Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-01 07:08:41
በዓለም ላይ የሰራተኞች ቀን መከበር የተጀመረበት ዋና ዓላማ የሰራተኛውን መደብ ታታሪነትና ትጋት እውቅና መስጠት፣ ለሰራተኛው መብቶቻቸውን በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር እና ሰራተኛውን ከብዝበዛ መጠበቅ ነው።


ከኢኮኖሚ የእድገት ምንጭ (Economic Factors) መካከል አንዱ ሰራተኛ (Labor) ነው! ስለዚህ የኢኮኖሚ ሞተር ለሆናችሁ #በላብ አደሮች በሙሉ ለምትታሰቡበት ቀን እንኳን አደረሳችሁ!
1.9K viewsWasyhun Belay, 04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:55:53 የኢትዮጵያን ገንዘብ "ብር" እየተዳከመ ያለው በፖለቲካ ወይስ በኢኮኖሚ አመክንዮ?



2.7K viewsWasyhun Belay, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 14:40:05 ጠንካራ ምንዛሬ እንዴት ይፈጠራል?| ብርን ከዶላር አንፃር ጠንካራ ማድረግ ይቻላል?


ብዙዎቻችሁ የየዕለት ግብይቶቻችሁን የምታከናውኑት በ "ኢትዮጵያ ብር" በመሆኑ የምንዛሬ ጉዳይ በኑሯችሁ እና በያዛችሁት ብር ላይ እየፈጠረ ያለውን ጫና ልብ አትሉም! ምክንያቱም.......


በሰው ሰራሽም (Artificial Currency Rate) ሆነ በትክክለኛው (Real Currency Rate) መንገድ ምንዛሬን ከፍ እና ዝቅ ማድረግ ይቻላል! ውጤቱ ግን......


ኢትዮጵያ ስለ ብር የመግዛት አቅም መዳከም (Devaluation) በምትሰጠው ትኩረት ልክ ብርን ከዶላር አንፃር ተገዳዳሪ ለማድረግ ምን ማድረግ ትችል ነበር?


የምንዛሬ ሁኔታ የሁላችንንም ህይወት እንዴት ነው እየነካ ያለው? አንድ የኩዌት ዲናር (የዓለም ጠንካራው ምንዛሬ) ለመግዛት ከ3 ዶላር በላይ ያስፈልጋል (አንድ ዶላር ለመግዛት 54-100 ብር ያስፈልጋል) ልዩነቱን ምን አመጣው?


ይህንን እና ሌሎች መሰረታዊ የምንዛሬ ነጥቦችን ለመረዳት የሚከተለውን ትንታኔ

ተመልከቱ ለሌሎችም እንዲማሩበት አድርጉ።
3.0K viewsWasyhun Belay, 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:35:24 ሁሉም ሰው ስለ ኢኮኖሚክስ መሰረታዊ የሚባሉትን ነጥቦች ቢያውቅ ጥሩ ነው!

Subscribe

3.3K viewsWasyhun Belay, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 07:58:02 የማይክሮ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ልዩነት!

የመንግስት የኢኮኖሚ ሪፖርት እና የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ባለመጣጣሙ ከሚነሱ ውዥንብሮች መሰረታዊ ምክንያት መካከል ዋነኛው መንግስት ስለማክሮ ኢኮኖሚ (የዋጋ ንረት፤ ጠቅላላ ምርት መጠን፤ ገቢ፤ የምንዛሬ ተመን፤ የገንዘብ አቅርቦት፤ ወዘተ) ሲያቀርብ ሰዎች የሚኖሩበት የማይክሮ ኢኮኖሚ (መሸመት እና ማምረት) ስርዓት ውስጥ በመሆኑ ነው!

ስለዚህ የኢኮኖሚ ስርዓት የሚመራበትን የማይክሮ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ምንነት፤ ልዩነት፤ ተግባር እና ፋይዳ ላይ የሚከተለው አስተምሮ

ተመልከቱ፡፡
1.1K viewsWasyhun Belay, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 16:49:25 የማይክሮ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ልዩነት!

የመንግስት የኢኮኖሚ ሪፖርት እና የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ባለመጣጣሙ ከሚነሱ ውዥንብሮች መሰረታዊ ምክንያት መካከል ዋነኛው መንግስት ስለማክሮ ኢኮኖሚ (የዋጋ ንረት፤ ጠቅላላ ምርት መጠን፤ ገቢ፤ የምንዛሬ ተመን፤ የገንዘብ አቅርቦት፤ ወዘተ) ሲያቀርብ ሰዎች የሚኖሩበት የማይክሮ ኢኮኖሚ (መሸመት እና ማምረት) ስርዓት ውስጥ በመሆኑ ነው!

ስለዚህ የኢኮኖሚ ስርዓት የሚመራበትን የማይክሮ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ምንነት፤ ልዩነት፤ ተግባር እና ፋይዳ ላይ የሚከተለው አስተምሮ

ተመልከቱ፡፡
2.3K viewsWasyhun Belay, 13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 08:36:48 Statement of the Problem

በጥናት ስራ ወቅት #ትክክለኛውን (Significant Problem) በርዕሰ ሀሳቡ ውስጥ ማመልከት አስፈላጊም ፈታኝም ነው። ብዙ ተማሪዎች በጥናታቸው ማረጋገጥ የፈለጉትን ጭብጥ በግልጽ ለመዘርዘር ይቸገራሉ።


ለአብዛኞች የርዕስ ምንጭ ኢንተርኔት ነው! እኔ በግሌ ከመማሪያ መፅሃፎቻችሁ፤ ከስራ ልምዶቻችሁ፤ ከምትመለከቱት ሁኔታ፤ ከግል ፍላጎቶቻችሁ በመነሳት የምትችሉትን፤ ዳታ የሚገኝበትን እና የእናንተ የሆነ (Orginal)/በሌሎች የተሰራም የርዕስ ሃሳብ ከሆነ ከቀደሙ ስራዎች የተለየ አተያይ ያለው ጥናት ብትሰሩ ጥሩ ነው።


#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ይደውል እና ርዕሴ "The #impact of unemployment on household welfare" ነው ይላል! ታዲያ በጥናት ማረጋገጥ የፈለከው ጉዳይ ምንድን ነው? ሲባል "ስራ አጥነት ለቤተሰብ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለሟሟላት ያለው ጫና" ይላል። ልብ በሉ Impact በአማርኛ ትርጓሜው #ጫና ነው እያለ ነው!


ከላይ ያለውን ምሳሌ ተከትሎ አጥኚው ስራ አጥ መሆን ያለውን #አሉታዊ_ጫና (Negative Impact) ሊፈልግ ነው ማለት ነው። ከዛ ስራ አጥ መሆን ገቢ እንዳይኖር ስለሚያደርግ ቤተሰቡ ድሃ ይሆናል/ይራባል (Research Hypothesis) የሚል አይነት ውጤት በመፈለግ ላይ ይሆናል ትኩረቱ (ሂደቱን ልብ ላይለው ይችላል)።


እዚህ ጋር ሁለት ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች አሉ፦

#አንደኛው፦ የጥናቱን ውጤት ዳታ ሰብስቦ ውጤት ከመተንተኑ በፊት ወደ እርግጠኝነት የቀረበ ግምት እያስቀመጠ ነው። ስለዚህ ምን አልባት ጥናቱ ሲጠናቀቅ የጥናቱ ውጤት ስራ አጥ መሆን መሰረታዊ (Significant) ችግር ቤተሰቦች ላይ አይፈጥርም! የሚል ከሆነ፡ እንዴት ብሎ? ለመቀበል በመቸገር ውጤት ወደ መለወጥ (Manipulation) ሊገባ ይችላል።


አስታውሱ ጥናት ማለት ከሚታወቅ መነሻ ወደ የማይታወቅ እውነት መሄድ ነው "Known To Unknown" ምን ማለት ነው? በላይኛው ምሳሌ አጥኝው ጥናት ከመጀመሩ በፊት ስራ አጥነት ተፅኖ እንዳለው ያውቃል። ነገር ግን #በዳታ እስካላረጋገጠ ድረስ ስራ አጥነት እንዴት (Negative/Positive? እና በምን ያህል ጥልቀት? (Significance Level) ተፅኖ እንዳለው ማወቅ አይችልም (መላምት ወይም Hypothesis ማስቀመጥ ግን ይችላል!)።


#ለምሳሌ፦ አንድ Independent Variable በጥናት ማረጋገጥ የተፈለገውን ውጤት (Dependent Variable) 89% ያህል ተፅኖ የመፍጠር አቅም ቢኖረው፡ እውነት ነው ተፅኖ አለው! ነገር ግን መሰረታዊ (Significant) የችግሩ መንስሄ አይደለም፡፡ ለዚህ ሲባል ነው በአብዛኛው በ90%, 95%, 99% አስተማማኝነት (Significance Level) ድረስ ብቻ የምትተነትኑት #ተፅኖ እና #መሰረታዊ_ተፅኖ የሚለውን ለመለየት ነው።


ማህበራዊ ሳይንስ ጥናት የምትሰሩ ተማሪዎች ዝቅተኛው 90% አስተማማኝነት (Significance Level) ቢፈቀድም የተፈጥሮ ሳይንስ ነክ ጥናት ለምትሰሩ ዝቅተኛው ከ95% አስተማማኝነት (Significance level) በታች እንዲሆን አትመከሩም።


በማህበራዊ ሳይንስ እስከ 90% Significance level ለምን ተፈቀደ? ካላችሁ በአብዛኛው በማህበራዊ ሳይንስ #ባህሪያዊ ጥናት (Quasi-Experimental) ስለሚከናወን ውጪያዊ ተፅኖዎችን ለመቆጣጠር ስለሚያስቸግር ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ Variable በአብዛኛው ከተፅኖ ነፃ ስለሚሆኑ ወደ ትክክለኛነት የቀረቡ የመሆን እድል ይጠበቅባቸዋል (#ለምሳሌ፦ መድሃኒት የማዳን አቅሙ በጥናት ከ95% በላይ የተረጋገጠ መሆኑን ማሳየት ይገባል እንደማለት ነው)። #ለምሳሌ፦ በማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ድሃ የመሆንን 90% ምክንያት ለመግለጽ እንኳን ፈታኝ ነው።


#ሁለተኛው፦ Impact, Effect, Determinant.....ብሎ የጀመረ ርዕሰ አሉታዊ (Negative) ችግር እየለየ ነው ብሎ ማለት አይደለም። የአንድ ጉዳይ ተፅኖ/Impact እያጠናቹ ነው ማለት መልካምም መጥፎም ተፅኖ ነው እያረጋገጣችሁ ያላችሁት። ምክንያቱም የውጤት ዝርዝራችሁ ላይ ቤታ ወይም ኮፊሸንት ሲነበብ Negative ወይም Positive እና የሚያወጣው ተፅዕኖው አሉታዊም አዎንታዊም ነው እያላችሁ ነው።


#ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በንግግሩ "ስራ ማጣቴ በህይወቴ Impact ፈጥሮብኛል" ቢል! ወዲያው ማመን የምትጀምሩት #ጉዳት ፈጥሮብኛል (ተርቢያለሁ፤ ተስፋ አስቆርጦኛል፤ ወዘተ) ማለቱን ነው እንጂ "ስራ አጥ መሆኔ የተሻለ የህይወት አረዳድ ሰጥቶኛል ወይም የፈጠራ ሃሳብ እንዳመነጭ አግዞኛል" እያላቹ እንደሆነ አትገምቱም። ነገር ግን ጥናት ስትሰሩ የተፅኖ ትርጉም እናንተ ሳትሆኑ ዳታው ነው አዎንታዊ/አሉታዊ ወይም Negative/Positive ማለት ያለበት።


በተመሳሳይ የጥናት ሀተታ ወይም Statement of the Problem ስታስቀምጡ ስለምታጠኑት ጉዳይ ችግር እየዘረዘራችሁ ሳይሆን የጥናታችሁን የቀደመ አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅኖ እያሳያችሁ ነው።
4.6K viewsWasyhun Belay, 05:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 20:28:23 ኢትዮጵያ የDual Exchange Rate ልትጀምር ትችላለች?|ባንኮች በጥቁር ገበያ ተመን ዶላርን መመንዘር ሊጀምሩ ይችላሉ? የዛሬ 2 ወር ያነሳሁት ሃይፖተሲስ ቢሆንም ድጋሚ ተመልከቱት.......


የገንዘብን የመግዛት አቅም በተለያየ ምክንያት ማዳከም አስፈላጊ ነው ተብሎ በታመነ ጊዜ ወይም ምንዛሬን ከቁርጥ ተመን ወደ ገበያ መር ለማዞር በሚደረግ ሽግግር ወቅት ጠቅላላ ገበያውን በአንዴ እንዳያናጋው ዘርፍ ወይም የንግድ ሁኔታው በመለየት የተለያየ የምንዛሬ መጠንን ተግባራዊ ማድረግ (አንዱን ዘርፍ በቁርጥ ተመን (Fixed Exchange Rate) መምራት ሌላው ዘርፍ በገበያ ተመን (Floating Exchange Rate) መምራት) ማለትም መንግስት በአንድ ሀገር ውስጥ የተለያየ የውጪ ምንዛሬ ተመን ሲጠቀም Dual Exchange Rate ወይም Multiple Foreign Exchange Rate ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ ወደዚህ የምንዛሬ ስልት ልትገባ ትችላለች? ብትገባ ጉዳቱ ምንድን ነው? ወይስ ሌላ ምርጫ አላት? ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን

ምርጥ ትንታኔ እስከመጨረሻው ተከታተሉት! ለሌሎች ያጋሩ።
4.3K viewsWasyhun Belay, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 08:14:29
አፍሪካ በኢኮኖሚ ሪፖርቶች ላይ በአብዛኛው ለሁለት ነው የምትከፈለው! ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል እና የሰሜን አፍሪካ ክፍል በማለት! የአፍሪካ የሰሜኑ ክፍል ያሉት ግብጽ፤ ሞሮኮ፤ አልጄሪያ፤ ሊቢያ፤ ቱኒዚያን እና ሱዳን (የሱዳን ክርክር ያለበት ቢሆንም)፤ በድምሩ 257 ሚሊየን ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ሲሆን በአንጻራዊነት የተሻለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት ነው፡፡

የተቀሩት የአፍሪካ ሃገራት በጆግራፊካል አቀማመጥ የምስራቅ፤ የምዕራብ፤ የመካከለኛው እና የደቡቡን የአፍሪካ አካባቢ የሚያካልሉት እና ከሰሃራ በርሃ ደቡባዊ ጫፍ የሚጀምሩት ሀገራት ከ54ቱ የአፍሪካ ሃገራት ከ46 በላዮቹ የሚገኙበት ሆኖ የ1.2 ቢሊየን ህዝብ መኖሪያ ሲሆኑ በድህነት መጠናቸው በአንጻራዊነት የከፋ ነው፡፡
4.2K viewsWasyhun Belay, 05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 09:51:31 ከPlagiarism ነፃ የሆነ የጥናት አሰራር (Plagiarism Free Content)!


የሌሎችን የጥናት ውጤት የራስ አድርጎ መስራት ወይም ተገቢውን ምንጭ ያለመጥቀስ በጥናት ስራ ውስጥ ወንጀል ነው። ስለዚህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚፈጠርን የመመሳሰል (Plagiarism) ችግር እንዴት ሊቀረፍ ይችላል?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ

በመመልከት ተማሩበት ለሌሎችም እንዲጠቀሙበት አጋሩት።
1.9K viewsWasyhun Belay, 06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ