Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2022-06-23 22:13:38 ዳታ በቀላሉ በStata እንዴት ይተነተናል ?/ How to interpret descriptive data results in Stata?

ከዚህ በፊት ዳታ ወደ SPSS እንዴት ማስገባት እንደሚቻል፤ እንዴት መተንተን እንደሚቻል እና እንዴት ቻርት ማውጣት እንደሚቻል አቅርቤላችሁ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በቀላሉ በStata እንዴት Descriptive ውጤት እና ግራፍ ማውጣት እንደሚቻል ይህንን

አጭር ቪዲዮ ሰርቻለሁ፡፡

የዚህ ቪዲዮ ዓላማ ሰዎች እንደመነሻ እንዲወስዱት እና ተጨማሪ ሌሎች መጽሃፍትን እና ቪዲዮችን በመመልከት ጥናታቸውን በቀላሉ በአቅማቸው ልክ መስራት እንደሚችሉ ለማስረዳት ያህል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በSPSS እንዴት ዳታ ማስገባት እና መተንተን እንደሚቻል የሰራሁትን ቪዲዮ ለምትፈልጉ ከታች ያለው ሊንክ ተጠቀሙ፡፡









7.8K viewsWasyhun Belay, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 19:04:04 ኢኮኖሚክስ ርህራሄ የለውም "Economics has bias" ይባላል! #ለምሳሌ፦ "የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ያገኛችሁትን ስራ ስሩ!" በሚል ምክር ሰዎች ጫማ መጥረግ ሲጀምሩ በተመሳሳይ "የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ለጫማ ማስጠረግ ወጪ ከምታወጡ ቀለም ገዝታችሁ በቤት ጫማችሁን አፅዱ!" የሚል ምክር ደግሞ ይሰጣል!
7.2K viewsWasyhun Belay, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 21:07:48 ፍራንኮ ቫሉታ የባለብዙ አደጋ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔ ቢሆንም ላለው አነስተኛ ጥቅም ሲባል የሚተገበረው ለምን ይመስላችኋል?

የኢትዮጲያ መንግስት የውጪ ምንዛሬ ያላቸው ሰዎች በማሳወቅ ብቻ ከውጪ የተወሰኑ መሰረታዊ ቁሳቁሶችን በማስመጣት እንዲሸጡ ፍቃድ መሰጠቱ ይታወቃል! ነገር ግን ይህ ውሳኔ የጎላ ጉዳት ቢኖረውም ውሳኔው ለኢኮኖሚው በተለይ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ጥቅም አለው በሚል እሳቤ ቀጥሏል! ታዲያ የሚታይ ጉዳት ያለው የፍራንኮ ቫሉታ ውሳኔ እንዲቀጥል የሚደረግበት መሰረታዊ ምክንያት ምን እንደሆነ ለመረዳት ይህንን ቪዲዮ

ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡
7.9K viewsWasyhun Belay, 18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 09:13:07 የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ችግር ከአቅርቦት ማነስ ወይስ ከፍላጎት ማደግ የመነጨ ነው?


በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ የብዙ ሀገራት ችግር ለዜጎቻቸው በቂ የሆነ የቁሳቁስ፤ የአገልግሎት እና የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ማዳረስ ነው፡፡


በተመሳሳይ የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፍላጎት ያለበት ቢሆንም አቅርቦትን በተመለከተ የባለብዙ ክፍተት ነው፡፡


ፍላጎት እና አቅርቦት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የኢትዮጲያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር የአቅርቦት በየጊዜው ማደግ ወይስ ተፈላጊው አቅርቦት ያለመጨመር?


በጠየቃችሁኝ መሰረት በምሳሌ በማስደገፍ ይህንን ቪዲዮ

አቅርቤላችኋለሁ እስከ መጨረሻው ተከታተሉ፡፡
7.7K viewsWasyhun Belay, edited  06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 22:47:53 ለጥናታችሁ በExcel የሚያምር 3D ቻርት እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?/How to make 3D pie chart in excel? ከዚህ ቀደም በነበሩ ቪዲዮዎች በSPSS ዳታ እንደሚገባ እና እንዴት እንደሚተነተን ሰርቼላችሁ ነበር! ዛሬ ደግሞ ከSPSS የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ በSPSS ፓይ ቻርት እና በExcel የሚያምር Pie chart አዘገጃጀት አሳያችኋለሁ። በጣም ጠቃሚ እና ሳቢ ጥናት እንድትሰሩ ስለሚያግዝ እስከመጨረሻው ተከታተሉ።

7.3K viewsWasyhun Belay, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 19:07:29 የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ጥቅም ወይስ ጉዳት/The effect of currency devaluation።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ (Devaluation) በጣም ጠቅሞናል! ይህንን ጉዳይ ለኢኮኖሚስቶች ካልሆነ በስተቀር ለመረዳት አዳጋች ነው! ስላሉት ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥቸበታለሁ፡፡


የብር የመግዛት አቅም መዳከሙ እድል ብቻ ሳይሆን ጉዳትም ይዞ መጥቷል ይህንን በምሳሌ በማነጻጸር የሚከተለውን ቪዲዮ ሰርቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡




8.0K viewsWasyhun Belay, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 13:38:39 በርካታ ሰዎችን መንግስት የሚያቀርበውን #የዋጋ_ንረት ቁጥር እንደሚያምኑ ስጠይቃቸው፡ ሁሉም በተመሳሳይ ገበያ ውስጥ የሚገጥማቸው የዋጋ ግነት እና መንግስት የእቃ ዋጋ 36% ነው የጨመረው የሚለው አይታመንም አሉኝ።


እርግጥ የመንግስት ወራዊ እና አመታዊ የዋጋ ንረት ቁጥሮች በማህበረሰብ እይታ አጠራጣሪ የሚሆኑበትን አሳማኝ አመክንዬ ልንገራችሁ።


1. የዜጎች የሸመታ አይነት መረጃ የቆየ መሆን። ሃገራት ከ3 እስከ 5 ዓመት የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ናሙና በመውሰድ በአብዛኛው ሰዎች ምን ምን በብዛት እንደሚሸምቱ (Household consumption survey) መረጃ ይሰበሰባል። ስለዚህ የዛሬ አምስት አመት በቤተሰቦች የሚዘወተር ሸመታ ዘንድሮ እንደቀጠለ ያስባል።


በተመሳሳይ የዛሬ ከ3 እስከ 5 ዓመት አንድ ቤተሰብ ለወራዊ እና አመታዊ ለፍጆታ የሚያወጣው ወጪ (Households expenditure survay) ዘንድሮም እኩል እንደሆነ ያስባል።


#ለምሳሌ፦ የዘንድሮ ዋጋን ለማነፃፀር የዛሬ 5 ዓመቱን መነሻ (Base year) አድርጎ መውሰድ ማለት ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ 5 ዓመት ስጋ በቤተሰብ ደረጃ በተደጋጋሚ የሚሸመት ከሆነ ትልቅ የወጪ ክብደት (Weight) የተሰጠ ቢሆን እና አሁን ላይ በወር አንዴም ስጋ ለማይገዛ ቤተሰብ ስጋ ትልቅ ክብደት ተሰጥቶ ቁጥሩ ይሰላል።


በተመሳሳይ የወጪም ሆነ የሸመታ ዝርዝር ተሰብስቦ የሚቀርበው አማካይ ቁጥር ከጎንደር ጥግ እስከ ጂግጂጋ ጥግ ተመሳሳይ ተደርጎ መቅረቡ በየቦታው ልዩነት ቁጥሩ ያወዛግባል።


2. የዋጋ ንረት ዓመቱን ሙሉ የተለዋወጠ ዋጋን ሲወስድ የሚሰበሰበው ዋጋ ከ150 በላይ ቁሶችን ጨፍልቆ ስለሚያሰላ የቀነሰውንም እጥፍ የጨመረውን ጠቅልሎ ስለሚይዝ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚፈልጓቸው ቁሶች ዋጋ እጥፍ ቢጨምሩም የ150 ቁስ አማካይ ሲሰራ ቁጥሩ አይዋጥም።


#ለምሳሌ፦ አንድ ቤተሰብ ዋናው ወጪው የቤት ኪራይ፤ ጤፍ፤ ዘይት፤ ሽንኩርት፤ ቲማቲም፤ ወዘተ ተሰብስበው ዋና ዋናዎቹ 10 ሊሆኑ ይችላሉ! እነዚህ 10 አስቤዛዎች ከአምናው ሁሉም 100% ዋጋቸው ቢጨምር ይህንን ቤተሰብ የሸቀጦች ዋጋ ንረት በ36% የጨመረው ቢባል ሊቀበል ይችላል?


#ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ ከጠቅላላ የዋጋ ንረት ድርሻ ውስጥ 56% ከምግብ ነክ የሚነሳ ሲሆን 44% ምግብ ካልሆኑ ቁሶች ይነሳል።


ተወደደም ተጠላም ዓለም የዋጋ ንረትን ለማስላት የሚመራበት ስሌት ከላይ ባስቀመጥኳቸው መርሆዎች ነው።


አንዳንድ ሀገራት የሸመታ እና የወጪ መረጃን ከ3-5 ከመጠበቅ በየዓመቱ እንዲሆን ያደርጋሉ። በተመሳሳይ የዋጋ ንረት አሃዙን በየከተሞቹ በመሰነጣጠቅ ያቀርባሉ።


#ለምሳሌ፦ በኢትዮጵያ አንዳንድ ክልሎች ከአዲስ አበባ እና ድሬደዋ ከተሞች በላይ ዋጋ ንረት እንዳለባቸው የCSA ሪፖርት ያሳያል።


የዋጋ ንረት ሲሰላ ቁጥሩን ፖለቲካሊ መነካካት ሊኖር ይችል ይሆናል! ነገር ግን የስሌት አካሄዱ በተለይ የመሰረታዊ ቁሶች ዋጋ ከፍተኛ በሆነበት ወቅት ቁጥሩ ብዙዎችን አያሳምንም።
6.9K viewsWasyhun Belay, edited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 20:42:07 #ጤነኛ_መግለጫ_ነው?

የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፦ "በመዲናዋ የመንግሥት ሠራተኞችን #የኑሮ_ውድነት_ጫና ለማቃለል 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ዘይት እና 3 ሺህ 500 ኩንታል ስኳር በተያዘው ሰኔ ወር ስርጭት ለማካሄድ ታቅዷል"፡፡ የሚል ዜና አየሁ!


የእውነት የዚህ አይነት መግለጫ የኑሮ ውድነት ትርጓሜን ካለመረዳት የሚነሳ መሆን አለበት እንጂ ለአንድ ወር በሸማቾች ዋጋ #በኮታ ዘይት እና ስኳር ማቅረብ እንደ ኑሮ ውድነት ጫና ማቃላያ መጋነኑ ልክ አይመስልም።

#ለምሳሌ፦ የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋም 42 ብር ከ16 ሳንቲም እንደሆነ መረጃው ያመላክታል፡፡


በሸማቾች በኩል ምርቶችን ለመንግሥት ሰራተኛው ማቅረብ መጥፎ አይደለም ነገር ግን ጊዚያዊ (Nominal) ድጋፍን እንደ ኑሮ ጫና የማቃለል እርምጃ ማቅረብ የኑሮ ውድነት ትርጓሜን ያቀጭጫል።
6.2K viewsWasyhun Belay, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:57:59 ከዚህ ቀደም በSPSS ዳታ እንዴት ማስገባት እንደሚቻል ቪዲዮ ከለቀኩ በኋላ ዛሬ ደግሞ ወደ SPSS የገባው ዳታ በቀላሉ የDescriptive output መተንተን እንደሚቻል አቅሪቢያለሁ! ጥናት ለምትሰሩ ሰዎች ያግዛችኋል ብዬ አስባለሁ!

6.6K viewsWasyhun Belay, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 15:13:10 Channel photo updated
12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ