Get Mystery Box with random crypto!

The Ethiopian Economist View

የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View T
የቴሌግራም ቻናል አርማ wasealpha — The Ethiopian Economist View
የሰርጥ አድራሻ: @wasealpha
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.32K
የሰርጥ መግለጫ

Wase.belay12@gmail.com(0913243956)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-26 20:39:40 አዳም ስሚዝ ለምን የኢኮኖሚክስ አባት ተባለ?፦ የዛሬ 300 ዓመት (1723-1790) የነበረው ኢኮኖሚስት እና ፊሎሰፈር አዳም ስሚዝ/Adam Smith ስለነፃ ገበያ (Free market)፤ የሠራተኛ ክፍፍል (Division of Labor) እና የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) መለኪያ ዙሪያ ባቀረባቸው ሃሳቦች ለ3 ክፍለ ዘመን የዘለቀ ተፅዕኖዎቹን እና ለምን የኢኮኖሚክስ/የዘመናዊ ኢኮኖሚክስ አባት እንደተባለ በዝርዝር ተመልከቱ።

#Subscribe ማድረግ አይርሱ!

2.0K viewsWasyhun Belay, 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:46:02 ጥቂት ሰዎች "ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ መፅሃፍ ምን ትላለህ?" አሉኝ። በእርግጥ ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ የባለብዙ የቤትስራ ሃገር እየመሩ የመፃፊያ/የማፃፊያ ጊዜ እና ተመስጦ ማግኘታቸው እየገረመኝ ነው መሰለኝ እስካሁን የፃፏቸውን መፅሃፍት አንብቤ አላውቅም! ነገር ግን የመፅሃፉቱ ሽያጭ ዓላማ መጥፎ አይደለም!
2.6K viewsWasyhun Belay, edited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 11:52:08 በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?


በዓለም ላይ የተለያዩ ገበያዎች አሉ! መንግስታት ሁሉንም የግብዓት ስርዓት የመቆጣጠር አቅም የላቸውም! በዋናነት በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ያለው ልዩነት ምንድን ነው? በነጭ፤ በግራጫ፤ በጥቁር እና በቀይ ገበያ ምን አይነት ቁሶች እና አገልግሎት እንደሚገበያዩ፤ ለምን ገበያዎቹ እየሰፉ እንደሆነ የሚከተለውን የመረጃ ዳሰሳ ጥናት ላይ በምሳሌ የተደገፈ ትንታኔ አቅርቤላችኋለሁ። እስከመጨረሻው ተከታተሉት።



3.3K viewsWasyhun Belay, 08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 20:05:21 አንድ ጥናት ስመለከት፦ "ዩክሬይን ከራሽያ ጋር የገባችበት ጦርነት ቆሞ በየዓመቱ በአማካይ በ3% የጠቅላላ ኢኮኖሚ (GDP) እድገት ቢኖራት የዛሬ ዓመት ወደነበረችበት ለመመለስ 13 ዓመት ይወስድባታል" ይላል።


"If we assume that in periods of growth, the Ukrainian economy grew by 3% on average, recovery after the war would take 13 years".


ከዚህ ቀደም በሶርያ ጦርነቱ ከተከሰተ ከ5 ዓመት በኋላ ተረጋግታ ቢሆን እንኳ ከጦርነቱ በፊት ማለትም 2009 ወደነበረችበት ለመመለስ ከ30 ዓመት በላይ ሊፈጅባት እንደሚችል ጥናት ቀርቦ ነበር።


"Syria's Economy Will Take At Least 30 Years to Recover, Says the U.N 2014".


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዚህ አውድ ቢጠና እንዴት ነው?
2.5K viewsWasyhun Belay, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 20:34:13 ቢሮክራሲ እና ሙስና ዋጋ ንረት ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ!


አምራቾችም ሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች በማምረትም ሆነ አገልግሎት በመስጠት ሂደት ውስጥ የሚገጥማቸውን ማንኛውም ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ወጪ በሙሉ የመጨረሻ ሸማች እና ተጠቃሚ ላይ እንዴት እንደሚደምሩት የሚከተለውን ትንታኔ

ተመልከቱ።
1.8K viewsWasyhun Belay, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 20:34:30 አፍሪካ የዓለምን 58% ከድህነት ወለል በታች ያለ ህዝብ ድርሻን ይዛለች! ነገር ግን ከድህነት ለመውጣት ከእቅዷ መካከል ከበለፀጉ ሀገራት የብድር እና የእርዳታ ጥያቄ እንደቀጠለ ነው።


"Existing debt relief mechanisms do not work well for Africa" ECA's Antonio Pedro.


የሚገርመው አፍሪካ ለመሰረታዊ ድህነቷ ምክንያት መካከል ሆን ተብሎ በሚከማች የውጪ እዳ ውስጥ መዝፈቅ መሆኑ በብዙ ጥናት እየተገለፀ የበለፀጉ ሀገራት ሆን ብለው ያከማቹትን እዳ ቀንሱ ስለተባሉ ይሳካል?
1.4K viewsWasyhun Belay, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 07:49:21 መንግስት ከወር በላይ የኢንተርኔት ገደብ መጣሉ እየፈጠረበት ያለው #Opportunity_Cost ዝቀተኛ ከሆነ የማናውቀው ብዙ ነገር አለ ማለት ነው!
3.0K viewsWasyhun Belay, 04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 11:47:37 በተለያዩ ምክንያቶች የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አንዴ ከፍ ካለ በጊዚያዊነት አቅርቦት ቢሻሻልም የጨመረ ዋጋ ወደ ነበረበት ለመመለስ ለምን ይቸገራል?


የዚህ ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን 4ቱን

ቪዲዮ ለመግለጽ ያህል።
866 viewsWasyhun Belay, 08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:33:19 አንዳንድ ወጣቶች "ስራ የማይጠፋበትና የሚያበላ ዘርፍ ምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ። በርግጥ የሚያበላም ሆነ በፍጥነት ስራ የሚገኝበት ስለሚባል የትምህርት መስክ ዛሬ ላይ መወሰን ከባድ ነው።



ልጅ ሆናችሁ በምትመኟቸው ዘርፎች ተመርቀው ለለት ፍጆታ ትግል ውስጥ ያሉ ብዙ ናቸው። ከዚህ ዩኒቨርስቲ መመረቅ እድል ነው ትሉባቸው ከነበሩ ተቋማት ወጥተው የሰራተኛው ገበያው ያልወሰዳቸው ብዙ ናቸው።  ምርጫቸውን ሰፊ ለማድረግ ከአንድ በላይ ድግሪ ይዘው በአንዱም ያልተቀጠሩ ትንሽ አይደሉም።


ኮሌጅ አልሄድም ብለው ብዙዎችን ቀጣሪ የሆኑ ብዙ ናቸው! ኢኮኖሚ ውስጥ አንዳንድ ከፍተኛ ገቢ እየተገኘባቸው ያሉ መስኮች የኮሌጅ ድግሪ ግዴታ የሆነባቸው አይደሉም።


ስለዚህ ለመማር ዛሬ ላይ ስትወስኑ ወቅታዊው የሰራተኛ ገበያ፤ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ እስከምርቃታችሁ እንደሚዘልቅ እርግጠኛ አትሁኑ።


የሰራተኛ ገበያው እና የቢዝነስ አዝማሚያው የሚወሰነው በጥረታችሁ እና ለሁኔታዎች ባላችሁ ተለዋዋጭ እይታ በመሆኑ ነባር መመዘኛዎችን በሂደት እየመረመሩ መሄድ ግድ ነው።
246 viewsWasyhun Belay, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 20:18:55 የመሰረታዊ ፍጆታ ገንዘብ ያለው ተከራይ እና የመሰረታዊ ፍጆታ እጥረት ያለበት የቤት ባለቤት መካከል ያለው ልዩነት #ተስፋ ብቻ ነው?


50% የሚሆኑ ዜጎቻቸውን የቤት ባለቤት ማድረግ ያልቻሉ የበለፀጉ ሃገራት አመክንዮ ምንድን ነው?


የዓለም መረጃ

2.4K viewsWasyhun Belay, 17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ