2022-10-21 19:30:53
በዚህ ወቅት የኢትዮጲያ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለ21 ቀን የሚያሸምት ነው! ምን ማለት ነው?
በዓለም ላይ ያሉ ሀገራት የውጪ ምንዛሬ ክምችት በብሄራዊ ባንኮቻቸው በኩል በሀገር ውስጥ አልያም በሌሎች ሀገራት ባንኮች ውስጥ እንደሚያደርጉ ይታወቃል፡፡ የውጪ ንግዶች ግብይት በአብዛኛው የሚደረገው በዶላር በመሆኑ ሀገራት ከፍተኛ ዶላር ከውጪ ምንዛሬ ግኝቶቻቸው ላይ ያስቀምጣሉ እሱ Foreign-Exchange Reserves ይባላል (የሌሎች ጠንካራ ምንዛሬ ያለባቸው ሀገራትን ገንዘብንም ሊያስቀምጡ ይችላሉ)፡፡
ሀገራት የውጪ ምንዛሬ ከውጪ ንግድ (Export)፤ ከብድር፤ ከእርዳታ፤ ከውጪ ከጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI)፤ ሌሎች ሀገራት ካሉ ዜጎጃቸው (Remittances)፤ ከቱሪዝም፤ ወዘተ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
የሚያከማቹትን የውጪ ምንዛሬ ከውጪ ሀገራት የሚፈልጓቸውን ቁሳቁሶች እና አገልግሎት ለመሸመት ሊጠቀሙበት ይችላሉ (ክምችቱ በዶላር አልያም በዓለም አቀፍ ቦንድ ሊሆን ይችላል)፡፡ ገንዘቡ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ጤነኛ ባልሆነባቸው ጊዚያት እንደ ዋስትን ያገለግላል፤ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን የመግዛት አቅም ለመቆጣጠር ያግዛል…..
#ለምሳሌ፡- በቂ የውጪ ምንዛሬ ያከማቸ ብሄራዊ ባንክ የገንዘቡን የመግዛት አቅም እንዳይወርድ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ እንዴት? በቂ የውጪ ምንዛሬ በሌለበት ገበያ ሰዎች ወደ ጥቁር ገበያ የሚኖራቸው ፍላጎት ስለሚያድግ በጥቁር ገበያ የአንድ ዶላር የምንዛሬ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል ምክንያቱም ብሄራዊ ባንክ የሰዎችን የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ በቀላሉ መመለስ ስለማይችል ነው፡፡
በዓለም አቀፍ ገበያ ጤነኛ የሚባለው መደበኛ የመሸጥ እና የመሸመት ሂደት ሲስተጓጎል ሀገራት ከውጪ ምንዛሬ ክምችታቸው እያወጡ ማክሮ ኢኮኖሚውን ከዋጋ ንረት እና ከምርት እጥረት ይታደጋሉ፡፡
#ለምሳሌ፡- አንድ ሀገር በዓመት ውስጥ 10 ቢሊየን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ከተለያዩ ምንጮች አግኝታ በተመሳሳይ ለተለያዩ ዓመታዊ ወጪዎቿ (ተገቢውን የውጪ እዳ መክፈልን ጨምሮ) በሙሉ 8 ቢሊየን ዶላር ወጪ ብታደርግ 2 ቢሊየን ዶላር ለመጠባበቂያ በሚል ብታስቀምጥ 2 ቢሊየን ዶላር ተቀማጭ ወይም በግምት ለ3 ወር የሚቆይ የሸመታ አቅም ያለው ክምችት አላት እንደማለት ነው፡፡
#ለምሳሌ፡- ቻይና እና ጃፓን ወደ ውጪ በመላክ የሚያገኙት ገቢ ከውጪ ከሚሸምቱት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ በመሆኑ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ክምችት አላቸው፡፡
የተወሰኑ ያደጉ እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የውጪ ምንዛሬ ክምችታቸው የምን ያህል ጊዜ የሸመታ አቅማቸውን እንደሚሸፍን ለማየት ያህል አሜሪካ ለ3 ቀን፤ ጀርመን ለ9 ቀን፤ ፈረንሳይ ለ27 ቀን፤ ኬንያ ከአራት ወር በላይ፤ ህንድ ለ8 ወር፤ ጃፓን እና ቻይና ከአንድ አመት በላይ፤ ሲዊዘርላንድ ከ2 ዓመት በላይ፤ ኢትዮጲያ ለ21 ቀን፤ ወዘተ ነው፡፡
ይህንን መረጃ ጉግል በመግባት መመልከት ይቻላል፡- In the latest reports, US Foreign Exchange Reserves equaled 0.1 Months of Import in Aug 2022, In the latest reports, Germany Foreign Exchange Reserves equaled 0.3 Months of Import in Jul 2022, Kenya Foreign Exchange Reserves equaled 4.9 Months of Import in Jun 2022, Switzerland Foreign Exchange Reserves equaled 31.5 Months of Import in Aug 2022, In the latest reports, France Foreign Exchange Reserves equaled 0.9 Months of Import in Jul 2022.
በቂ የውጪ ምንዛሬ በብሄራዊ ባንኮቻቸው ማከማቸት የቻሉ ሀገራት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ተጨማሪ ብድር ለመቀበል የሚኖራቸው መተማመኛ ደረጃ የተሻለ ነው ሊሉ ይችላሉ፤ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የተለያዩ አደጋዎች በሚፈጠሩ ጊዜ እና መደበኛ እንቅስቃሴዎች ሲስተጓጎሉ እንደ ዋስትና ሆኖ ያገለግላል (የ2008 የፋይናንስ ቀውስ ወቅት፤ በኮቪድ ወቅት፤ አሁን ደግሞ በራሽያ እና ዩክሬን ጦርነት ወቅት፤ ወዘተ ወቅት ሀገራት ችግሮችን አልፈውባቸዋል)……
የውጪ ባለሃብቶች ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ የሃገሪቷን የውጪ ምንዛሬ ክምችት እንደ መተማመኛ ይቆጥራሉ! ስለዚህ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ክምችት አለ ማለት የሰሩበትን በቀላሉ መቀበል መቻላቸውን በመተማመን በዛች ሀገር ኢንቨስት ለማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ የውጪ ምንዛሬ ክምችት የሌላት ሀገር በዓለም አቀፍ አበዳሪ ሀገራት እዳ የመክፈል አቅሟ ደካማ ነው ስለሚባል ከፍተኛ የብድር ወለድ እንዲሰላባት ሊያደርግ ይችላል፡፡
የውጪ ምንዛሬ ክምችት መጠን እድምታው ለሁሉም ሀገራት ተማሳሳይ አይደለም ምክንያቱም ኢትዮጲያ እና ጀርመን ለዓለም አቀፍ ተቋማት የብድር ጥያቄ ቢያቀርቡ ተመሳሳይ መስፈርት፤ የውጪ ባለሃብቶች ኢትዮጲያ እና ጀርመን ሀገር ኢንቨስት ለማድረግ ተመሳሳይ መስፈርት ሊኖራቸው አይችልም፡፡
#ለምሳሌ፡- በተለይ የየሃገራቱ የውጪ ምንዛሬ ክምችት መጠንን በተመለከተ ተመሳሳይ መስፈርት ባለሃብቶች ሊኖራቸው አይችልም! ምን ማለት ነው አንድ ህንዳዊ ባለሃብት ጀርመን ሀገር ኢንቨስት በማድረጉ ገንዘቡን በውጪ ምንዛሬ የማግኘት እድሉ ኢትዮጲያ ውስጥ ኢንቨስት የማድረግን ያህል በብዙ መለኪያ አያሰጋውም ለማለት ነው፡፡
ሀገራት ለአደጋ ጊዜ ከሚኖራቸው ክምችች በላይ በፍጥነት ኢኮኖሚያዊ አቅሞቻቸውን ለማጠናከር የንግድ ሚዛን ክፍተታቸው ዝቅተኛም ሆኖ የውጪ ምንዛሬ ክምችታቸው ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ምን ማለት ነው? ፈረንሳይ የውጪ ምንዛሬ ክምችቷ ከኬንያ በታች የሚያቆያት መሆኑ ሀገራቱ ያላቸውን የውጪ ምንዛሬ ለመጠቀም የወሰኑበትን ደረጃ እንጂ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ እና ድክመትን አመላካች ነው ማለት እንዳልሆነ ያሳያል፡፡
#ማስታወሻ፡- IMF በዘንድሮ ትንበያው የቀጣይ ዓመት የኢትዮጲያ የውጪ ምንዛሬ ክምችት የሸመታ አቅም አሁን ካለበት 21 ቀን ወደ 18 ቀን ዝቅ ሊል ይችላል ብሏል፡፡ በ2014 ኢትዮጲያ ከውጪ የሚያስፈልትን ቁሳቁሶች በተወሰነ መልኩም ለመሸመት ከ18 ቢሊየን ዶላር በላይ እንዳወጣች ይታወቃል ስለዚህ በ2022 በግርድፉ ከተሰላ 1.03 ቢሊየን ዶላር ገደማ የውጪ ምንዛሬ ክምችት በካዝናዋ አላት እንደማለት ነው፡፡
7.1K viewsWasyhun Belay, 16:30