Get Mystery Box with random crypto!

አፍሪካ በኢኮኖሚ ሪፖርቶች ላይ በአብዛኛው ለሁለት ነው የምትከፈለው! ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል | The Ethiopian Economist View

አፍሪካ በኢኮኖሚ ሪፖርቶች ላይ በአብዛኛው ለሁለት ነው የምትከፈለው! ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ክፍል እና የሰሜን አፍሪካ ክፍል በማለት! የአፍሪካ የሰሜኑ ክፍል ያሉት ግብጽ፤ ሞሮኮ፤ አልጄሪያ፤ ሊቢያ፤ ቱኒዚያን እና ሱዳን (የሱዳን ክርክር ያለበት ቢሆንም)፤ በድምሩ 257 ሚሊየን ህዝብ የሚኖርበት አካባቢ ሲሆን በአንጻራዊነት የተሻለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ያለበት ነው፡፡

የተቀሩት የአፍሪካ ሃገራት በጆግራፊካል አቀማመጥ የምስራቅ፤ የምዕራብ፤ የመካከለኛው እና የደቡቡን የአፍሪካ አካባቢ የሚያካልሉት እና ከሰሃራ በርሃ ደቡባዊ ጫፍ የሚጀምሩት ሀገራት ከ54ቱ የአፍሪካ ሃገራት ከ46 በላዮቹ የሚገኙበት ሆኖ የ1.2 ቢሊየን ህዝብ መኖሪያ ሲሆኑ በድህነት መጠናቸው በአንጻራዊነት የከፋ ነው፡፡