሉ የምትተኛበት መኝታ ሁሉ በመርገምዋ ጊዜ እንደ ነበረው መኝታ ያለ ይሆንባታል፤ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ እንደ መርገምዋ ርኵስነት ርኵስ ነው።
²⁷ እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ነው፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

ሴት ልጅ ለአባቷ የተሰወረ ቁርጥማት ናት እሷንም ማሰብ እንቅልፍ ያሳጣዋል››(መጽሐፈ ሲራክ 42፡9)


ወዳጄ ከላይ እንደተመለከቱት የጉድ አገር ገንፎ ያቃጥላል እንዲሉ! አጃዒብ ያስብላል አይደል!? ህህህም! እንግዲህ ነገር ቢበዛ ይሆናል የዋዛ ይባላልና! ሁሉንም ማስረጃዎቼን እለጥፋለው ብል ለአንባቢ ድካምና የቀን ስራ ስለሆነ ጥቂት ማስረጃዎችን ከአዲስ ኪዳን ላክልልዎትና ወደሌሎቹ ነጥቦች የምናልፍ ይሆናል። የ1ኛ ጢሞቲዎስ ፀሐፊ ሴቶችን በግልፅ ሴቶች በነገር እየተገዙ በዝግታ ይማሩ እንጂ ወንድ ላይ ልትሰለጥን(ከወንድ እኩል ልትሆን) አልፈቅድም በማለት ሲያገላቸው እንታዘባለን፦

1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤
¹² ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም።

የሚገርመው ነገር ለምን እንዲህ እንዳለ ምክንያት ሲያቀርብ የፊት መሪ ኋላ ቀሪ! በሚል ብሂል ወንድ ቀድሞ ስለተፈጠረና ሴት ደግሞ የኋላ ኋላ ስለተፈጠረች እንዲሁም ቅጠል በልታ የተታለለች ሴት እንጂ ወንድ እንዳልሆነ በመግለፅ ሴቶችን ምንም አታመጡም አርፋቹ የበታች ሆናቹ ተቀመጡ ሲል እስከ አፋንጫቸው ድረስ ሲነካቸው እንታዘባለን፦

1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች።
¹⁴ የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤


1 ቆሮ 14፥35 ለሴት በማኅበር መካከል መናገር ነውር ነውና፥ ምንም ሊማሩ ቢወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ።

1 ጴጥሮስ 3፥7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ 

ቀለሜንጦስ 2÷14 ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን ዓሜን ብላ ትቀበላለችና።

«ከልብስ ብልይገኛል ኃጢአትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል፡፡»(መጽሐፈ ሲራክ 25፡24)

 
ከዚህ በላይ የሴቶችን መብት መናድና ሴቶችን ማግለል ከወዴት ይመጣል ወዳጄ? ወዳጄ እርስዎ በእነዚህ ሴቶች ቦታ ቢሆኑና እርኩስ፣ ደካማ ፍጥረት፣ በዝግታ ይማሩ፣ መናገር አልተፈቀደም ቢባሉ ምን ይሰማወታል? ሴቶች ማለት በቀላሉ እንደ እንቁላል ሊሰበሩና ሊጎዱብን ስለሚችሉ ልንንከባከባቸው ይገባል'ኮ አይደል!? ለዚያም ነው ነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" እንዲህ ያሉን፦ ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 17, ሐዲስ 80″
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም በአሏህ እና በመጨረሻ ቀን የሚያምን በምንም ነገር ሲመሰክር መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል! ሴትን በደግነት ተንከባከቡ! ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነውና"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَإِذَا شَهِدَ أَمْرًا فَلْيَتَكَلَّمْ بِخَيْرٍ أَوْ لِيَسْكُتْ وَاسْتَوْصُوا بِالنِّسَاءِ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ خُلِقَتْ مِنْ ضِلَعٍ

እስቲ ወደ ሌሎች ነጥቦች እንለፍና ሌላ ትዝብት እንመልከት።
1.1K viewsedited  20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 13:42:16 ይድረስልኝ ለኡስታዜ ወሒድ ዑመር!


Kedir Mohammad


https://t.me/ewnet_lehulum
675 views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 11:38:31 ተሰቀለ ¡

ክርስቲያን: የኢየሱስ ፈቃድ ለኛ ሀጢያት ተቸንክሮ ወዶ እና ፈቅዶ መስዋዕትነት መሆን ነው

መጽሐፍ : መሞት ፈቃዱ አልነበረም ከሞት ያድነው ዘንዳ ይለምን ይማጸን ነበር

“አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው።”
— ማቴዎስ 21፥22

“አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።”
— ማርቆስ 14፥36

ሉቃስ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው።
⁴⁴ በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ።

መዝሙር 34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።

መዝሙር 142
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ለመንሁ።


⁵ አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ አንተ ተስፋዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
⁶ እጅግ ተቸግሬአለሁና ወደ ልመናዬ አድምጥ፤ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።

መጽሐፍ: እርሱ መሲሁን ያድነው ዘንዳ ቃል ገብቷል

“በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።”
— መዝሙር 50፥15

መዝሙር 91 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ “ወዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን አውቆአልና እከልለዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል፤ እመልስለታለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁ።
¹⁶ ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”

“እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ፤ የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።”
— መዝሙር 20፥6 (አዲሱ መ.ት)

“በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።”
— መዝሙር 138፥7

“እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ፦ እንግዲህ፦ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ ተብሎ የተጻፈው ይህ ምንድር ነው?”
— ሉቃስ 20፥17

መዝሙር 118
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ ሰማኝ አሰፋልኝም።
⁶ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?
⁷ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ።

¹⁷ አልሞትም በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለሁ።
¹⁸ መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ፤ ለሞት ግን አልሰጠኝም።

²² ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤

“አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።”
— መዝሙር 118፥28

ማቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦

መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።

መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።


¹¹ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
¹² እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

¹³ በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

“ይህ የሆነ፦ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።”
— ዮሐንስ 19፥36

መዝሙር 34
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
¹⁸ እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።
¹⁹ የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል።
²⁰ እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።

²¹ ኃጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይጸጸታሉ።
²² የባሪያዎቹን ነፍስ እግዚአብሔር ይቤዣል፥ በእርሱም የሚያምኑ ሁሉ አይጸጸቱም።

“እርሱም፦ እላችኋለሁ፥ ከወዴት እንደ ሆናችሁ አላውቃችሁም፤ ሁላችሁ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ይላችኋል።”
— ሉቃስ 13፥27

መዝሙር 141
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥ ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ።
¹⁰ እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኃጢአተኞች በወጥመዳቸው ይውደቁ።

ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
²³ የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

መዝሙር 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
⁹ እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ።
¹⁰ ጠላቶቼ ሁሉ ይፈሩ እጅግም ይጐስቍሉ፤ ወደ ኋላቸው ይመለሱ፥ በፍጥነትም ይፈሩ።

“ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋር አቀረበ፤ ፍጹም ትሑት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት።”
— ዕብራውያን 5፥7 (አዲሱ መ.ት)

“መሥዋዕትንና ቊርባንን አልፈለግህም፤ ጆሮቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትን፣ የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም።”
— መዝሙር 40፥6 (አዲሱ መ.ት)

መዝሙር 51 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ መሥዋዕትን ብትወድ ኖሮ ባቀረብሁልህ ነበር፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ደስ አያሰኝህም።

“ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር፣ በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።”
— 1ኛ ሳሙኤል 15፥22 (አዲሱ መ.ት)

“ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።”
— ምሳሌ 21፥3 (አዲሱ መ.ት)

መዝሙር 86
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ አቤቱ፥ አንተ መሓሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ምሕረትህም ለሚጠሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።
⁶ አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ የልመናዬንም ድምፅ ስማ።
⁷ ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ።

መጽሐፈ ሲራክ 2:10-11
በዘመን የቀደሙ ሰዎችን አስተውሉ በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ማነው? እወቁ እሱን በመፍራት መከራውን የታገሠ በመከራ እንደ ጣለው የቀረ ማነው? ለምኖትስ ቸል ያለው ማናው?

የጻድቁን ኢየሱስን ጸሎት ጆሮ ዳባ ብሎት እንዲሰቀል ለጠላቱ አሳልፎ ሰጠው ? ወይስ ከጭንቁ አዳነው !

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏህ ወበረካቱህ

በወንድም ሀቢብ

@ewnet_lehulum
781 viewsedited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:00:06 وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

@ewnet_lehulum
797 viewsedited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ