Get Mystery Box with random crypto!

Amhara Bank S.c

የቴሌግራም ቻናል አርማ amarabank — Amhara Bank S.c A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amarabank — Amhara Bank S.c
የሰርጥ አድራሻ: @amarabank
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77
የሰርጥ መግለጫ

Beyond Finance
ከባንክ ባሻገር

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 10:08:02 እንኳን ለኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
አማራ ባንክ
ከባንክ ባሻገር

https://t.me/Amarabank
49.1K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 19:16:14
16.4K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 19:15:38
አማራ ባንክ በነገው እለት በይፋ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ለገሃር
በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል።
አማራ ባንክ! ከባነክ ባሻገር!
16.4K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 12:57:39 አማራ ባንክ ሰኔ 11 2014 ስራዉን በይፋ እንደሚጀምር አስታወቀ።

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባንኩ የምረቃ እለትም 70 የተሟሉ ቅርጫፎች የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

እሰከ ሰኔ 30 ባሉት ቀናቶች ባንኩ ቅርጫፎቹን ወደ ከ100 በላይ የሚያሳድግ መሆኑንም ገልጿል።

የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚዉን ለማሳደግ የተከፈተ ባንኩ ሲሆን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽዎ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነዉ ብለዋል።

የሕዝብ ባንክ መሆኑን አንስተዉ እሰካሁን በብሄራዊ ባንክ ደንብ መሰረት የአክሲዮን ሸያጭ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዉ በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች አክሲዮኖች ተሽጠዋል ብለዋል።

የካቲት 2/2014 ዓ.ም ዋና እና ምክትለረ ስራ አስፈጻሚዎችን ማስመረጡን አንስተዋል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸዉ እስከ ሰኔ 30 አጠቃላይ መቶ ቅርጫፎች ስራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዉ ሰኔ 11 ላይ በመክፈቻዉ 70 ቅርጫፎች ስራ ይጀምራሉ ብለዋል።

የሰራተኛ እና የስራ ቁሳቁስ ግብዓት የማሟላት ስራዎች ተሰርተዋል ሲሉ ገልጸዋል ዋና መሪ ቃሉን "ከባንክ ባሻገር "ብሎ የጀመረዉ አማራ ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በስራዎቹ እንደሚወጣ አስታዉቋል።

እስከ ሰኔ 11 ባሉት ቀኖችም ባንኩ የፓናል ዉይይት፣ የደም ልገሳ እና ሌሎችም መርሀ ግብሮች እንደሚኖሩት አስታዉቋል።

ባንኩ የማህበራዊ አገልግሎቱን ለመወጣት እንዲያስችለዉ ሰኔ 11 ቀን ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽት 3 ሰአት ድረስ የአምበሳ ባስ ተጠቃሚዎችን ወጭ መሸፈኑን አስታዉቀዋል።

ተጠቃሚዎችም በእለቱም ያለምንም ክፍያ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉም አስታዉቋል።

ባንኩ ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ስራዉን የጀመረ ሲሆን እስካሁንም ከ4 ቢሊየን ብር በላይ በስራ ላይ ማዋሉን ባንኩ አስታዉቋል።
19.2K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 10:34:14
54.5K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 13:07:15 አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ)

ክቡራን የአማራ ባንክ አ.ማ. (በምስ ኤጀንሲ በጻፈው ደብዳቤ ባለአክስዮኖች በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው በባንኩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡

ክቡራን ባለአክስዮኖች ፊርማችሁ ባንኩን ስራ ለማስጀመር እና የባንኩ ባለአክስዮን መሆናችሁን ለማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ ተግባር መሆኑን እያስታወቅን ፣ ባለአክስዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች ከጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ቀርባችሁ በባንኩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማችሁን እንድታኖሩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡


ባለአክሲዮኖች ለፊርማ ሲመጡ፦

● አክስዮን የገዙበትን ፎርም እና ክፍያ የፈጸሙበትን የባንክ ስሊፕ ፣ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ፣ ፖስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆኑ ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቢጫ ካርድ እና ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ፤ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

● ወኪል ከሆኑ ውል ለመዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውን ከአንድ ኮፒ ጋር እና ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መፈረም የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን ፣ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ወኪሎች ከውክልና ማስረጃ በተጨማሪ የወካዮቻችሁን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ ቢጫ ካርድ ይዛችሁ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡

● የንግድ ማህበራትን በተመለከተ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችንና ቅድመ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በሪፖርተር እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡

ማሳሰቢያ


● ከዚህ ቀደም አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ያደረገውን ጥሪ ተቀብላችሁ ፣ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንዲሁም በህግ ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ፊት ቀርባችሁ ለባንኩ አደራጆች ውክልና የሰጣችሁ ባለአክስዮኖች በወኪሎቻችሁ አማካኝነት የሚፈረምላችሁ በመሆኑ ፣ በድጋሜ ቀርባችሁ መፈረም የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

● አክስዮን በምትፈርሙበት (በምትገዙበት) ጊዜ ሙሉ ስማቹህን እና አድርሻቹህን አሟልታቹህ ያላስመዘገባቹህ ባለአስክዮኖች ፣ ከዚህ ቀደም ውክልና ብትሰጡም ባትሰጡም በግንባር ቀርባቹህ መረጃቹህን የማሟላት ግዴታ ያለባቹህ መሆኑን እናስታውቃለን። መረጃቹህ ያልተሟላ ባለአክስዮኖች ፣ መረጃቹህ እስኪሟላ ድረስ ስማቹህ በባንኩ የአክስዮን መዝገብ የማይገባ እና ባለአክስዮን ለመሆን የማትችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።


● በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ከተደቀነው ስጋት አንጻር ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ፣ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንድታደርጉ እናስታውቃልን፡፡



አማራ ባንክ አ.ማ.
(በምስረታ ላይ)
174.3K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-26 13:07:06
119.6K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-16 16:02:48
እንኳን ለ1496ኛው ዓመት የነብዩ መሀመድ (ሰ.ዓ.መ) የመውሊድ በዓል በሰላምና በጤና አደረስዎ!
133.2K views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-25 22:13:35 ውድ የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
አማራ ባንክ አ.ማ እንኳን ለ2014 ዓ.ም አዲስ አመት እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

አማራ ባንክ ምሥረታውን በማጠናቀቅ ስራ ለመጀመር ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስከረም 14/2014 ዓ.ም የፀደቀ ሲሆን፤ በቀጣይ ባንኩ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ለማግኘት እንዲያስችለው ባለአክሲዮኖች በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርባችሁ በባንኩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማችሁን እንድታኖሩ ይጠበቃል።
ከዚህ ቀደም ውክልና የሰጣችሁ ባለአክሲዮኖች በወኪሎቻችሁ አማካኝነት የሚፈርምላችሁ ሲሆን፤ ውክልና ያልሰጣችሁ ባለአክሲዮኖች ግን በቅርብ ቀን በምናስታውቀው ቀንና ቦታ በመቅረብ ባንኩን ስራ ለማስጀመርና የባንኩ ባለአክሲዮኖች መሆናቸሁን ለማረጋገጥ መፈረም የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እናስታውቃለን።

ለበለጣ መረጃ
0921943382
0921607902 ይደውሉ።

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ
180.0K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 19:26:27 ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ2014 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰላም፣ የጤናና የስኬት ይሁንልን።https://t.me/amarabank
206.4K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ