Get Mystery Box with random crypto!

ወግ ብቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ wegoch — ወግ ብቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ wegoch — ወግ ብቻ
የሰርጥ አድራሻ: @wegoch
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.51K
የሰርጥ መግለጫ

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።
✔ @getem @serenity13
✔ @wegoch @Words19
✔ @seiloch
✔ @zefenbicha
Creator @leul_mekonnen1

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 25

2022-04-16 21:52:36 እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 9)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

"ቆይ ራስሽ አልነበርሽ እንዴ የነገርሽኝ?"ስትለኝ እያወራን ያለነው በአንድ ዓይነት ቋንቋ አለመሆኑ ተገለጠልኝ ።

"ምኑን ነው ደግሞ እኔ የነገርኩሽ እምዬ?"

"ለዳንኤል የፍቅር ስሜት ምላሽ ሳይሰጡ መቀመጡ የህክምናው አንድ አካል ነው አላልሽኝም ራስሽ?"

"እእእእ....እ...እሱን ነው እንዴ 'ምትይው?አዎ ነግሬሻለሁ ልክ ነሽ ኧረ እኔ ነኝ ደነዟ"አልኩ ምንተ ሀፍረቴን እየተቅለሰለስኩ።ለዳንኤል ስሜት እንዳለኝ እንዴት አወቀችብኝ ብዬ ስጨነቅ እሷ ለካ ያሰበችው ሌላ ነበር! 'አይ እምዬ! ቀልቤን ገፈፍሽው የስራሽን ይስጥሽ' ስል በልቤ

"ለሱ ስሜት እንዳለሽምአውቃለሁ!"ብላ እጥፉን ቀልቤን ገፈፈችው።ብርግግ ብዬ ተነሳሁና

"ምን አልሽ?ም...ምንድነው ያልሽው?"አልኳት ወገቤን ይዤ።ተውረገረግሁባት ቢባል ይቀላል።አላፍርምኮ ልክድ ነው?

"ምነው ዋሸሁ?" ስትናገር ከልክ በላይ ዘና ብላ ነው። ወዲያው ቀጠል አረገችና

"እናትሽ'ኮ ነኝ!እ?ይህን ዕውነት የመካድ ሀሳቡ አለሽ?" ስትለኝ

"ሁሁሁሁሁፍፍፍፍፍፍፍፍ!የለኝም" በረጅሙ ተንፍሼ አልጋው ላይ ከቁሜ ወደቅሁበት።አፍታም ሳልቆይ ፈትለክ ብዬ ተነሳሁና

"እና እያወቅሽ ነው ይህን ሁሉ 'ምታደርጊው?" በድጋሚ ጮህኩ።

"አዎ" አሁንም ዘና ብላለች።እኔ ግን ባሰብኝ

"እውነት ነበር ለካ!"አልኩኝ።

"ምኑ?"

"አባዬ እናትሽ አንዳንዴ ክፉ ናት ያለኝ...እንዴት ለማላፈቅረው ሰው ልዳር መሆኑ ሰላም ሰጠሽ?"ስል ፊቷ ተለዋወጠ።አትኩራ ለሴኮንዶች አየችኝና ለዘብ ባለ አንደበት እንዲህ አለችኝ...

"እየውልሽ ሚጥሻዬ...አባትሽ ክፋትና ለራስ ማወቅ የሚባሉት ሁለት ሀሳቦች ይምታቱበት ነበር።ለሞት ያበቃው ከልክ ያለፈ ርህራሄውና ሰው አማኝነቱ እንደሆነ ታውቂያለሽ።ስለራስህ አስብ...ላንተ ሳትሆን ለሰዎች መሆን አትችልም ማለቴ ክፉ ያስብለኝ ነበር።የዋህነቱን ስለሚያውቁ ሞልቶ የተረፋቸው ሳይቀሩ ችግረኛ መስለው አበድረን ይሉታል።አበድሮ አይረካም ነበር...የሁዋላ የሁዋላ እሱ ራሱ ነፍሱን አስይዞ በማይሆን ብድር ውሀ ሆኖ ቀረ እንጂ..."እንባዋን ታግላ ማስቀረት ተሳናት።

"...ሰማሽ ሚጡ ለራስሽ እወቂበት!ያንቺን አጥር በጅምር ትተሽ የጎረቤት አጥር ስታጥሪ ጎረቤትሽ ጀሌውን ልኮ በጀርባ ያዘርፍሻል።በሁዋላ አብሮሽ የጠፋሽን ንብረት ሊያፋልግሽ ይመጣል።ከዘረፈሽ ገንዘብ የሩቡን ሩብ 'ለአንዳንድ ነገር ትሁንሽ' ብሎ ሸጎጥ ያደርግልሻል።ብታምኚም ባታምኚም የምትኖሪበት ዐለም Reality ይህ ነው"

አሁን ደግሞ እንባዋ ቆሞ ወደሆነ ወደማላውቃት አይነት አስፈሪ ሴት ተቀየረችብኝ።የምትነግረኝ ነገር ከኔ ህይወት ጋር ምን እንደሚያገናኘው ባላውቅም ልክ መሆኗን አልክድም።ለህይወትሽ የሚበጅሽ ስዩምን ማግባቱ ነው ለማለት ነው ይሄ ሁሉ? ራሷን አረጋግታ ስትቀመጥ ጨከን ባለ አንደበት እንዲህ አለችኝ።

"ዕውነታውን ተጋፈጭው ጊዜ!"

"የምኑን ዕውነታ?"

"የዳንኤልን ሞት መቀበል ከብዶሻል አውቃለሁ።"

"ማን ያውቃል እኔ ቀድሜው እንደማልሞት?እ?"

"እየውልሽ ሚጥሻዬ..."ልትቀጥል ስትል የክፍሉ በር ተንኳኳ።

"ይግቡ"አልኩ በደመነፍስ።ዳንኤል ነበር።እናቴ ሲያለቅሱ የቆዩ ዐይኖቿን እየጠራረገች

"ልጅ ዳንኤል!ና ግባ እስኪ"አለችው።ገብቶ ከጎናችን ተቀመጠ።ዝምታ በመሀከላችን ነገሰ።እናቴ

"እ...እናንተ መነጋገር ሳይኖርባችሁ አይቀርም እኔ ልሂድ!"ብላ ስትነሳ እጇን ይዤ በተማፅኖ አስተያየት

"እማ አትሂጂ አብረሽኝ ሁኚ!"አልኳት።ከዳንኤል ጋር ለብቻችን አንድ ክፍል ውስጥ የመቀመጡን ሀሳብ አልወደድኩትም።እምዬ እንዴት እንዳሰበችው አላውቅም።

"ስጋትሽ ገብቶኛል ግን ሁለታችሁም ላይ ዕምነት አለኝ።በነፃነት አውሩ"ብላ ጥላን ወጣች።እኔኮ ግን እሷ የምታምነኝን ያህል ራሴን አላምነውም።ከመውጣቷ

"አታስቢ ዶክተር! ከበሽታዬም በላይ ስብዕናሽ ወሰኔን እንዳላልፍ ያስገድደኛል"አለኝ።ምን ዐይነት ጦር የሆነ ንግግር ነው?

"እ...እኔ እንደዛ አላልኩም...ለማለት የፈለኩት..."ጠቋሚ ጣቱን ከንፈሬ ላይ አድርጎ በምልክት ዝም እንድል ነገረኝ።ዝም አልኩ።ትኩርርርርርር አርጎ ሊያየኝ ነው ብዬ ስፈራ ጣቱን አነሳና በዝግታ ሳቀብኝ።

"አሃሃሃ...ሃሃሃሃሃ...ሃሃሃ"

"ምን ያስቅሀል?"

"ትፈሪኛለሽ አ?ምኔ ነው ሚያስፈራሽ ቆይ?"

"ኧ...ኧረ እኔ አልፈራህም!ለምን እፈራሀለሁ?"ነጭ ውሸት ዋሸሁ።ሲጠጋኝ እፈራለሁ...የሆነ የማላውቀው ንዝረት መላ ሰውነቴን ይሰማኛል...በአካል ስንራራቅ ደግሞ ንዝረቱ ወደጭንቅላቴ ይወጣል...የምናብ ንዝረት...ከሀሳብ ተነስቶ ሰውነትን የሚያናውጥ ንዝረት።ይሄንን ይመስለኛል "ኤክስፐርቶቹ" የስሜት ፍቅር የሚሉት።የስሜት ፍቅር ሲራራቁ የሚደበዝዝ አካላዊ ቅርርብ ላይ ብቻ የተመሰረተ "ፍቅር-ቅብ" እንጂ ፍቅር አይደለም ሲባል ሰምቻለሁ። ምናውቄ?ኧረ በሆነልኝና ዳንኤል በጊዜ ሂደት የምረሳው የሆነ ጊዜ ላይ በህይወቴ የተከሰተ ጥሩ ነገር ሆኖ ባለፈልኝ!

"እህህህህም!ካልሽ እሺ...ግን ከአንደኛ ሚዜ'ኮ ምንም አይደበቅም...ንገሪኝ?"

"ያምሀል ግን?ንክ ነገር ነህ አይደል? "አልኩ ሌባ ጣቴን ጭንቅላቴ አካባቢ ከጆሮዬ ከፍ አድርጌ ቡለን እንደማላላት እያጠማዘዝኩ።

"እንግዲህ ሐኪሟም አንቺ ነሽ እኔ ምናውቄ!"

"ቀልዱ እዚህ ጋ ቢያበቃና ወደቁምነገሩ ብንገባስ?"አልኩ በመሰላቸት።

"በዛች ቀን ከጎንሽ መሆን እፈልጋለሁ!በሰርግሽ ቀን!ደስታሽን ባልካፈል ይፀፅተኛል" ከምሩ ነው?

"ኧረ ተው የኛ ክርስቶስ!ፍቅርህስ የት ገባ?የመኖሬ ምክንያት ነሽ የተባልኩትስ?ወይስ ስሜቱ ሰርጌ ላይ አንደኛ ሚዜ እስከመሆን አጀግኖሀል??ፍቅርህ የት ሄደ?"እየጮህኩ አፈጠጥኩበት።የሚደነግጥ ዐይነት አይደለም።

"እሱንማ ሸጥኩት"

"ዳንኤል ክፉ ነገር እንዳደርግ አታስገድደኝ እባክህን!"የደም ስሬ ሲግተረተር ይሰማኛል።

"ምን?ልትገይኝ ነው?ትንሽ ነውኮ የቀረኝ ታገሺ ሰበብ እንዳልሆንብሽ"

"እስኪ እየኝ"አልኩ ዐይኑ ላይ አፍጥጬ።ጉንጭና ጉንጩን በሁለት እጆቼ ይዤ አፈጠጥኩበት።

"ንገረኝ"

"ምን ልንገርሽ?"

"ውሸት ነው በለኝ"

"ምኑ?"

"አ...አሁን የሚሰ...ሰማኝ"...እንባዬን ማን መቶ ተው ይበልልኝ!

"ምንድነው የሚሰማሽ?" ትኩርርርርር ብሎ አየኝ።

"ታውቀዋለህ...ሳ...ሳ..ልነግርህ ታውቀዋለህ" እንባዬን በአይበሉባው ጠረገና

"እባክሽን ተይ ጊዜ!"አለኝ እጆቼን ከጉንጮቹ እያስለቀቀ

"ምኑን ልተወው?"

"የሚሰማሽን"

"አንተ ትተኸዋል?"በድጋሚ እንባዬ ወረደ።

"በፍፁም ልተወው አልችልም"

"እንጥፋ"አልኩ ሳላስበው።

"ከዛስ?"ፈገግ አለ።

"ከዛማ በቃ አብረን እንኖራለን!"

"አንቺ ሴት ጅል ስትሆኚም ያምርብሻል ልበል!?"

"መብትህ ነው በል!በነካ አፍህ እንጥፋ ላልኩህም እሺ በል"

ይቀጥላል

ደራሲት:- ማዕዶት ያየህ

@wegoch
@wegoch
@paappii
4.4K viewsDAVE / PAPI, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 22:34:33 እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 8)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።


ቆይ ግን እግዜር አይስትም አይደል? እኔን የፈጠረኝ በ system ችግር አይደለም አይደል?ለምንድነው ደስታ እኔጋ ሲደርስ ራሱን የሚያጠፋው ብዬ ማበድ ቀረኝ።ምን አይነት ከንቱ ነሽ ጊዜ?ይቺም ፈተና ሆና ስታለቃቅሺ ቢያይሽ እዮብ እንዴት ይሆን የሚታዘብሽ?

ስር ሚዜው መጣ ተባለ።የሁሉም ዐይን እሱን ለማየት አሰፈሰፈ ።የኔ ዐይኖች ግን ለምንም ስላልጓጉ ይቅርታ ጠይቄና በራስ ምታቴ አሳብቤ ክፍሌ ገብቼ ልቀረቀር ስል አንድ ድምፅ መለሰኝ።

"ሙሽሪት ወዴት ነው?እንግዳ አትቀበይም እንዴ?"የሚል የመልዐኩ የዳንኤል ድምፅ!ዞር ያልኩበት ፍጥነት ቢለካ ከብርሀን ፍጥነት ሳይወዳደር ይቀራል?ዐይኔ የሚያየውን ለማመን አዳገተው።አፌን ከፍቼ ቀረሁ።ዳንኤል ሙሉ ሱፉን ግጥም አድርጎ ለብሶ ከስዩም ጎን ቆሟል።ሁለቱም በፈገግታ ተሞልተው ያዩኛል ።የኔ ድንጋጤ ግን ልክ አጧል።ጴጥሮስ ራሱ መቼም አልከዳህም ያለውን ጌታ በአንድ ሌሊት ሶሰት ጊዜ አላውቀውም ብሎ ሲሸመጥጥ እንዲህ የደነገጠ አይመስለኝም።ምንድነው እነዚህ ሰዎች ከጀርባዬ የጠነሰሱት?እናቴን ባይኔ ፈለኳት...አየሁዋት...ደንግጣለች።ዐይኗን አይቼ ስለጉዳዩ የምታውቀው አንዳች እንደሌለ ተረዳሁ።

"እንግዲህ ሲጠበቅ የነበረው ስር ሚዜዬ ይኸው!"ሲል ስዩም ቤት ውስጥ ያለው ሁሉ ሞቅ አርጎ አጨበጨበ።ጭንቅላቴ ላይ አንዳች የበረዶ ግግር የወደቀብኝ ይመስል ከቁሜ ወድቄ ሶፋው ላይ ዘጭ አልኩበት።የዚህን ሶፋ ውለታ መቼም ከፍዬ አልጨርሰው!በዚህ ግርግር ውስጥ እጅጉን የተጠቀምኩት በዙሪያዬ ካሉት ሰዎች በላይ እሱ ከአጠገቤ በመሆኑ ነው። መሬት ላይ ብዘረርስ ኖሮ?እንደዛ ከቁሜ ወድቄም የኔን ጥያቄአዊ አስተያየትና ድንጋጤ ምክንያት ከእናቴና ከዳንኤል ውጭ ያወቀ አልነበረም መሰለኝ እንግዳ የሆነ አስተያየትና ጥያቄ አልገጠመኝም።ወይም እኔ አላስተዋልኩም መሰለኝ።የሁሉም ትኩረት ሚዜው ላይ ነበር።ሴቶቹ በውበቱና በግርማሞገሱ እየተደነቁ እርስበርሳቸው ይንሾካሾካሉ።ቀሪዎቹ የወንድ ሚዜዎች በቁመናው ስላስከነዳቸው ነው መሰለኝ በግርምት ተውጠው ያዩታል።

"እንኳን ደስ አለሽ ዶክተር!"አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ።ከምኔው የተቀመጥኩበት እንደደረሰ አላውቅም።ክው አልኩ።የሰላምታውን አፀፋ ረስቼ ዐይኖቹ ላይ አፈጠጥኩ።ያ አስማታም ዐይኑ ትኩርርርር አርጎ እያየኝ ነው።ያ የሚያርበተብተው አስተያየት...

መታመሙን አሁን ገና ከልቤ አመንኩ።ምን አይነት ድንበር ዘለል ፍቅር ነው ለሚያፈቅሩት ሰው የሰርግ ሽርጉድ ላይ እስከመገኘት የሚያደርሰው?እንዴት እንዳስበው ፈልጎ ነው?ይሄ ምናይነት የዞረ ድምር ነው?እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህንን ማድረግ ቀርቶ አስበዋለሁ?ኧረ ማንም ይህንን አያስብም!ማንም!

"አ...አ...መሰግናለሁ ግ...ግን ምንድነው እየሆነ ያለው አልገባኝም"አልኩት።ሲያየኝ የሚሰማኝ መርበድበድ አሁን በድንጋጤና ግራ በመጋባት ተተክቷል።እሱም ገብቶታል።ያው ዳንኤል አይደል?ፊት ቀርቶ ልብ ማንበብን የተካነ አይደል?

"በሁዋላ አስረዳሻለሁ...አሁን ጊዜው የመደሰት እንጂ የጥያቄ አይደለም።ተደሰቺ ሙሽሪት"አለና በጂፓሱ ከሚደመጠው የሰርግ ዘፈን ጋር አብሮ እያንጎራጎረ ከፊት ለፊቴ ካለው የሶፋ ወንበር ላይ ተቀመጠ።

"አይዞሽ ሙሽሪት ...
አይበልሽ ከፋ አይበልሽ ከፋ...
ሁሉም ያገባል በየወረፋ በየወረፋ..."

ሲል ለኔ የሚሰማኝ

"አይዞሽ ሙሽሪት
አይበልሽ ከፋ አይበልሽ ከፋ
ሁሉም ይሞታል በየወረፋ በየወረፋ..." እንደሚል ሆኖ ነው።

ተደሰቺ ማለት ምን ማለት ነው?ይህ ቃል እኔ የማላውቀው ሌላ ዳንኤልኛ ትርጉም አለው እንዴ?ፍቅር እንደዚህ ነው እንዴ በሞቴ?እንደዚህ አስተሳሰብ አዛብቶ ለእብድ አምስት ጉዳይ ያደርጋል በክርስቶስ?ሲገባኝ ለኔ ፍቅር እግዚአብሔር ነው።ፍቅር ክርስቶስ ነው።ራስን ገድሎ ሌላን ማዳን እንጂ ሰውን በቁም መግደል ከመቼ ወዲህ ፍቅር ሆነ?ከመቼስ ጀምሮ መሲሁን ወከለ?

የምር ይህ ሰው እንደሚለው ይወደኛል?እንጃ!ከወደደኝ ለምን ያሳዝነኛል?ለምን ያቆስለኛል?ይህ እንደሚያም ጠፍቶት ነው?ለሱ የሚሰማኝ የሆነ ውሉን የማላውቀው ሞገደኛ ስሜት እንዳለ ቃል በቃል ሳልናገር መረዳት አቆቶት ነው አጨብጭቦ ሊድረኝ የተሰናዳው?ዕድሜ ዘለዐለሜን ሰው ስመርቅ "ከዳንኤል ዓይነት ሰው ፈጣሪ ይሰውራችሁ!"እንድል ይፈልጋል ልበል?

እናቴ በዐይኗ ምልክት ሰጥታኝ ወደክፍሏ ሄደች።ተከትያት ገባሁ።በጥያቄ ልታጣድፈኝ ተዘጋጅታ ጠበቀችኝ። ከመግባቴ ለሴኮንዶች እንኳን ሳትታገስ

"ሚጡ ምንድነው ነገሩ? ልታብራሪልኝ ትችያለሽ?"

"አልችልም ምክንያቱም ምንም አላውቅም"

"እንዴት አታውቂም? "

"እንደዚህ ነዋ እማዬ ልክ እንደዚህ?"እምባዬ አመለጠኝ።ሳግ ፋታ ነሳኝ።ያልጠበቀችውን ስሆንባት ደነገጠችና

"ቀስ በይ ሚጥሻ ሰው ይሰማሻል!"አለች ድምፁዋን ዝቅ አድርጋ ጠቋሚ ጣቷን ከንፈሯ ላይ አድርጋ!እንደጮህኩ አልታወቀኝም ነበር።

"Who cares!ምናገባኝ ይስሙአ!እማ የነሱ ወሬ ከኔ ስብራት ይበልጣል?ማንም....ማ...ንም ምንም ቢል አሁን ከ...ከደማው በላይ ልቤ መቼም አይደማም ገባሽ?"የባሰ ጮህኩ።

"እሺ በቃ እሺ!ልክ ነሽ አንቺ...እኔኮ የማይሆን ነገር አውርተው የባሰ እንዳታዝኚብኝ ብዬ ነው።እንጂማ ተራ ሀሜት እኔ እናትሽ ግድ እንደማይሰጠኝ ታውቂያለሽ...ነይ እስኪ ጋደም በይና እናውራው"እቅፏን እየጠቆመች እተኛበት ዘንድ ጋበዘችኝ።እቅፏ ፈውሴ ነው።እጇ የሆነ ዓይነት የመድሀኒትነት ይዘት አለው።ስትነካኝ ሰላሜ ሲበዛ ይታወቀኛል ።


እቅፏ ላይ ተጋድሜ መነፍረቅ ጀመርኩ።ከከፋኝ ሳላለቅስ እንደማይወጣልኝ ስለምታውቅ ዝም በይ አላለችኝም።እላዩአ ላይ ጣል ያረገቻትን ፎጣ በጥርሴ ነክሼ ምርርርር ብዬ አለቀስኩ።መነፍረቁ ሲበቃኝ ቀና ብዬ

"እምዬ ተጫወተብኝ ይሄ የተረገመ!"አልኳት።

"ማነው እሱ?"

"ዳንኤል!"አልኩ ጥርሴን በእልህ ነክሼ።

"ምን ብሎ ነው የተጫወተብሽ?"

"እወድሻለሁ ብሎ ዋሸኝ!ሰ...ሰ ...ሰራልኝ!እምዬ ይቅር በይኝ ዋሽቼሻለሁ"እምባዬን ላስቆመው ተሳነኝ።

"ምንድነው የዋሸሺኝ እስኪ ተረጋጊ ሳታለቅሺ ንገሪኝ"አለች እንባዬን እያበሰች።

"ሰ...ሰርጉ ይራዘም ያልኩሽ እ...እውነትም የመዘጋጃ ጊዜ አጥቼ አልነበረም።ምክንያቴ ሌላ ነበር"

"ምክንያትሽ ዳንኤል ነበር አውቃለሁ"ስትለኝ እምባዬ ደረቀ።ወሰን በ
የሌለው ድንጋጤ መዳፉ ውስጥ ከቶ ሲያሸኝ ተሰማኝ።

"ም...ምን?ምንድነው የምታውቂው እማ?ደ...ደግሞስ ሳልነግርሽ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?ማወቅሽንስ ለምን አልነገርሽኝም? ይህንን ሁሉ ጊዜ ለብቻዬ ሁሉንም ስጋፈጥ ዝም ያልሽው ልጄ ምን ያህል ጠንካራ ናት ብለሽ experiment እየሰራሽብኝ ነበር?"በጥያቄ ላይ ሌላ ማለቂያ የሌለው ጥያቄን እየደረብኩ አዋከብኳት።


ይቀጥላል

#ማዕዶት #ያየህ

16/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
4.7K viewsDAVE / PAPI, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 21:52:24 እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ(ክፍል 7)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሰው በደስታ ብዛት የሚያደርገው ጠፍቶት እናንተ እዚያ ደስታ ላይ ሳትፈልጉ የክህደትን ቀዝቃዛ ውሀ እንደምትቸልሱበት ማሰብ ይከብዳል አይደል?በረሀብ ሰውነቱ ከመነመነ ህፃን ላይ ወተት እንደመንጠቅ፣ጉልበታቸው የሚንቀጠቀጥን አዛውንት ገፍትሮ ቦታቸው ላይ ሄዶ እንደመቀመጥ፣ የነፍሰጡርን ጭንቅ እንደማየት ያህል ይጨንቃል።

ስለስዩም ተጨነቅሁ...ስለእናቴ ተጨነቅሁ...ስለዳንኤል ተጨነቅሁ...15 ቀናት ለቀሩት ሰርጌ የኔ ስሜት ከበረዶም የቀዘቀዘ ነበር።ቤተ ዘመዱ እረፍት አጥቶ ይዋከባል...ሙሽራው በሀሴት ይገባበት ጠፍቶታል።ሚዜዎቹ ሽርጉዳቸው ለጉድ ነው።የኔ በሀሳብ መሰነግ "ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ"በሚባል የአባባል ካባ ተድበስብሶ ጠያቂ አጣ።እናቴ በበኩሏ ጭንቀቴ ቢገባትም ምንም ማድረግ እንደማይቻል አምና የሰርጉን ዝግጅት እያሽሞነሞነችው ነው።

በሰርጉ ዝግጅት ምክንያት ስራ ከገባሁ ዛሬ 10 ኛ ቀኔ በመሆኑ ዳንኤልን ለ 10 ተከታታይ ቀናት አላየሁትም።ስጨነቅ ደሲለዋል መሰለኝ ስልኬን አይመልስም።የጽሁፍ መልዕክቶቼም ምላሽ አያገኙም።እንዳብድ ነው እንዴ የሚፈልገው?

መከረኛው ሰርግ ቀናት ሲቀሩት የሚዜና የጓደኛ ትውውቅ በሚል ሰበብ ሰው እንዲሰባሰብ ተወሰነ።ያው እንደምስል መቀመጥ እንጂ እንደሙሽራ የውበቴ፣የአለባበሴ...የሰርጉ ጭፈራ የመሳሰሉት ነገሮች ላይ በሰፊውና በትኩረት ማውራቱ ባይሳካልኝም እዚህ ላይ ዋናዋ ተዋናይት እኔ እንደመሆኔ መሳተፌ የግድ ነበር።

"ሙሽሪት ኧረ ፊትሽን ፍቺው!ያለላርጎ ዘፈዘፍሽው'ኮ ሃ...ሃ...ሃ...መዳር እንደዚህ የሚያስደብር ከሆነማ I will stay single forever....ሃ....ሃ....ሃ..."ትላለች ከሚዜዎቼ አንዷ የሆነችው ሶልያና።

"ባክሽ ተያት የወጉ ነው...ስንት የሚያሳስባት ነገር ይኖራል ጎጆ ወጪ ነች'ኮ አንቺ ደግሞ" ትቀጥላለች ሌላኛዋ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተጠራው ሰው ቀስ በቀስ ቤቱን መሙላት ጀመረ።ሁሉም መጥተው አንድ ሰው ብቻ ጎደለ።የወንዱ ሙሽራ ስር ሚዜ...

ሁሉም እርስበራሱ ማን ይሆን እያለ በሹክሹክታ ይነጋገራል ።ስዩም አብሮአደግ ጓደኛውን የመጀመሪያ ሚዜው እንደሚያደርገው ነግሮኛል ።

"ሙሽር ስር ሚዜህ ዘገየሳ ምነው?"የተሰበሰበው ሁሉ በየተራ ስዩምን ይጠይቁታል ።

"ይመጣል ይመጣል!አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው ያረፈድኩት ብሎኛል እየመጣ ነው ተጫወቱ"ይላል ፈገግ እያለ።በመሀል ሰረቅ እያረገ ሲያየኝ የተዘፈዘፈ ፊቴ ስቅቅ ያረገኝና ድንጋጤና ሀፍረት የተነባበረበት ፈገግታዬን እለግሰዋለሁ።መጨነቄ ገብቶታል።ግን አልጠየቀኝም።ቢጠይቀኝስ ምን እላለሁ?

'ላንተ የነበረኝን ፍቅር ዳንኤል የሚባል መልዐክ በክንፉ ሰብስቦ ወሰደብኝ' ልለው ነው?ወይስ ደግሞ

'ስዩም ከዚህ ጋብቻ የምታተርፈው ፀፀትን ብቻ ነው ....ልቅርብህ ...ልቤ ውስጥ የነበረህ ቦታ አሁን በሌላ ተይዟል...በሀሳቤ ከወሰለትኩብህ ቆየሁ....ከማገጥኩብህ ሰነባበትኩ...ሰርጉ እንዲራዘም የፈለኩት ለዚህ ውስልትናዬ ዕድሜ ለመጨመር እንጂ የሰርጉ ሽርጉድ ፋታ ነስቶኝ አልነበረም።የምትመጣው ልታስረኝ እንጂ ልታገባኝ አልመስልሽ አለኝ...ጣቴን እንጂ ሌላ የተመኘ ልቤን በወርቅ ቀለበትህ አታስረውም....
ላረኩብህ ነገር ምንም ብትቀጣኝ ሲያንሰኝ ነው...ለማደርስብህ የሞራል ስብራት ጌታ መጥቶ 'ከመሀላችሁ ሀጥያት የለብኝም የሚል ይውገራት' ቢል እንኳን ምድር ላይ ያለው ሰው ሁሉ ከኔ ክህደት አንፃር ፃድቅ ነውና ማንም ይወግረኝ ዘንድ ፈቃዴ ነው' ብለው ኩነኔዬ ይፋቅልኝ ይሆን?እንጃ!

ዘመናይ ማርዬ...
ዘመናይ ማርዬ...
ስም አወጣሁልሽ...
ሁለት ልብ ብዬ...
ወላዋይት ብዬ...

የኛ ሙሽራ ዶክተሪቱ...
ማን ያውጣሽ ከመዓቱ...

የሚል ይመስለኛል ለሰርጉ የተከፈተው ዘፈን!

ይቀጥላል!

በማዕዶት ያየህ

15/04/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
4.5K viewsDAVE / PAPI, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 17:36:34 .....
ለእኔም እኮ አይገባኝም፤ ቆይ በሕይወታችን የምንፈልገው ትልቁ ነገር ፍቅር ነው አይደል? ያውም ጥልቅና ነጋሪ የማያስፈልገው እንዲው በአይን ብቻ የሚገባን? ይህንን የሁሉን መሻት እኮ ነው የኔ ሆኖ ያገኘሁት፤ ታዲያ ለምንድነው ማመሰገኑ የቸገረኝ? ለምን ይሆን ልቤን የጭነት ያህል የሚከብደው? ለምንድነው አሁንም ያልሞላ ክፍተት እንዳለ የሚሰማኝ?

ያኔ....
እሱ ወላጆቹን በሞት አጥቶ በሀዘን የተሰበረበት ጊዜ ነበር፤ በዛ ሁሉ ስቃይ ውስጥ ሆኖ የኔን አብሮነት ሲሻ የራስህ ጉዳይ የምልበት አቅም አልነበረኝም ግን ያውቀዋል አፍቅሬው አልነበረም።
በቆይታ እሱም ሀሳቡን የሚቀይር እኔም ልቤ የፈቀደውን የማደርግ መስሎኝ ነበር። ጊዜያት ባለፉ ቁጥር የሱ ፍቅር ሲጨምር እኔ ለሱ ያለኝ ክብርና የጓደኝነት መውደድ እንዳለ ከመዝለቁ ውጪ ልቤን ለፍቅር ማስረከብ አቃተኝ።

ራሴን እኮ እጠይቀዋለው "ያልወደድሽለትን አንድ ነገር ጥቀሺ" ብባል አፌ ይተሳሰራል እንጂ ይህ ነው የምለው አንዲት ሳንካ እንኳን የለበትም፤ ግን አላፈቀርኩትም።

ምንም ቢጠየቅ በሚገርም ብስለት ነገሮችን ያብራራል፤የእይታው አድማስ፣ የምልከታው ጥግ "ለካ ይህም አለ እንዴ?" እንዳስባለኝ ነው።

ቁጥብ ነው እናም ኮስታራ፣ ስክን ያለ፣ ልክ እንደ ውሀ የሚጋባ አይነት የእርጋታ መንፈስ ያለው፤ የልጅ አዋቂ።
በፊት በፊት ሰዎች የዚህ አይነት የስብዕና ጥልቀት የሚኖራቸው ከህይወት ብዙ ሲቀስሙ ይመስለኝ ነበር፤ እሱ ባለበት የእድሜ ልክ እንዴት ላስበው እችላለው?
በዚህ ለይ ደግሞ አፍቃሪነቱ፣ አይኑ ለይ የማየው መውደድ፣ አይን ያዝ ከሚያደርግ ግርማ ሞገሱ ጋር ልብን የመቆጣጠር ሀይል አለው፤ታዲያ እኔን
ማሸነፍ ለምን ተሳነው?

ብዙ ጊዜ ሁሉን እርግፍ አድርጎ ስለመተው እና ብቻዬን ስለመሆን አስባለው፤ እሱ ያንን እንዳደርግ አይፈቅድልኝም እንጂ።
"ራሴን አጠፋልሽና ትገላገያለሽ" ያለኝን ባሰብኩት ቁጥር ልቤ ይጨነቃል ለነገሩ እንደዛ ባይለኝም እንኳን ያንን ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማይል እርግጠኛ ነኝ፤ ለሱ የመኖሩ ምክንያት ነኛ!
አንዳንዴ "ቆይ መውደድ ያልቻልኩት ሁሌም ቅርቤ ስለሆነ በእጅ የያዙት ሆኖብኝ ነው? ሳጣው እንደ እሳት ሊያንገበግብኝ?" ብዬ አስባለው።
ነገር ግን ተጣልተን በቆየንባቸው ጊዜያት ከፋኝ እንጂ ያንን ፍቅር ግን አልታመምኩትም።

አከብረዋለው፣ ለሱ ያለኝ መውደድ ከልብ ነው፤ አንዲት እንቅፋት እንኳን በህይወቱ እንድታጋጥመው አልፈልግም፤ ሳቁ ነው የሚናፍቀኝ፤ የወደደውና የሚያስፈልገው እንዲሆንለት ነው ምኞቴ፤ ይህን ለመሰለ ስብዕናው መቼስ ቢያንስበት እንጂ አይበዛም።

ፍቅር ግን ተሰርቶ አይመጣም አይደል? "ይህንን ሰው መውደድ አለብኝ!" ማለት ነበረብኝ? ብልስ ይሆንልኛል?፤ ነው ወይስ ልክ እንደ ተሰማኝ ማስመሰል አለብኝ? ማንም ሰው እኮ ከራሱ አያመልጥም።
እንዳልወደድኩት ማሰቡ ለራሱ የጥፋተኝነት ስሜት ይፈጥርብኛል ግን እውነታው እሱ ነው ካልሆነ ከራስ ጋር ድብብቆሽ ይሆናል።
ፍቅር ደግሞ ይሰጠናል እንጂ በስራ አናመጣውም፤ በማንቆጣጠረው ልክ ውስጣችንን ሞልቶት እናገኘዋለው ያኔ ከዛ ሰው ጋር መሆን አማራጭ የሌለው ብቸኛው ውሳኔያችን ነው።

ግን ማናችን ነን የተሳሳትነው?
ያ ጥልቅ ስሜት ሳይሰማኝ ለሱ ስል ባላመንኩበት ህይወት ውስጥ እየዳከርኩ የራሴን ስሜት ለማዳፍን የምሞክረው፣ በገዛ ህይወቴ ለይ የመወሰን ስልጣኔን የተነጠኩት፣ ደስተኛ እንደማልሆን እያወኩኝ በተቀመረልኝ አብሮነት ውስጥ ማለፍ ግድ የሆነብኝ እኔ? ወይስ.....
ያለ ልክ የሚያፈቅራት ሴት እሷ ጋር ያ ስሜት እንደሌለ እያወቀ እንኳን መውደዱ ያልቀነሰበት፣ ከሷ ጋር ለመሆን የሷ መኖር እንጂ መልካምነቷ ግድ የማይሰጠው፣ የነገው ህይወቱ ከሷ መኖር ጋር የተሳሰረበት፤ እውነተኛው አፍቃሪው እሱ?
ማናችን ነን ልክ?.....የቱስ ጋር ነው የተሳሳትነው?
.
.
ለዚህ እኮ ነው... ለኔም አይገባኝም የምለው።

@wegoch
@wegoch
@paappii

By mahlet
4.3K viewsDAVE / PAPI, 14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:47:28 በማዕዶት ያየህ


@wegoch
@wegoch
@tizur_12
5.3K viewsDAVE / PAPI, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 10:47:28 እብድ አይፈቀርም ያለው ማነው?
-----------------------------------------

እንዲህ አልነበረምኮ ውላችን!ሊጠፋ እንደሚችል አልገመትኩም።ዩኒቨርስቲ ልንሄድ ምደባ የምንጠብቅ ሰሞን አንድ እብድ ሰፈራችንን ተቀላቀለ።እቁብ መጣልና የእድር መዋጮ መክፈል ላይ አልተሳተፈም እንጂ የማህበራዊ ህይወታችን አንዱ አካል ሆነ።ስሙን ሲጠይቁት "እንጃ"ነበር መልሱ።በዚያው ስሙ "እንጃዬ"ሆኖ ፀደቀ።

ቁርሱን አንዱ ቤት...ምሳውን ሌላ ቤት እየጠለፈ፣ራቱንም የራራ እያበላው ተጎራብተን መኖር ጀመርን።የሰፈሩ ጎረምሶች ተረባርበው መጠነኛ የላስቲክ ጎጆ አቆሙለት።

እና በመሀል እኔ የ 19 ዓመቷ ተስፈኛ ተማሪ ከእንጃዬ ለጠየቁኝ ሁሉ 'እንጃ!' የሚያስብል ፍቅር ነደፈኝ።ሲያመጣው ልክ የለው!
"አጃኢብ!....የሰለሞን ልጅ እብድ አፈቀረች"ተባለ።እብደቴ ሰርተፊኬት አገኘ።እናቴ ደነፋች!አባቴ ለያዥ ለገናዥ አስቸገረ።እገድላታለሁ ብሎ በእናቱ ስም ምሎ ሽጉጥ ደቀነብኝ።እኔም የልብ ልብ ተሰማኝና ጨርቄን ሳልል ማቄን እንጃዬ ቤት ከተምኩ።
እንጃዬ ብዙ አያወራም።ሳቅ ብቻ ነው መልሱ።ከስንት አንዴ ካወራም ምንም ይበሉት ምን "ይገርማል"ብቻ ነው የሚለው።
"እንጃዬ ግን ትወደኛለህ?

"ይ...ይገርማል"

"አባቴ'ኮ ሽጉጥ አወጣብኝ እንጃዬ ምን ላድርግ?"

"ሽጉጥ...ሽ...ሽጉጥ"መርበትበት የጀምራል።ሽጉጥ ካየ አልያም ስለሞት ከተወራ እንጃዬ የባሰ ሕመም አለበት።እኔም ነውር አልፈራም ነበር ቲሸርቴን አውልቄ ፊት ለፊቱ እቀመጥና ምላሹን ስጠብቅ

"ይ...ይገርማል "ይለኛል ። በዘመድ አዝማድ ብመከር አልሰማ አልኩ።እረዱኝ አልኩ።የዪኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሲሆን ጎንደር መመደቤን አወቅሁ።ጉዱ የመጣው ይሄኔ ነው።'እንጃዬን ትቼ የትም አልሄድም' አልኩ።ቤተሰቡና ዘመድ አዝማዱ ተረባርቦ የእንጃዬን ቤት አፈረሰው ። እሱ እንደነሱ ክፋት አያውቅ

"ይ...ይገርማል"ብሎ ዝምምም ነው።ክፍሌ ውስጥ ተቆለፈብኝ።አባቴ ቀኑ ሲደርስ ልብሴን በሻንጣ አስይዞ በግድ ጎንደር ሊልከኝ ሲል እጄን በምላጭ ከትፌ ራሴን ለመግደል ሞከርኩ።እናቴ ተንሰፈሰፈች...ግን ምንም ማድረግ አልቻለችም።ያው ተለክፌ አይደል?

እንዳወራ ቢፈቀድልኝ እኮ እንጃዬ ማለት መልዓኬ ነበር። እንደቅዱስ ገብርኤል ሰላምና ደስታን አብሳሪዬ!እሱ የቤት ኪራይ የለበት...የቀለብ ሸመታ አያስጨንቀው...ልብስ ልግዛ አይል ልጠብ የለ...የልጆቹ ነገር አያሳስበው... የቤተሰብ ክብር አይል!ብቻ በዚያ ኑረት ውስጥ ለኔ ብቸኛው ጥሩ ነገሬ እንጃዬ ብቻ ነበር።
የሆነ ምሽት ታዲያ ታላቅ ወንድሜ እና አባቴ ሊገድሉት ሲያሴሩ፣መልዐኬን ሊነጥቁኝ ሲዶልቱ ሰማሁ።ወፈፍኩ!ጨርቄን መጣል ቀረኝ።አብሮ እንደኖረ ቤተሰብ ሳይሆን መንገድ ላይ እንደተገኘ የማይታወቅ ሰው አቀለልኳቸው።ከስፍራቸው አነሱብኝ።የአባቴን ሽጉጥ አንስቼ ጭንቅላቴ ላይ ስደቅነው ወንድም ተብየው

"እስኪ ምላጩን በመሳብ ተባበሪን እስኪ!በፈጠረሽ ይህን ካረግሽ ውለታሽን አንችለውም!" አለኝ።አባትየው ግን ወደማባበሉ ዞረ።

"ህሊናዬ በፈጠረሽ እንዳታደርጊው ያስጠይቅሻል"ሲል ተማፀነኝ።እኔ ግን ብሶብኝ እርርርርፍ!

"ኧኧኧረ!ያስጠይቀኛል?አንተ እንጃዬን ስትገድል መላዕክት አይደሉ 'ሚቀበሉህ?"
እናቴ ከጓዳ ብቅ ብላ የያዝኩትን ስታይ በሚሰቀጥጥ ጩኸት ቤቱን አደበላለቀችው።አንጀቴ ተንሰፈሰፈ።የዚያን ቀኑን የእናቴን ሁኔታ ሳስብ ነው ምን ያህል ልክ እንዳለፍኩ የገባኝ።ልክፍቱ ግን አልተወኝም።

ስህተቴ ማፍቀሬ አልነበረም።ስህተቴ እብድ ማፍቀሬም አልነበረም።ስህተቴ ሰው እንደሚለው ከሆነ ደፋርነቴ ነበር።ለካ አንዳንድ ስሜቶች መዳፈናቸው የግድ ነ መሰለኝ!እንጃ!

መንደርተኛው ''ጉድ ጉድ ጉድ! ለየላት በቃ ይች ልጅ?እብድ አፍቅራ ራሷን ልታጠፋ?ምነው ደህና ልጅ አልነበረች?አይይ!ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ'' ሲለኝ ትልቁን ዳቦዬን ይዤ እንጃዬ ቤት ከተምኩኝ።ዳቦዬ ተባረከች።በእብዱ ካህን የክብር ካባዋን ገፈፈች።ለካ እንጃዬ ዳቦ መባረክ ያውቃል።የኔ ንፁህ!ጣጣችንን ጨርሰን እርቃኔን ከጎኑ ስጋደም ብርግግ ብሎ ተነሳ።ደንግጬ

"ምነው እንጃዬ?"ስለው

"ይ...ይገርማል"አለኝና መልሶ ተኛ።

ጠይም መልክ ከንፅህና ጋር ሲዋሀድ እንደዚህ ነው የሚያምረው?ገላውን የሰፈሩ ወጣቶች በሳምንትም ሆነ በሁለት ሳምንት አንዴ ያጥቡታል።ዳሩ እሱ ባይታጠብም ንፁህ ነው።ተባዮቹ ራሱ እሱጋ የሚመጡት ከየትም የማትገኝ ንፁሕ የደም ጠብታን ፈልገው ይመስለኛል።እርጋታ የሚዘዋወርበት ...ምቀኝነት የማያውቅ እንደ ምንጭ ውሀ የጠራ ደም ከሱ ሰውነት በቀር ሌላ የትም ያለ አይመስለኝም።ዝምታው ለሰሰሰስስስስ ያለ ንፋስ ነበር።ከቀትር ፀሀይ ቀጥሎ የሚመጣ!የሚያበርድ የሚያቀዘቅዝ...እያነቃ የሚያደነዝዝ ዓይነት!!

ልብ ከደነደነ ለካ ሽጉጥ እሾህ ይሆናል!ተተኩሶ የሚገድል ሳይሆን ወግቶ የሚነቀል ቀላል ህመም...እዚያ ሞገደኛ ስሜት ፊት ምንም ነገር ኮስሶብኝ ነበር...ቤተሰብ ኮሰሰብኝ...ሽጉጥ ኮሰሰብኝ...ክብር ኮሰሰብኝ...ዕውቀት ኮሰሰብኝ...ተስፋ ብቻ ነበር የገዘፈብኝ።እንጃዬ ስሜቴን ያውቃል ፣ፍቅራችን የጋራ ይሆናል የምትል የሞኝ ተስፋ!

ከዚያች ምሽት በሁዋላ ታሪኬ መልኩን ቀየረ።ብናስራት ራሷን ታጠፋለች በሚል ስጋት ቤት ውስጥ የሚቆጣኝ ቀርቶ ቀና ብሎ የሚያየኝ ስለሌለ ነፃነቴን እስከጥግ ኖርኳት።ቁርስ ከእንጃዬ ጋር...ምሳም ከሱ ጋር...ራትም እንደዛው...አልፎ አልፎ አዳሬም እዛች የፈራረሰች የላስቲክ ቤት ውስጥ ሆነ።እናቴ ጭንቅ ጥብብ ቢላት
"ህሊናዬ በፈጠረሽ አዳሩ እንኳን ይቅርብሽ...በፍርሀት እሞትብሻለሁ "

"እሜ እንጃዬን ነው የፈራሽው?ይልቅ አባቴንና ወንድሜን ፍሪያቸው"

"እሺ ቢያንስ..."
"ቢያንስ ምን?"አቀርቅራ ዝም አለችኝ።ጭንቀቷ ገባኝ።የዳቦው ነገር አሳስቧት ነበር።

"እሜ የኔ ክብር የሄደው ገና እንጃዬን ሳፈቅር ነው"አልኳት።የኔ አንጀታም!ብርድ ልብስ ሸጥታ ሸኘችኝ!ከዛ ንፁሕ ሰው ጋር ሞቆኝ የሰላም እንቅልፍ ተኛሁ።
የወር ደሜ እንዳልመጣ እያወቅሁ፣ ፀንሼ ሊሆን እንደሚችል እያወቅሁ፣ለሁለተኛ ጊዜ ሽጉጥ ሊደቀንብኝ እንደሚችል እያወቅሁ ዝምታን መረጥኩ ።ሆዴ ገፋ...ራሴው ፈቅጄ በፈፀምኩት ነገር ወንድሜ ፍቅሬን ሊገድልብኝ ሽጉጥ ይዞ ወጣ።እኔስ የዋዛ ነኝ?በረኪናዬን አንጠልጥዬ እየጮህኩ ተከተልኩታ!መንደርተኛው ግልብጥ ብሎ ከቤቱ ወጣ!ሌላ ወሬ ተገኘለት!

"ጉድ በል ሀገር!ህሊና የጋሽ ሰለሞን ልጅ ከእንጃዬ አረገዘች"ተባለ።ቡና እስከ ስምንተኛው እየተጣደ የምቦጨቅበት ርዕስ ተገኘ።በረኪናውን ሲቀሙኝ ዐለሙ ዞረብኝ...እናቴ ወንድሜን መማፀን ጀመረች።
"ዞር በይ እማዬ ፊት ለፊቷ ነው የምደፋላት!"ይላል።እንጃዬ ግራ ገብቶት በዝምታ እያየኝ አለቀሰ።

"ሽሽ...ሽጉጥ"አለ።
ሳለቅስም አባባሁት መሰለኝ።ያልተያዘው አፌ ብቻ ስለነበር የቻልኩትን ያህል ጮሄ ድምፄ ሰለለ።ወንድሜ በምልጃ ብዛት ምላጩን ሳይስብ ወደቤቱ ገባ።ከዚያች እርጉም ቀን በሁዋላ...ያ ሽጉጥ ከተደቀነበት በሁዋላ እንጃዬን በከተማው አየሁት ያለኝ የለም።ግን ተሳስቻለሁ እንዴ?የዛን ንፁህ ሰው ልጅ መግደል ነበረብኝ?
ስህተቴ ማፍቀሬ አልነበረም...ስህተቴ እንጃዬን ማፍቀሬም አልነበረም...ስህተቴ ልጄ አይደለችም...ስህተቴ የተገኘሁበት ቦታ ነበር።ስህተቴ ሰፈሩ ነበር።ለምኩራብ(ለልጄ)ስለአባቷ ሳወራት ገነትን እየጎበኘሁ ይመስለኛል።ስፍፍፍ እላለሁ።

"የዛሬ 6 ዐመት መኖር ጥሞኝ ነበር"እላታለሁ።
5.2K viewsDAVE / PAPI, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 23:15:48
መማረር +ማማር =( ውበት )

ካሊድ አቅሉ


አተኩሬ አየዋት ለዛ ያለው ወሬ እያወራች ቢሆንም በመሀል ቀልቤ ተሰርቆ መልክዋ ላይ አተኩርዋል ከአይን የገዘፈ ልብ ላይ ሚጫወት ነፍስ ያለው ውበት ይታይባታል በድምፆችዋ ጅረት ታግሼ ለደቂቃዎች ገነትን ላይ እራሴን ጥዬ ከምንጭዋ ተጋርቼ የመጣው ይሰማኛል። ንፋሱ ቀልባችንን ላለመረበሽ በስሱ ሚነፍስ ፍቅር አቀጣጣይ ማራገቢያ ይመስላል።

"የት ሄድክ " አለችኝ ሽምጥ የጋለበውን ቀልቤን አይታ
"አለው" አልኩዋት ወደ ምድር ለመመለስ ሳልንደረደር ወርጄ

" ሰማዩን አየህው ፀሐይ ልትገባ ስትል እንዴት እንደ ቀላ "አለችኝ

" አዎ ደሞም እኮ ልትወጣ ስትልም ሰማይ ታቀላለች" አልኩዋት ትዝብቴን ጠቆም ለማረግ ከዛም ቀጠልኩ ...

" ንዳድዋን ስትለቅ ውላ መጥለቂያዋ ሲቃረብ ውበትን , መስከንን, እና ደብዘዝ ብሎ መጉላትን ታሳያለች ጠዋት ልንሞቃት ወተን እናንጋጣለን ቀትር ሲቃረብ እናማራታለን ብቻ የፀሐይ ጉልበት እና ውበት ሁሌም ይደንቀኛል ። ማማር ለካ እያስደሰቱ ብቻ ሳይሆን እያማረሩ ማለፍ ነው ። ውብ ነገር ምንፈልገውን ገነት እንደሚሰራልን ሁሉ የምንርቀውንም ገሀነም ያጎናፅፈናል ። "

ብዬ መልስዋን ለመስማት ጆሮዬን አዘጋጀው ...

" ሆ በል ተነስ ፀሐይን ቁጭ ብለን ስናማ ጨረቃ መጣችብን " ብላ የሁለት ማክያቶ ሂሳብ ጠረጵዛው ላይ አኑራ ቦርሳዋን ይዛ ተነሳች ...............

@wegoch
@wegoch
@paappii
4.3K viewsDAVE / PAPI, 20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 19:08:20 ጎረቤታችን ናቸው። አለም ለእነሱ መዋደድ ግድ የሚሰጠው ይመስላቸዋል ወይ ሰው ባለበት ለፍቅራቸው ምስክርነት መናገር ፍቅር ያጠናክራል የሚል እውቀት ጭንቅላታቸው ውስጥ ሰርጿል ።
እንዴት እንደሚከባበሩ ፣ እንደሚዋደዱ አንዳቸው ለአንዳቸው ስጦታ እንደሆኑ በሆነ ምክንያት ሰብሰብ ስንል መዘብዘብ ይጀምራሉ። የልጃቸውን ልደት አዘጋጅተው ማታ ከቤርሳቤት ጋ ሄድኩ ፤ ጥሩ ሰዎች ስለሆኑ እና ቤርሳቤት ማህበራዊ ህይወት ስለምትወድ ሄድን ። የተገናኙበትን እለት ለዘጠነኝ ጊዜ ሳያዛነፍ ሳይጨመር እየተቀባበሉ ተረኩልን ። ለዘጠነኛ ጊዜ ሰምተነዋል ሳንል ሁሌም ሲነግሩን የምንጠይቀውን ጥያቄ የምናጨበጭበውን ጭብጨባ አጨበጨብን ።
ድንገት እናንተ የት ነው የተገናኛችሁት አለችን ኤልሳ ። ከቤርሳቤት ጋ ተያየን። ፈጠን ብዬ ፦ አዳማ የ leadership ስልጠና ስሰጥ ቢሮዋ ወክሏት ሰልጣኝ ነበረች ። ተከይፌባት በሰበባ-ሰበብ ስልኳን ተቀበልኩ ። ደጅ ጠንቼ እትት ብዬ ይሄው አንድ ልጅ ወለድን
አልኩኝ፤ አለቀ። ውሸት ብዙ አይጎተትም ብዙ ካልተጠና በቀር ቤርሳቤት ዝም አለች።
የአወራሁት ውሸት ነበር ። ለካ ሁሉ እውነት አይወራም ። ለካ የሚከደን ገጠመኝ አለ። ለካ ለራሳችን ደግመን የማንነግረው የሚጎመዝዝ እውነት አለን። እውነታው ፦ ከቤርሳቤት ጋ የተገናኘነው ጭፈራ ቤት ነው የተገናኘን ቀን ነው የተናፋነው ፤ ወሲባችን ፍቅር አልነበረውም ፤ ከአንድ ዙር መፋተግ በኋላ፤ አንድ ዙር ፍቅር አልባ ወሲብ እንዳለቀ ፊቴን አዞርኩ ሲጋራዬን ለኮስኩ ፤ ፊቷን አዙራ ስልኳን መነካካት ጀመረች ። ሁለታችንም ጀብረር ብለን ነበር። ምንም ያላወራው ይመስለኛል ፤ እርግጠኛ ነኝ ከዚህ በኋላ አንገናኝም ፤ በአንድ ቀን የምትጋደም ፣ ከሴተኛ አዳሪ ገንዘብ ባለመቀበል ብቻ የምትበልጥ ወይም የምታንስ ልጅ ማን ቁምነገር ይሰጣታል። አስክሮ ፣ እትትት ብሎ የሚቾምስ አለሌ ሸሌ ወንድ ለቁምነገር እንደማይሆን እርግጥ ነው። ተኛን !
ሳንተቃቀፍ ተኛን።
እኩለ ለሊት እንዳለፈ ይመስለኛል አመመኝ ከተኛሁበት አልጋ ተስፈንጥሬ ከአልጋዬ ብዙ
ሳልርቅ ወለሉ ላይ አስመለስኩ ።
ከመቅፅበት ተነስታ ከጎኔ መጥታ ልቤን ያዘችልኝ ፤ ከሆዴ ጀምሮ አማጥኩኝ ፣ አማጥኩኝ አቅም አነሰኝ እና ጥምልምል አልኩ ፤ መታገል ፣ ማጓራት ብቻ የሚወጣ ግን የለም ውሃ ጠጣ ብላ ሰጠቺኝ ፤ ትንሽ ጠጣሁ አፍታ ሳይቆይ የጠጣሁትም ውሃ ወጣ ። ቀና በል ፥ ይሸትኻል አለቺኝ ፤ ትውከቱ እንዳይሸተኝ ቀና እያደረገችኝ ፤ እሷን ተደግፌ ቀና አልኩ ጨርቅ አምጥታ (ከውስጥ የለብስኩትን ቦዲ) ውሃ ነክራ አንገቴን ፣ ግንባሬን አራሰችልኝ ፤ ቅዝቅዝ አለኝ ። ቀስ ብዬ ጠቅልል ብዬ ተኛሁ ፤ ስትንጎዳጎድ እንቅስቃሴዋ ይሰማኛል ፤ አቅሜ ተዳክሞ ስለነበር ለጥ አልኩ ። ጠዋት ስነቃ እና ማታ የሆነውን ሳጤነው ሁኔታዋ እና እንክብካቤዋ አንጀቴን በላው።
ትውከቴ ከቦታው የለም ፤ እንዴት አልተፀየፈችውም ፤ ማን ስለሆንኩ አንደዚህ
ተንከባከበቺኝ ?! አብረን ቁርስ በላን ። ስለማታው ሁኔታ ምንም አላወራንም ፤ አፈርኳት ፤ ውለታዋ ቆጠበኝ። ከዛ ቀን በኋላ አብረን ነው የምንውለው። ተልካሻ ስፍራ ፤ በማይረባ ሁኔታ እንዴት እንደዚህ ግጣሜን ላገኝ ቻልኩ ።
በሁለት ወር ከአስራምስት ቀን ዳግም ለሁለተኛ ቀን ተዋሰብን ፤ ያኔ ሰውነቴ ተቀብሏት
ነበር ፤ ሰውነቷ ተቀብሎኝ ነበር እናም ተዋሃድን ፤ የሚዋደዱ ሰዎች ሲዋሰቡ ወሲቡ
ውህደት ነው ፣ የነፍስ ቁርኝት ፤ ተቆራኘን።
ውድ ቦታ እና ቅዱስ ቦታ ብቻ ነው ትክክለኛ ሰው የሚገኘው ያለው ማነው? ህይወታችን የሚመዘነው በምናገኘው ደስታ ነው ።
ዛሬ አምናታለሁ ! የምትንዘላዘልበትን ምክንያት ደፍኜዋለሁ ፤ ፍቅሬ እንድትታመነኝ ሰርቷታል
። እንደትላንት እንዳልሸረሙጥ ከእሷ ጋ ያለኝ ነገር ይጋርደኛል ። ሰው መቼ በተገናኘበት ስፍራ ብቻ ይመዘናል ፤ ያለንበት ስፍራ ሁሌ መቼ ልካችን ሆኖ ያውቃል። አጀማመራችን ሳይሆን አካሄዳችን ነው የማንነታችን ማሳያ ። ይሄ በልባችን የተፃፈ የምንኖረው እውነት ነው ። ይሄን እውነት መግለፅ ረብ ለሌለው ትዝብት መጋለጥ ነው። ሁሉ እውነት አይነገርም። አንዳንዴ አንዳንድ ውሸት ከእውነት ይበልጣል ።


@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
4.9K viewsDAVE / PAPI, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 21:41:27 እንደሚሞት እያወቅሁ አክመዋለሁ (ክፍል 6)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

...ከመተኛቴና ከመነሳቴ በፊት ለሱ ዕድሜን መለመን የዘውትር ፀሎቴ ሆነ።እኔምኮ እሞታለሁ...ግን ከሱ መቅደምን ሻትኩኝ።በልቤ ይገባው አይገባው ባላውቅም ትልቅ ቦታን ሰጠሁት።ቀስ በቀስ የስዩምን ቦታ እያጣበበው እንደሆነ ታወቀኝ።እየራቋት የሚሄዱ የብርሀን ጭላንጭል ቀስ በቀስ እንደምትደበዝዝና እንደምትጠፋው ላቆመው ያሰብኩት ጎጆ መሰረቱ እየተወላገደና እየነካከተ ሲከስም ይታወቀኛል።

ስዩም ሲደውል አንስቶ ማናገሩ ከምንም በላይ ቀዝቃዛ ስሜት እና እኔ ነኝ ያለ ድብርት ውስጥ ይጥለኛል።ድምፁ 'ተኮንነሻል አንቺ ከንቱ!'የሚል የገሀነም ጥሪ ይመስለኛል።ልብ ካላዘዘ አካል ግዑዝ አይደል?ዐይን ሌላ ሲያማትር አይደል የትዳር የመፍረሻ ደወሉ የሚያቃጭለው?ሌላን ሰው መንካት...ሌላን ሰው መሳም...ከሌላ ሰው ጋር አካል መጋራት አይደለምኮ የመወስለት ማስረጃው።የመወስለት ንጋት ወገግ ብሎ የሚታየው ልብ ለሌላ ሲመታ ነው።

የኔም ልብ ለስዩም ማዜሙን እየተወ ደም የሚረጨው ለዳንኤል ሆነ!ለሚሞተው ታካሚዬ...እኔም በሁለቱ መሀል መሰነጉ የተመቸኝ ይመስል ዝምታዬን አስታመምኩት።እጄ ላይ እየሟሟ እያየሁት...ቫይረሱ እያሸነፈው እየወደቀ እያየሁት...መድሀኒት አልፈልግም እያለ እያስለቀሰኝ እንኳን የውስጤን ለሁለት መከፈል የወደድኩት ይመስል ዝም አልኩ።

አንዳንዴ ለኔ ያለው ጥልቅ ፍቅር ነው ወይስ ጥልቅ ጥላቻ ብዬ ግራ እስከሚገባኝ ድረስ ያቆስለኛል።በነጋታው ነፍስ በሚያለመልም ንግግሩ ይጠግነኛል።

መድሀኒቶቹን ሰብስቦ ያመጣና ዐይኔ እያየ የቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ይጥላቸዋል።ምርርርርር ብዬ እያነባሁ አይቶ እንዳላየ ጥሎኝ ይሄዳል ።በቀጣዩ ቀን የጣለውን እጥፍ መድሀኒት ያመጣና ፊት ለፊቴ እየዋጠ "ከንግዲህ አላስለቅስሽም እመኚኝ"ሲል ምሎ ተገዝቶ ይሄዳል።ትናንት ያለቀስኩትን አምስት እጥፍ የሚሆን እንባ አፍስሶ

"ቆይ እኔ ግን ምናይነት ሰው ነኝ?ለምን አትገይኝም? በናትሽ ግደይኝና ፅደቂ!"አንተን ብሎ አፍቃሪ!እስኪ መጀመሪያ ዕድሜህን አስላ!'ብለሽ ተቆጭኝ!አልገርምሽም ግን?እየሞትኩ ስወድሽ ምንድነው 'ሚሰማሽ?መሞቱ አይቀርም ብለሽ ችላ ብለሽኝ ነው ወይስ መፈቀሩ ተስማምቶሻል?ምናይነት ሴት ነሽ ኧረ?እኔስ ምናይነት ደነዝ ነኝ?"

ምናይነት ፍቅር ነው ይሄ በማርያም!ዛሬ እንደዚህ ብሎ በነጋታው

"ባላውቅሽ የምሞተው ከዐመት በፊት ነበር ዶክተር።አንድ ዐመት የኖርኩት በዚህ መድሀኒት እንዳይመስልሽ...ባንቺ ነው።ፈጣሪን ነገን አሳየኝ ብዬ የምማፀነው ላየው የምናፍቀው አንድ ጥሩ ነገር ስላለ ነው ግዝሽ።እናቴኮ በሽታዬን አታውቅም ዶክተር።አንቺን ማፍቀሩ ነው በሽታዬ የሚመስላት።ታውቃለች እንዴት እንደምወድሽ።ይህን ጠጠር የምውጠው አንቺን ለማየት ነው በቃ''ይልና እያየሁት መድሀኒቱን ይውጣል።

በሌላ በኩል ስዩም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የቀረው አንድ ሳምንት ብቻ ነው።አይቀሬው ሰርግ ደግሞ ከ 15 ቀናት በሁዋላ ይደገሳል።ሙሽሪት አካሏ ቬሎ ልቧ ማቅ ለብሶ አበጀሽ የኛ ሎጋ ሊባልላት ነው።ሁሉም ደስተኛ ሆኗል ።ከኔና ከዳኒ በቀር።እናቴ "ላይቀርልሽ አታለቃቅሺብኝ"አይነት ንግግር ተናገረችኝ።ለነገሩ ልክ ናት።ሁለት ነገሮች አይቀሬ ናቸው።አንድም ሰርግ...አንድም ቀብር...በጥቁር ቬሎ ላግባ ይሆን?


ይቀጥላል።

በማዕዶት ያየህ

12/07/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
5.1K viewsDAVE / PAPI, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 06:40:34
የድርቁን ነገር ብዙ ተማክረን ነበር፤ እኔስ ከብቶቼን ይዤ ሸሸው። የልጅ ምክር የማይሰሙ ጎረቤቶቼ ግን ሲያፌዙብኝ ነበር። ይኸው ረሀብ መጣ የነገርኳቸውም ደረሰ። አሁን ከዚ ግጦሽ አጭጄ ብሰድላቸው ስንት ከብት ይተርፍ ይሆን?
ሚስኪን ከብት በፌዘኞች ጥፋት ለሚሰዋ!
..................
2013, ድንባሮ
@ribkiphoto
@wegoch
@wegoch
.................
4.8K viewsRibka Sisay, edited  03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ