Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-05 19:06:01 የዓለም ባንክ ሃገራት ቢያንስ የ15 ከመቶ የግብር ገቢ ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) ምጣኔ ቢኖራቸው ጥሩ ነው ይላል!


ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ ያለው ድርሻ በዓመት ውስጥ የሚሰበሰብ የግብር መጠን በዓመት ውስጥ ለሚመዘገበው ጠቅላላ ኢኮኖሚ ምርት መጠን (GDP) በማካፈል የሚገኝ ስሌት ነው፡፡


#ለምሳሌ:- በኢትዮጲያ በ2016 ዓ/ም 440 ቢሊየን ብር ከግብር ቢሰበሰብ እና ለጠቅላላ ሃገራዊ ምርት 7 ትሪሊየን ብር ቢካፈል (ማለትም 130 ቢሊየን ዶላር* በ54ብር ምንዛሬ ተባዝቶ 7 ትሪሊየን ብር ቢመጣ) ግብር ከጠቅላላ ሀገራዊ ምርት (GDP) 6.2 ከመቶ ሊመጣ ይችላል (በ2016 ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ 520 ቢሊየን ብር ተገማች ገቢ ውስጥ 440 ቢሊየን ብሩ ማለትም 84.6 ከመቶውን ከግብር ነው!)፡፡


#ለምሳሌ፡- የአውሮፓ ሃገራት ከፍተኛ የግብር ከጠቅላላ ኢኮኖሚ ምጣኔ አላቸው (ሲዊድን (42 ከመቶ)፤ ዴንማርክ (35 ከመቶ)፤ ፈረንሳይ 45 ከመቶ፤ ወዘተ የደረሰ ሽፋን ሲይዙ)፤ አሜሪካ (26 ከመቶ)፤ ቻይና (4.6 ከመቶ (የትልልቅ ተቋማት ባለቤት መንግስት ከመሆኑ ጋር ሊገናኝ ይችላል)፤ ህንድ (11 ከመቶ)፤ ግብጽ እና ኬኒያ (13 ከመቶ)፤ ናይጄሪያ (10.8 ከመቶ)፤ ወዘተ፡፡


ግብር ብቸኛ የኢኮኖሚ የገቢ ዋስትና ላይሆን ይችላል! በዓለም ላይ 14 ሀገራት ምንም የገቢ ግብር ከኢኮኖሚው የማይሰበስቡ ሲሆን ከነሱ ውስጥም የተባበሩት አረብ ኢሚሬት፤ ባህማስ፤ ሶማሊያ፤ ባህሬን፤ ኪዌት፤ ኳታር፤ ወዘተ፡፡ ምክንያታቸው የተለያየ ቢሆንም ገቢን ከሌሎች ሴክተሮች ለመሰብሰብ፤ በግብር ቅነሳ አምራች እና ሸማች ክፍሉ ከጫና ተላቆ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ፤ ሀገራቸውን ለዜጎቻቸው መኖሪያነት ምቹ ለማድረግ፤ የውጪ ኢንቨስትመንት ወደ ሃገራቸው ለመሳብ፤ ወዘተ ሲሉ ነው፡፡


የስትራቴጂ ትግሉ፡- ከአምራች ክፍሉ ግብርን በመቀነስ የካፒታል እጥረት ሳይገጥመው በመንቀሳቀስ ከፍተኛ የስራ እድል እንዲፈጥር እና ከፍተኛ ምርት እንዲያመርት መፍቀድ በሚለው እና ከሚጣል ከፍተኛ ግብር የሚገኘውን ገቢ ለኢኮኖሚው የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን እና ድጎማዎችን ለማቅረብ ማሰብ መካከል ነው፡፡


ነገር ግን እንደ ኢትዮጲያ ከግብር ማዕቀፍ ውጪ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተሳታፊዎችን በማስቀመጥ እና የግብር አሰባሰብ ህግ እና አሰራር ደካማ በመሆኑ የሚነሳ ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ ያለው ድርሻ ማነስ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተቋማት ድክመት እንጂ እና ስትራቴጂ መሆን አይችልም፡፡




2.5K viewsWasyhun Belay, 16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 08:44:00 የውጪ ባንኮች መግባት ብቻውን በኢትዮጲያ Liberalization ተከናወነ ላያስብል ይችላል! ምክንያቱም መንግስት ከውሃ እና መብራት ክፍያ ጀምሮ እስከ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ክፍያ እና ጠቅላላ የመንግስት የፕሮጀክቶች ሞዳሊቲ ተቀማጭ እና ፋይናንስ ስርዓትን በመንግስት ባንክ እና በቴሌ በኩል ሞኖፖሊ ማድረጉን ማቃለል ከጀመረ ምን አልባት ሊሆን ይችላል፡፡
3.5K viewsWasyhun Belay, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:04:54 ግብር ከጠቅላላው ኢኮኖሚ (GDP) ያለው ድርሻ ስሌት| በኢትዮጵያ ግብር ከGDP ያለው ድርሻ 6.4%| የግብር መጠን ማነስ ስትራቴጂ ወይስ ድክመት? የዓለም ተሞክሮ እና የኢትዮጵያ ንፅፅር! ኬንያ ከኢትዮጵያ በእጥፍ የሚበልጥ ግብር ከጠቅላላ የኢኮኖሚ አቅም (GDP) ንፅፅር መያዟ እንደሃገር ምንን ያመለክታል?


ይህን በተመለከተ የሚከተለውን

ትንታኔ  ይመልከቱ!
3.9K viewsWasyhun Belay, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 12:23:35 አዲስ አክሲዮን በመግዛት እና ነባር አክሲዮን በመግዛት መካከል ያለው ልዩነት፤ እድል እና ስጋት! አክሲዮኖችን መግዛት ኢንቨስትመንት መሆን የሚችለው የተጠና እና ምክንያታዊ ሲሆን ነው። የአክሲዮን ትርፋማነት እንዴት ይለካል?


ስለዚህ አዲስ የሚመሰረት አክሲዮን ለመግዛት እና ስራ ከጀመሩ ተቋማት ነባር አክሲዮን ለመግዛት ከመወሰን በፊት ከግምት መከተት ያለባቸው ጠቃሚ ሃሳቦችን

ይመልከቱ።
4.6K viewsWasyhun Belay, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 19:54:03 አንዳንዶች ስለራሴ ይጠይቁኛል፦ በትምህርት ተቋማት የኢኮኖሚክስ አስተማሪ አይደለሁም! መደበኛ ስራዬም ከኢኮኖሚክስ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ አይደለም! ነገር ግን እስከ ሁለተኛ ድግሪ ድረስ የተማርኩት ኢኮኖሚክስን በመሆኑ በየቀኑ በሱ ዙሪያ ለጥቂት ደቂቃም ቢሆን ለማንበብ እሞክራለሁ! ካወኩት ላይ ለእናንተም አጋራለሁ! በሱም ጥሩ ስሜት ይሰማኛል!
4.9K viewsWasyhun Belay, 16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 13:45:56 አዲስ አክሲዮን በመግዛት እና ነባር አክሲዮን በመግዛት መካከል ያለው ልዩነት፤ እድል እና ስጋት! አክሲዮኖችን መግዛት ኢንቨስትመንት መሆን የሚችለው የተጠና እና ምክንያታዊ ሲሆን ነው። የአክሲዮን ትርፋማነት እንዴት ይለካል?


ስለዚህ አዲስ የሚመሰረት አክሲዮን ለመግዛት እና ስራ ከጀመሩ ተቋማት ነባር አክሲዮን ለመግዛት ከመወሰን በፊት ከግምት መከተት ያለባቸው ጠቃሚ ሃሳቦችን

ይመልከቱ።
5.4K viewsWasyhun Belay, 10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 07:55:24 በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም!


በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን

በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።
5.2K viewsWasyhun Belay, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:37:40 በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም!


በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን

በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።
5.0K viewsWasyhun Belay, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 19:32:39 የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያ ወቅት ማለትም 1944 የዓለማችን 40 ሀገራት 730 ተወካዮቻቸውን በመላክ አሜሪካ ውስጥ የወርቅ ክምችትን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን ለመጠቀም ሶስት ሳምንታት የፈጀ ውይይት በማድረግ ስምምነት ላይ ደረሱ ስምምነቱ በአካባቢው ስያሜ Bretton Woods Agreement ይባላል፡፡


የምንዛሬ ተመኑ ዓላማ በፉክክር ምክንያት የሚፈጠር የገንዘብን የመግዛት አቅም የማዳከም አደጋን የመቀነስ እና ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገትን የመፍጠር ነበር፡፡ ዋናዎቹ የስምምነቱ ተዋናዮች አሜሪካ፤ ካናዳ፤ የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት፤ አውስትራሊያ እና ጃፓንን የያዘ ነበር፡፡


ወርቅን እንደ ጠንካራ የዓለም የምንዛሬ ተመን የመጠቀም ስምምነት ሁለት ጠንካራ የዓለም ተቋማትን ፈጠረ እነሱም ምንዛሬን ለመቆጣጠር እና ገንዘብ ነክ የአስተዳደር ድጋፎችን ለማድረግ የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና የልማት ብድር እና ድጋፍ ለማድረግ የዓለም ባንክ (World Bank) ናቸው (ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት እስከ አሁን ድረስ 190 አባል ሃገራትን ይዘው ቀጥለዋል)፡፡


የዚህ ስምምነት የረጅም ዓመታት አጠንጣኞች ታዋቂው እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜይራንድ ኬይነስ ከአሜሪካዊው ኢኮኖሚስት ሃሪ ዲክሰር ጋር በመሆን ነበር፡፡


የጆን ሜይራንድ ኬይነስ ዓላማ ለዓለም ጠንካራ ማዕከላዊ ባንክ (የታሰበው መጠሪያ Clearing Union ነበር) ለመፍጠር እና ጠንካራ የዓለም መገበያያ ገንዘብ (የታሰበው መጠሪያ Bancor ነበር) ለመፍጠር ነበር፡፡ ነገር ግን አሜሪካዊው ኢኮኖሚስት በወቅቱ ጠንካራ የነበረው የአሜሪካ ዶላር እንዲመረጥ ሃሳብ በማቅረቡ አዲሱ ብር ሳይሳካ ቀረ፡፡


ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት በተግባር ከባድ ስለነበር እስከ 1958 በአግባቡ ለመተግበር አልቻለም! ነገር ግን 28 ግራም ወርቅ የ35 ዶላር ዋጋ እዲኖረው ወስነው ሲመነዝሩ ነበር፡፡ አካሄዱ ሌሎች ሃገራት ዶላር ለማግኘት ወርቅ የመሰብሰብ ግዴታ ውስጥ ሲገቡ አሜሪካ በዶላሯ ወርቅ የመሰብሰብ እድል አግኝታ ነበር፡፡


ሁኔታው የተለወጠው በ1971 በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኒክሰን አሜሪካ ዶላርን በወርቅ መተመን እንደማትፈልግ በመግለጻቸው ወርቅን መገበያያ ምንዛሬ አድርጎ የመጠቀሙ ስምምነት ከተቋቋመ ከ20ዓመታት በኋላ ፈረሰ፡፡ በወቅቱ ሀገራት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ለመፍጠር የነበራቸው ህልም በመክሸፉ በወቅቱ ጠንካራ የነበረውን የአሜሪካ ዶላር እንደ ዓለም አቀፍ መገበያያ ተመን አድርገው መውሰድ ጀመሩ፡፡ እስካሁንም ዶላር ዓለምን ዘዋሪ ሆኖ ዘልቋል፡፡
5.6K viewsWasyhun Belay, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-28 18:34:27 28 ግራም ወርቅ 35 ዶላር የሚመነዘርበት ወቅት! በዓለም ላይ የወርቅ ክምችት እንደምንዛሬ የሚቆጠርበት ጊዜ እና ወርቅ በዶላር የመቀየር ልምምድ| "Bancor" የተባለው ዓለም አቀፍ ገንዘብ በዶላር የመሸነፍ ሚስጥር| ዶላርን የዓለም ዘዋሪ ገንዘብ ያደረገው አጋጣሚ!


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ትንታኔ ይመልከቱ! ለሌሎችም እንዲማሩበት አጋሩት!
5.8K viewsWasyhun Belay, 15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ