Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-04 20:43:28 ስለ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በጥልቀት ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው በሙሉ የተከፈተ ቻናል!
If you are passionate about Economics, This page is for you!


Subscribe

373 viewsWasyhun Belay, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 14:45:33 የአንዱ ሴክተር ወይም ሀገር መዳከም አልያም መነቃቃት ለሌላው ሴክተር ወይም ሀገር ላይ ያለው ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ተጽኖ/Spillover Effect ይባላል፡፡ በተለምዶ Spillover Effect ለአሉታዊ ተጽኖ (Negative Spillover Effect) መግለጫ ሆኖ የሚቀርብ ቢሆንም ለአዎንታዊ ተጽኖም (Positive Spillover Effect) መገለጫ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን በዓለም ገበያ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው እና ማዕቀብ ውስጥ በመግባታቸው በዓለም ውስጥ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በመቀነሱ በዋናነት ሰፊ የንግድ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ተጽኖ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ሁኔታ ሌሎች ሀገራት በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምክንያት Negative Spillover Effect ደረሰባቸው ይባላል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ የዓለም ማዕቀብ ስለተጣለባት ህንድን አጋር ሀገር በማለት በርካሽ ነዳጅ ብታቀርብላት እና የህንድ ኢኮኖሚ መነቃቃት ቢያሳይ በራሽያ ጦርነት ሰበብ ህንድ Positive Spillover Effect ደረሰባት ሊባል ይችላል (ናይጄሪያ ጦርነቱን ተከትሎ የነዳጅ ገበያዋ ደርቷል ይህም በተመሳሳይ አወንታዊ ተጽኖ ሊባል ይችላል!)፡፡

ቀጥተኛ የትርፍም ሆነ የኪሳራ ተካፋይ የማይሆን ነገር ግን ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚጋሩ የኢኮኖሚ ክፍሎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን መሰረት በማድረግ ራሽያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በሶስተኛ ሀገራት ላይ የሚፈጠር ከራሽያ መሸመት ያለመቻል ችግር Externalities Spillover Effect ሊባል ይችላል፡፡

#ለምሳሌ፡- የአትክልት ማሳዎች ምርታምነት ቢሻሻል ለአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አወንታዊ ተጽኖ ሊፈጠርለት ይችላል፤ አፋር ክልል ችግር ውስጥ ቢገባ ሌላው ክልል በጨው አቅርቦት እጥረት አሉታዊ ተጽኖ ሊፈጠርበት ይችላል፤ በሀገር ውስጥ ለቻይና ተቋራጭ ፕሮጀክት መስጠት የእውቀት ሽግግር ቢፈጠር አዎንታዊ ተጽኖ ሊፈጠር ይችላል፤ የሶሻል ሚዲያ መምጣት ለጥቂቶች ገንዘብ መስሪያ ለብዙዎች የወጪ ምክንያት ሆኗል! ወዘተ ማለት ነው፡፡

በዚህ ወቅት የዓለም ሀገራት ኢኮኖሚ በጣም የተሳሰረ ከመሆኑ የተነሳ የአንዱ ሀገር ኢኮኖሚያዊ መቀዛቀዝም ሆነ በፍጥነት ማደግ ሌሎች ሀገራት ላይ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ መፍጠሩ አይቀርም ይሁ ሁሉ Spillover Effect ይባላል፡፡
2.6K viewsWasyhun Belay, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 19:19:29 በኢትዮጵያ የሞንተሪ እና የፊስካል ፖሊሲዎችን እየመሩ ያሉት የትኞቹ ተቋማት ናቸው? ለድህነት ቅነሳ አቅም ያለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ የትኛው ነው?



1.5K viewsWasyhun Belay, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 11:15:30 መሰረታዊ የሚባሉት የኢኮኖሚ መሳሪያዎች በሁለት ይከፈላሉ፦ እነሱም የሞንተሪ/Monetary ፖሊሲ (የገንዘብ ስርጭት ቁጥጥር፤ የወለድ ተመን፤ የውጪ ምንዛሬ ተመን እና የፋይናንስ ተቋማት ቁጥጥር) እና የፊስካል/Fiscal ፖሊሲ (የግብር፤ የቀረጥ እና የበጀት) ናቸው።


ከሁለቱ የፖሊሲ አማራጮች የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር፤ የዋጋ ንረት እና ስራ አጥነትን ለመቀነስ ውጤታማው የትኛው ነው? በሁለቱ ፖሊሲዎች መካከል በጥምረት መስራት ላይ ችግር የሚሆነው ምክንያት ምንድን ነው?


በኢትዮጵያ ሁለቱን ፖሊሲዎች የሚመሩት ተቋማት የትኞቹ ናቸው? ከላይ ከተዘረዘሩት ጥያቄዎች በተጨማሪ ሰፊ ማብራሪያ ያለበትን ቪዲዮ

ተመልከቱ ለሌሎችም ግንዛቤ እንዲያገኙበት አጋሩት።
2.5K viewsWasyhun Belay, 08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:21:38 ጤነኛ የሚባለው የወጪ ዝርዝር ቀመር (The Golden Rule of Budgeting!)

ሰዎች ከገቢዎቻቸው ላይ የሚያወጡት ወጪ በዘፈቀደ ሳይሆን በስሌት መሆን አለበት! (በ50/30/20 ወይም በ30/30/30/10 ወይም በ80/20 ቀመር መሰረት) ስለሆነም ከወጪያችሁ ለመሰረታዊው (Need) እና ለፍላጎቶቻችሁ (Want) ምን ያህል ድርሻ መስጠት አለባችሁ? እንዲሁም ምን ያህል መቆጠብ መቻል ነው ጤነኛ በሆነው የወጪ ዝርዝር ውስጥ እንዳላችሁ የሚያሳየው?

በአዲስ አበባ በተደረገ የቀደመ ጥናት ሰዎች ከ50/30/20 ወርቃማው የወጪ ዝርዝር ህግ አንጻር ያሉበትን ደረጃ ቪዲዮው

ላይ በመመልከት እናንተ ደግሞ ያለባችሁበትን ደረጃ በማስላት ተጠቃሚ ይሁኑ!

Subscribe በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ Share ያድርጉት!
1.3K viewsWasyhun Belay, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 09:45:55 ጤነኛ የሚባለው የወጪ ዝርዝር ቀመር (The Golden Rule of Budgeting!)

ሰዎች ከገቢዎቻቸው ላይ የሚያወጡት ወጪ በዘፈቀደ ሳይሆን በስሌት መሆን አለበት! (በ50/30/20 ወይም በ30/30/30/10 ወይም በ80/20 ቀመር መሰረት) ስለሆነም ከወጪያችሁ ለመሰረታዊው (Need) እና ለፍላጎቶቻችሁ (Want) ምን ያህል ድርሻ መስጠት አለባችሁ? እንዲሁም ምን ያህል መቆጠብ መቻል ነው ጤነኛ በሆነው የወጪ ዝርዝር ውስጥ እንዳላችሁ የሚያሳየው?

በአዲስ አበባ በተደረገ የቀደመ ጥናት ሰዎች ከ50/30/20 ወርቃማው የወጪ ዝርዝር ህግ አንጻር ያሉበትን ደረጃ ቪዲዮው

ላይ በመመልከት እናንተ ደግሞ ያለባችሁበትን ደረጃ በማስላት ተጠቃሚ ይሁኑ!

Subscribe በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ Share ያድርጉት!
2.6K viewsWasyhun Belay, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 08:55:46 #Invisible_Hand
ስውሩ እጅ የሚመጣው ከየት ነው?



1.2K viewsWasyhun Belay, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 15:39:50 ኢትዩጵያ ውስጥ ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት መሰረታዊ ምክንያቶች የሚመነጩት ከየት ነው?

1.4K viewsWasyhun Belay, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 07:37:39 ከገጠር ወደ ከተሞች የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት መሰረታዊ ምክንያቶች የሚመነጩት ከየት ነው? ከኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች መካከል ክብደት የሚወስደው የትኛው ነው? መንግስት ለምን ነጠላ ምክንያት ላይ ያተኩራል?

2.4K viewsWasyhun Belay, 04:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 09:43:58 አዳም ስሚዝ ለምን የኢኮኖሚክስ አባት ተባለ?፦ የዛሬ 300 ዓመት (1723-1790) የነበረው ኢኮኖሚስት እና ፊሎሰፈር አዳም ስሚዝ/Adam Smith ስለነፃ ገበያ (Free market)፤ የሠራተኛ ክፍፍል (Division of Labor) እና የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) መለኪያ ዙሪያ ባቀረባቸው ሃሳቦች ለ3 ክፍለ ዘመን የዘለቀ ተፅዕኖዎቹን እና ለምን የኢኮኖሚክስ/የዘመናዊ ኢኮኖሚክስ አባት እንደተባለ በዝርዝር ተመልከቱ።

#Subscribe ማድረግ አይርሱ!

163 viewsWasyhun Belay, 06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ